No summary available.
ኀዲር 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ሃርሴማ ሰልሞን - ጠበቃ አቶ አምባቸው ዮሐንስ ቀረቡ።
መልስ ሰጪ፡- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ - ነገረ ፈጅ አቶ ግርማ ገ/ፃዱቅ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር መዝገብ ላቀርብ የቻለው የግራ ቀኙን ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ በኮ/መ/ቁ. 56916 ሐምል 27 ቀን 1999 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ዲኝነት ተገቢውን የሕግ ትርጉም ያልተከተለ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት በቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ነው።
ጉዲዩም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው።
የአሁን መልስ ሰጭ ከሣሽ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ በመሆን በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከራክረዋል። ከሣሽ ተከሣሽን አስተምሯል። ተከሣሽም ከትምህርት ተመልሰው ከሣሽን ለማገልገል ግዳታ ገብተዋል። የማያገለግለ ቢሆን ለማስተማር ተብል የወጣውን ወጭ ብር 29ዐ,961 /ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አንድ ብር/ ለመክፈል ተዋውለዋል። ስለሆነም እንደውለ ለአራት ዓመት እንዱያገለግለ ወይም ገንዘቡን እንዱከፍለ ይወስንልን የሚል ክስ ቀርቧል።
ተከሳሽም ለዚሁ ክስ የሰጡት መልስ ወጭውን የሸፈነው የኔዘርላንድ ፋልውሺፕ ፕሮግራም ነው፤ ግዳታውም ወደ አገራቸው ተመልሰው እንዱያገለግለ እንጂ በከሣሽ ተቋም ለማገልገል አይደለም፤ እንደገቡት ግዳታም ወደ አገራቸው ተመልሰው በማገልገል ላይ ናቸው፤ የቀረበውም ውል በመካከላቸው ያለውን ትክክለኛ መብትና ግዳታ አያሳይም፤ ግልጽ ነፃነትን የሚያሰናክል ስለሆነ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
የግራ ቀኙን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብል ያየው ፍ/ቤትም በመ/ቁ. ዐ3727 ግንቦት ዐ2 ቀን 1999 ዓ.ም.
በዋለው ችልት በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል ቀርቧል፤ የትምህርት ደረጃቸውን እንዱያሻሽለ የአንድ ዓመት ዔረፍት ተሰጥቷል፤ የትምህርት ዔድለም የተሰጠው ባገኙት ተጨማሪ ችልታ መሰረት እንዱያለግለ ነው፤ ሲመለሱም ለአራት ዓመት ተኩል ለማገልገል ተዋውለዋል፤ ሰኔ 23 ቀን 1995 ዓ.ም. የተፃፈላቸው ደብዲቤ የትምህርት ዔድለ የተገኘው በዩኒቨርሲቲው እንጂ በግላቸው አለመሆኑን ያሳያል፤ በመሆኑም እንደግዳታቸው ካላገለገለ ከሣሽ ወይም 3ኛው ወገን የከፈለለትን ገንዘብ ለአሰሪው መክፈል እንደሚገባው በውለ ላይ ስለተመለከተ እና መብትና ግዳታው በግልጽ ስለተጠቀሰ በገቡት ግዳታ መሰረት ያገልግለ ወይም ገንዘቡን ብር 29ዐ,961.00 ይክፈለ ሲል ወስኗል።
በአሁን አመልካች ቅሬታ አቅራቢነት የይግባኝ ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ጉድለት አላገኘሁበትም በማለት በመልስ ሰጭነት የተሰየመውን ሳይጠራ መዝገቡን ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከላይ ባጭሩ በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች የተሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ ሉታረም ይገባል የሚለውን መሰረት በማድረግ ነው።
የቅሬታው ፍሬ ቃልም፡የትምህርት ዔድለ የተገኘው በግል በመፃፃፍ ሆኖ እያለ ይህ አልታየልኝም፤ ወጭውንም የሸፈነው የትምህርት ዔድለን የሰጠኝ ድርጅት ነው፤ ስለዚህ የአሁን መልስ ሰጭ በጉዲዩ አመልካች ላይ ክስ የማቅረብ መብት የለውም፤
ትምህርቱን የተማርኩት ከሦስትኛው ወገን ጋር ባደረኩት ስምምነት መሰረት ነው፤ ስምምነቱም ወደ አገር ተመላሼ ለማገልግል ነው፤ ውለን የፈረምኩትም ካልፈረምሽ የዔረፍት ፍቃደ አይሰጥሽም የድጋፍ ደብዲቤም አንጽፍም ስላለኝና አዘጋጅተው በማቅረባቸው እንቅፊት እንዲይፈጠር በመስጋት ነው፤ በግል ያገኘሁት ስለመሆኑ ወጭውንም ሦስተኛው ወገን ስለመሸፈኑ ያስባገኝም ግዳታ ምን እንደሆነ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቀርባለሁ፤ እንደውለ ይፈፀም እንኳ ቢባል የግል ነፃነቴን ይነካል፤ ለትምህርት ምን ያህል ገንዘብ እንደወጣ እንኳን ሳይረጋገጥ የተሰጠ ውሣኔ ስለሆነ ሉሻር ይገባዋል የሚል ነው።
የአሁን መልስ ሰጭም የበኩለን ክርክር አቅርቧል። ይዘቱም በግላ የተገኘ የትምህርት ዔድል ነው የተባለው ሀሰት ነው፤ በ1995 ዓ.ም. የኔዘርላንድስ መንግሥት በሰጠው ነፃ የትምህርት ዔድል ዩኒቨርሲቲው ተጠቃሚ እንዱሆን ከትምህርት ሚ/ር በተፃፈ ደብዲቤ መነሻ እንዱወዲደሩ ተደርጎ ያገኙት ለመሆኑ፣ የትምህርት ዔድለ በዩኒቨርሲቲው ኮታ ለመሆኑ፣ ትምህርቱን እንዱማሩ ስፖንሰር የሆነው መልስ ሰጭ ለመሆኑ በማስረጃው ከመልሱ ጋራ አያይዘናል፤ ውለን የፈፀሙት በገዛ ፈቃዲቸው እንጂ መገደድ ስላልተፈፀመባቸው በግራ ቀኛችን መካከል የተደረገው ውል እንደ ሕግ ያገለግላል፤ ሦስተኛ ወገን ሳይሆን ደመወዝ ከፍልና ስፖንሰር ሆኖ ያስተማረ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ክስ ለማቅረብ መብት አለው የሚለ ናቸው።
No topics extracted.
አመልካችም በመልስ መልሳቸው ላይ ክርክራቸውን በማጠናከር አቅርበዋል።
በሰበር ደረጃም ሆነ በሥር ፍ/ቤቶች ሁለቱም ወገኖች ያቀረቡት ክርክር ከላይ ባጭር ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች በሥር ፍ/ቤትም ሆነ በዚህ የሰበር ችልት የሚያቀርቡት የትምህርት ዔድለን ያገኘሁት በግል ባደረግሁት መፃፃፍ ነው፤ በዚህም የተነሣ ወጭውን የሸፈነው ሦስተኛ ወገን ነው፤ የግዳታውም ዓይነት ወደ አገሬ ተመልሼ እንዲገለግል የሚገልጽ ሲሆን ወደ አገሬም ተመልሼ እያገለገልኩ ስለምገኝ የሚጠበቅብኝ ግዳታ የለም የሚለው የፍሬ ነገር ክርክር ይገኝበታል። ይሁን እንጂ በዚህ አኳኋን የቀረበውን የማስተባበያ የፍሬ ነገር ክርክር ተከራካሪው ወገን በማስረጃ አስደግፍ ማስረዲት ይኖርበታል። የመዝገቡን ግልባጭ እንዲየነው ይህንኑ ክርክር ሉደግፍ የሚችል ማስረጃ አልቀረበም። በመሆኑም አንድ ተከራካሪ ወገን በማስረጃ ያልተደገፈ የፍሬ ነገር ክርክር ስለገለፀ ብቻ የቀረበበትን ክስ አስተባብሎል ለማለት የሚቻል አይደለም። በዚህ ረገድ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለውሣኔው መሰረት ያደረገው አመልካችና መልስ ሰጭ ያደረጉትን የጽሁፍ ስምምነት ስለመሆኑ የውሣኔው ግልባጭ ያስረዲል። ይህም የውል ስምምነት ግልባጭ ቀርቦ ከዚህ የሰበር መዝገብ ጋር በመያያዙ ተመልክተነዋል።
አመልካች ይኸው የጽሁፍ ስምምነት ሉያስገድደኝ አይችልም የሚል ክርክር ሲያቀርቡ ለዚህ ክርክር በምክንያትነት የገለጹት ውለ በመካከላቸው ያለውን ትክክለኛ መብትና ግዳታ አያሳይም የሚለውንና ካልፈረምሽ የዔረፍት ፈቃድ አይሰጥሽም የድጋፍ ደብዲቤም አንጽፍም ስላለኝ እንቅፊት እንዲይፈጠር በመስጋት ነው የሚለውን በማተት ነው።
ሆኖም የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ ማየት እንደሚቻለው በይዘቱ የተዋዋይ ወገኖችን መብትና ግዳታ ለይቶ ያስቀመጠ፣ መብትና ግዳታውም በግልጽና በተነፃፃሪ ሁኔታ የሰፈረበት በመሆኑ በመካከላቸው ያለውን ትክክለኛ መብትና ግዳታ አያሳይም የሚለው ክርክር የሰነደን ይዘት ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። በውለ ላይ የተመለከተውን ፊርማ ላስቀምጥ የቻልኩት በነፃ ፍቃድ አይደለም የሚለውም ክርክር ቀርቧል። እንደተባለውም በሕግ ፉት ሉፀና የሚችል ውል ለመያዝ መሟላት ከሚገባቸው ቋሚ ሁኔታዎች አንደ ጉድለት የላለበት የፈቃድ ሁኔታ መኖር ነው። ይኸው ፈቃድ በስህተት በኃይል ወይም በተንኮል የተገኘ እንደሆነ ውለ እንደማይፀና በሕግ ተመልክቷል። አመልካች ከእነዚህ በአንደ የተነሣ የተሰጠ ፈቃድ ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር የለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ የጠቀሱት የፍሬ ነገር ክርክር ምናልባትም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 171ዐ የተጠቀሰውን /መጉዲት/ የሚለውን ያሟላል እንዲይባል አመልካች ይህንኑ ክርክር በአባባል ደረጃ ጠቀሱት እንጂ ካልፈረሙ የዔረፍት ፈቃድ እንደማይሰጣቸው፣ የድጋፍ ደብዲቤም እንደማይፃፍላቸውና በአጠቃላይ እንቅፊት እንዲይፈጠርባቸው በመስጋት የችግራቸው ሁኔታ ገፊፍቷቸው ውለን እንዱፈፀሙ በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ በሕግ ምክንያቶች የሚያዝ አይደለም።
በአኳያው ግራ ቀኙ ነሐሴ ዐ2 ቀን 1995 ዓ.ም. ያደረጉት ውል አመልካች በውጪ ለመማር የተሰጣቸው ዔድል በተባለው ጊዜ እና የተባለውን የትምህርት ዘርፍ ተከታትለው ተመልሰው በመልስ ሰጭ ተቋም ለምን ያሕል ጊዜ ማገልገል እንዲለባቸው፣ ይህን ባያደርጉ በምትኩ መልስ ሰጭ አሰሪው ወይም ሦስተኛ ወገን የከፈለለትን ሙለ ገንዘብ ብር 29ዐ,961 /ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አንድ ብር/ አመልካች ለመልስ ሰጭ የመክፈል ግዳታ እንዲለባቸው እና በተመለሱም ጊዜ ያላቸው ተነፃፃሪ መብት ምን እንደሆነ በግልጽ እና በማያሻማ አኳኋን ተገልጿል።
ይህ ውል በይዘቱ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1678/ለ/ አንፃር ሲታይም የውለን ጽናት ሉያስቀር የሚችል አንዲችም ምክንያት የለበትም። በሕግ ፉት የፀና ውል ያደረጉ ወገኖችም እንደ ውለ እንዱፈጽሙ ውለ ሕጋዊ ውጤት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው። እንደ ውለ ያልተፈፀመለት ወገን እንደ ውለ እንዱፈፀምለት ከውል ያገኘውን መብት ለማስፈፀም መብት ያለው በመሆኑ የመልስ ሰጭ የክስ አቤቱታ አግባብነት ያለው ነው። ይሁን እንጂ እንደ ውለ እንዱፈፀምለት የሚጠይቀው ወገን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1776 እንደተመለከተው ይፈፀም የሚባለው ግዳታ የፈፃሚውን የግል ነፃነት የሚነካ ከሆነ ያለፍላጎቱ ተገድ ሉፈፀም አይገባም። በዚህ ጉዲይ አመልካች እንደገቡት ግዳታ እንደሙያቸው ለመልስ ሰጪ እንዱያገለግለ የሚገደደት የፈቀደ እንደሆነ ብቻ ነው። በፈቃዲቸው ለተባለው ጊዜ ያሕል ለማገልገል ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን በአማራጭ ሉከፈል የሚገባውን የገንዘብ ክፍያ ሉፈጽሙ ይገባል።
ይህንን በሚመለከት ምንም እንኳን ለትምህርቱ ሲባል ሦስተኛ ወገን የከፈለለትን ሙለ ገንዘብ ብር 29ዐ,961.00 /ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አንድ ብር/ በሚል የገንዘቡ መጠን ተለይቶ የተቀመጠ ቢሆንም ይኸው ገንዘብ ለትምህርት የተከፈለውን ማናቸውንም ወጭ ለመሸፈን ሲባል የተደረገ መሆን ይኖርበታል። ለትምህርት ተብል የተከፈለው ወጭ ትምህርቱን ጀምረው ከማጠናቀቃቸው በፉት የታወቀ ወይም ሉታወቅ የሚችል ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት የታወቀ አይደለም። እንደ ውለ አመልካች ለማገልገል ካልፈቀደ እንደ ውለ ምትክ ግዳታቸውን በገንዘብ ሉከፍለ፣ እርሳቸውን ለማስተማር ተብል በአሰሪውም ሆነ በሦስተኛው ወገን በእርግጥም ያወጣውን ማናቸውም ወጭ ላሆን ይገባል። ይህንን በሚመለከት መልስ ሰጭ በውለ ላይ የተጠቀሰውን ብር 29ዐ,961.00 የሚለውን በመጥቀስ ለክሱ መሰረት አደረገ እንጂ አመልካችን ለማስተማር ሲባል በመልስ ሰጭም ሆነ በሦስተኛው ወገን በትክክል የወጣውን ወጭ በማስረጃ አላረጋገጠም። ስለሆነም የአሁን አመልካች ሉከፍለ የሚገባውን የትምህርት፣ የትራንስፖርት እና ደመወዝ ሳይከፍለ ለማገልገል ከፈለጉ የሥር ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ እንደገለፀው እንዱያገለግለ ይህንን ለመፈፀም ካልፈለጉ ግን አሰሪው ወይም ሦስተኛው ወገን በደመወዝም ሆነ በትራንስፖርት ወይም ማናቸውንም ለትምህርቱ ተብል የተከፈለውን ወጭ ዘርዝሮ ሲያቀርብና በማስረጃም አስደግፍ ሲያስረዲ የታወቀውን እውነተኛ ወጭ የአሁን መልስ ሰጭ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1776 መሰረት የመክፈል ግዳታ አለባቸው በማለት ፈርደናል።
ው ሣ ኔ