No summary available.
ታህሣሥ 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሽሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሚፍታህ ከድር - ጠበቃ አቶ ከበደ እጉማ ቀረቡ ተጠሪ፡- የባህር ትራንዚት አገልግልት - አቶ መላኩ መኮንን ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 2ዐ6ዐ8 የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ፤ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በከሣሽነት ቀርበው ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በመርከብ ያስጫንኩትን የንግድ ዔቃ ተጠሪ /ተከሣሽ/ ከመርከብ አራግፍና የወደብ ፍርማሉቲዎችን አጠናቅቆ ለማስረከብ ተስማምቶ ብር 287ዐ /የሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ብር/ የአገልግልት ክፍያ ተከፍልታል።
ሆኖም አስራሰባት ጥቅል ዔቃዎችን ሲያስረክብ ሁለት ጥቅል ዔቃ ያላስረከበ በመሆኑ የዔቃዎቹን ግምት ብር 3765ዐ /ሰላሣ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሣ ብር/ ከነወለደ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ የእኔ ግዳታ ከመርከብ የተራገፈትን ዔቃዎች አስፈላጊ የወደብ ፍርማሉቲዎችን በማስፈፀም ዔቃውን አስጭኖ ለባለዔቃው ማስተላለፍ፣ዔቃው የተጎዲ ከሆነ በአንሹራንስ አስመርምሮ የጉዲት ማረጋገጫ መቀበልና ለዔቃው ባለቤት ማስተላለፍ፤ ወይም በእጥረት የተደገፈ ከሆነ የእጥረት ማረጋገጫ ሰርቲፉኬት መቀበልና ለባለእዲው ማስተላለፍ ብቻ ነው። ከመርከብ የተፈለገውን ዔቃ የማስቀመጥ ኃላፉነት የለበትም። በመሆኑም በግዳታችን መሰረት የተወጣን በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የማስረዲት ሸክሙን አልተወጣም በማለት ክሱን ውድቅ ያደረገበት ሲሆን፤በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ተጠሪ በክሱ የተገለፀውን ገንዘብ ከነወለደ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። ተጠሪ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ፣ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ኃላፉ የሚሆንበት ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዳታ የለበትም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፣ ምክንያቱም ተጠሪ አስራዘጠኝ ጥቅል ዔቃ ከመርከብ የተራገፈና ከወደብ የደረሰ መሆኑን በማረጋገጥ በራሱ ደረሰኝ የመጋዘን ክፍያ አስከፍልኛል። ይኸ ከሆነ ዔቃውን ስላልተረከብኩ እኔ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የላለው ሲሆን ለጎደለው ሁለት ጥቅል ዔቃ ተጠያቂ እንደሚሆን አግባብነት ያላቸውን የሕግ ማዔቀፍች በማየት ለመረዲት ይቻላል። ስለዚህ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከሕግ ወይም ከውል የሚመነጭ ኃላፉነት ተጠሪ የለበትም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ የቅድሚያ ክፍያ የተፈፀመው ዔቃዎቹን ለማስተላለፍ እንጅ ዔቃዎቹን ስለተረከብን አይደለም፤ የወደብ ግልጋልት የሚሰጠው በኤርትራ የወደብ ባለሥልጣን ስለነበረ እነርሱ ለሚፈጽሙት ስህተት ተጠሪ ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት የላለ በመሆኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል፣ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካችና ተጠሪ በጽሐፍ ያቀረቡት ክርክር በአጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን፣ ይኸ ችልት የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በማስመጣት በግራ ቀኙ በኩል የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ተመልክቷል።
የአመልካችንና የተጠሪን የቃል ከርክር አዲምጧል። ስለሆነም ተጠሪ፣ የጠፈትን ሁለት ጥቅል ዔቃ ዋጋ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ጭብጥ በአግባቡ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ "የዔቃ አስተላላፉነት" ተግባር ምንድን ነው? የሚለውን መመለስ ይጠይቃል። የዔቃ አስተላላፉነት ተግባር ማለት በአገር ውስጥ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዔቃ ተቀባይነት ወይም ዔቃ ላኪን ለመወከል የጉምሩክ ሥነ ሥርዓትና የወደብ ሥነ ሥርዓት እና ላልች ሥነ ሥርዓቶችን አስፈጽሞ የገቢ ወይም የወጭ ዔቃዎች ከወደብ እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ የማድረግ ተግባር እንደሆነና ይኸም ተግባር የዔቃ ማስረከብን እና ማጓጓዝን ሥራ የሚጨምር ስለመሆኑ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው ሰነድች የተመለከተ ሲሆን በእኛም አገር ይህ ትርጓሜ ሕጋዊ ዔውቅና እና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስለ ዔቃ አስተላላፉነት ከደነገጋቸው ደንቦች ለመረዲት ይቻላል። ስለሆነም የተጠሪ የዔቃ አስተላላፉነት ግዳታና ኃላፉነት ከዚህ መሰረታዊ የሆነ ትርጓሜ አንፃር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
በሁለተኛ ደረጃ ተጠሪ በአመልካች የተሰጠውን የሥር ትእዛዝ በመቀበል፣ አመልካች ለአስራ ዘጠኝ ጥቅል ዔቃዎች የመጋዘን ኪራይ እና የአገልግልት ክፍያ እንዱከፍለ በመጠየቅ ክፍያውን በራሱ ደረሰኝ ተቀብሎል። ተጠሪ አስራ ዘጠኝ ጥቅል ዔቃዎች ከመረከብ መራገፊቸውንና መጋዘን ውስጥ መግባታቸውን በመግለጽ ከኤርትራ ወደብ አስተዲደር ጋር በተፃፃፊቸው ደብዲቤዎች ግልጽ አድርጓል። እነዚህ ማስረጃዎች በተጠሪ በራሱ የተዘጋጁ ሰነድች ናቸው። ስለዚህ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2ዐ18 መሰረት ሰነድቹ በአዘጋጃቸው በተጠሪ ላይ ዔቃዎቹ ወደብ ለመድረሣቸውና ለመራገፊቸው የአስረጅነት ዋጋና ክብደት ያላቸው ሲሆኑ ተጠሪ በራሱ የተዘጋጁትን ሰነድች ይዘትና ታዓማኒነት በመቃወም ሁለት ጥቅል ዔቃ አኔ አልተረከብኩም ስለዚህ በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የሕግ ድጋፍና መሰረት የላለው ነው።
በሶስተኛ ደረጃ ተጠሪ የሥራ ትእዛዝ የተቀበለባቸው ዔቃዎች በወደብ ያልተራገፈና አጥረት የተፈጠረ ከሆነ ኃላፉነት ካለበት አካል የእጥረት ሰርቲፉኬት በማውጣት ለአመልካች የማስተላለፍ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ አጥብቆ የሚከራከርበት ነጥብ ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የሥራ ትእዛዙን እንደተቀበለ ሁለት ጥቅል እቃ እጥረት ያጋጠመ መሆኑን ለእጥረቱ በኃላፉነት ከሚጠይቀው አካል የእጥረት ሰርቲፉኬት አውጥቶ ለአመልካች አልሰጠም። በተቃራኒው ተጠሪ አስራዘጠኝ ጥቅል ዔቃዎች እንዲለ በመግለጽ አመልካች ለአስራ ዘጠኝ ጥቅል ዔቃዎች የወደብና የመጋዘን ኪራይ እንደዚሁም የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈለው ጠይቆ ክፍያውን ተቀብሎል። ተጠሪ ሁለት ጥቅል ዔቃዎች ያጎደለ መሆኑን ለአመልካች ያሣወቀው ዔቃው ከወደብ ወደ አዱስ አበባ በሚጫንበት ጊዜ ነው። ይኸም ተጠሪ የአስተላላፉነት ግዳታውን በአግባቡ ያልተወጣና በዚህ ምክንያት አመልካች ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን ያረጋግጣል። ከላይ በዝርዘር የገለጽናቸው ምክንያቶች ተጠሪ የአስራ ዘጠኝ ጥቅል እቃዎች የወደብ መጋዘንና የአገልግልት ክፍያ ከአመልካች የተቀበለና ለአመልካችም የእጥረት ሰርቲፉኬት ያልሰጠ በዚህም ምክንያት አመልካች ላይ ጉዲት ያደረሰ መሆኑን አመልካች የሥራ ትእዛዝ ተቀብል የወደብ፣ መጋዘንና የአገለግልት ዋጋ ክፍያ የጠየቀበትንና ክፍያ የተቀበለበትን ግዳታውን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዲት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 179ዐ መሰረት በኃላፉነት የመጠየቅና ለአመልካች ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት። ስለሆነም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከላይ በዝርዝር የተቀመጡት የሕግ ድንጋጌዎች እና የአመልካችና የተጠሪ ከውል የመነጨ ተነፃፃሪ ግዳታና ኃላፉነት በአግባቡ ሣይገናዘብ ተጠሪ ከሁለት ጥቅል እቃ በኃላፉነት የሚጠየቅበት ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዳታና ኃላፉነት የለበትም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ 1- የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 2ዐ6ዐ8 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ይፃፍ።
2- ተጠሪ የሁለት ጥቅል ዔቃ ዋጋ ብር 3765ዐ /ሰላሣሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሣ ብር/ ከስ ካቀረበበት ነሐሴ 1ዐ ቀን 1986 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ለአመልካች ይክፈል ብለናል።
ለሚመለከተው ይፃፍ።
3- በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የራሣቸው ይቻለ። ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ታህሣሥ 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
የማየነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።