No summary available.
ህዲር 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሰላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ሰናይት ገነሜ ገንታ - ሣሙኤል ደመቀ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የቤት ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረችው አመልካች ናት። ተጠሪዎችን የከሰሰችውም ይቻላል በተሰኘ ማህበር በሸንሻኖ ቁጥር 13 የሚታወቅ 175 ካሬ ሜትር ግቢ ያለው ጅምር ቤት ሸጠውልኝ ውለ በተደረገበት ዔለት ቀብድ ከፍያለሁ ቀሪውን ደግሞ በማህበሩ በአባልነት ሲያስመዘግቡኝ፣ እዲና እገዲ እንደላለበት ሲያረጋግጡ፣ ካርታውን ከአስፈላጊው ድክመንቶች ጋር ሲያስረክቡኝ፣ ጉዲዩ ለማህበራት ማደራጃና ማስፊፉያ ቢሮ ሲቀርብ እንደዚሁም የሽያጭ ውለ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሲፈፀም ልከፍል ተስማምተናል። ሆኖም ተጠሪዎች እንደውላቸው አልፈፀሙም። ይልቁንም የጀመርኩትን ግንባታ እንዲላካሂድ ችግር ፈጥረውብኛል። ሰለዚህ በውላቸው መሰረት እንዱፈጽሙ ይገደደልኝ በውለ የተመለከተው የመቀጫ ገንዘብ እንዱከፍለም ይወሰንባቸው በማለት ነው። ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አቅርበውም ውለን ለመተግበር ያልቻለችው አመልካች ናት በማለት መቀጫ ትከፍላቸው ዘንድ እንዱወሰን ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ክሱን ከሰማ በኋላ በሁለቱ መካከል ተደረገ የተባለው የሽያጭ ውል የሕጉን መስፈርት አያሟላም የሚል ምክንያት በመስጠት በሁለቱም ወገኖች የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል ክርክር ያስነሣው ጉዲይ የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ውል የሚመለከት ነው ወይስ በማህበርተኝነት የመተካት መብትን የሚመለከት? የሚለውን ነጥብ ለማጣራት ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከስር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር በዝርዝር ተመልክተናል። ከዚህም ግራ ቀኝ ወገኖች የቤት ሽያጭ ውል አድርገናል ብለው ያምኑ እንደነበር፤ በውለ አፈፃፀም ረገድ ችግር ካጋጠማቸው በኋላ ግን ወደ መካሰስ እንዲመሩ፣ በመጨረሻም በተለይ ተጠሪዎች በሕጉ መሰረት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የለም ወደሚለው በማዘንበል እንደተከራከሩ ለመገንዘብ ችለናል። ክሱን ያስተናገደው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመጨረሻ ውሣኔ የሰጠው በግራ ቀኝ ወገኖች መካከል ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1723 የተመለከተውን መስፈርት አያሟላም በረቂቅ ደረጃ የቀረ ነው በማለት ነው።
በእርግጥ የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 የማይንቀሣቀሱ ንብረቶችን የባለቤትነት መብት ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውልች ማሟላት ስለሚገባቸው መስፈርቶች ደንግጎአል። ከዚህ የተነሣም እንደውለ ይፈፀም ዘንድ ውሣኔ እንዱሰጥ የተጠየቀው ፍ/ቤት የውለን ሕጋዊነት በቅድሚያ ለማረጋገጥ ክርክሩ ከፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 አንፃር ማየቱ ተገቢ ይሆናል። በልላ በኩል ግን ውል ነው በሚል የቀረበለት ሰነድ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 እንደተመለከተው በእርግጥም የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው ወይስ ላላ የሚለውን ነጥብም መመርመሩ ተገቢ የሚሆንበት አጋጣሚ እንደሚኖር ማሰቡ ተገቢ ይሆናል። በያዝነው ጉዲይ እንደሚታየው ተጠሪዎች በእነሱ ስም ብቻ ካርታና የባለቤትነት መታወቂያ ተለይቶ የተሰጠው ቤት እንዲላቸው ክርክሩ አያመለክትም። ይልቁንም ጅምር ነው የተባለው ቤት የሚገኘው ይቻላል በተሰኘ የቤት ሥራ ማህበር አጠቃላይ ይዞታ ስር እንደሆነ ነው መዝገቡ የሚያመለክተው ተጠሪዎች የዚህ ማህበር አባላት እንደመሆናቸው መብት እንዲላቸውም የሚያከራክር አይደለም። አከራካሪ የሚሆነው ወይም ልዩ ትኩረት በመስጠት ላታይ የሚገባው ተጠሪዎች በማህበሩ ላይ ያላቸውን መብት ለሦስተኛ ወገን ሉያስተላልፈ ይችላለ ወይ?
የሚችለ ከሆነስ ስርዓቱ ምንድነው? የሚለው ነው።
ሰዎች በመደራጀት የሕብረት ስራ ማህበር ማቋቋም እና በዚህም በጋራ የመጠቀሙ ሁኔታ በሕግ እውቅና የተሰጠው ነው፣ በዚህ መልክ የሚቋቋሙት ማህበራት በሕግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው መብትና ግዳታቸውም በሕግ የተወሰነ ነው። የህብረት ስራ ማህበራትን በተመለከተ በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ያለው የህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/91 ነው። ይህ አዋጅ ስለማህበራት ዓላማ፣ ስለማህበራት አመሰራረት፣ ስለሚመሩባቸው መርሆዎች፣ ስለሕግ ሰውነትና ኃላፉነት፣ ስለመተዲደሪያ ደንብ፣ ወዘተ በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን አካቶአል። በዚህ መዝገብ ለተያዘው ጉዲይ አወሳሰን ቀጥተኛ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንደ የአዋጁ አንቀጽ 19 ሲሆን ይህም በአንድ በኩል የማህበር አባል ዔጣውን ወይም ጥቅሙን ለማስተላለፍ እንደሚችል በመርህ ደረጃ ሲደነግግ፤ በልላ በኩል ደግሞ የማስተላለፈ ሁኔታም የራሱ የሆነ የተለየ ስርዓት እንዲለው ያመለክታል። የማህበሩ አባል ዔጣውን ወይም ጥቅሙን ለማስተላለፍ ቢፈልግ ከማህበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል። የሚለው አንደ ሁኔታ እንደሆነ በንኡስ አንቀጽ 1/ለ/ ተመልክቶአል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በማህበር ተደራጅቶ የተገኘውን መብት የማስተላለፉያ ስርዓቱ በግል ከተገኘ መብት የተለየ መሆኑን ነው። መብት የሚተላለፍለት ወገንም በአስተላላፉው መብት መጠቀም የሚችለው በመተካት የማህበሩ አባል መሆን ከቻለ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 ከተመለከተው የማይንቀሣቀስ ንብረት መብት ማስተላለፉያ ስርዓት የተለየ ነው። በመሆኑም በማህበር በመደራጀት የተሰራውን ቤት ሸያጭ ውል በፍ/ብ/ሕግ ቁ/ 1723 ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር አያይዞ ማየቱ ትክክል አይሆንም በተያዘው ጉዲይም ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የተዋዋለት በማህበሩ ያላቸውን መብት ለማስተላለፍ በመሆኑ ክርክሩ መታየት ያለበት ከአዋጅ ቁ.
147/91 አንፃር ነው። ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች ውለ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1723 መሰረት የተደረገ አይደለም ከሚል በመነሣት የሰጡት ውሣኔ ሕጉን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.