No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3674ዐ ህዲር 23 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሰላሴ አልማው ወላ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ ዓብደል ዋሀብ ኢብራሂም - ጠ/ ገ/ማርያም ገ/እግዚአብሕር ተጠሪ፡-
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
የአሁኑ ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ከሣሾች ሲሆኑ አመልካች ተከሣሽ ነበሩ። ከሣሾች ባቀረቡት ክስም የከሣሾች አባት በከፍተኛ 24 ቀበላ 13 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 2ዐ11 የሆነውን ቤት በ3/13/198ዐ ዓ.ም በተፃፈ የወለድ አገድ ውል በብር 29,ዐዐዐ (ሃያ ዘጠኝ ሺህ) ለ1ዐ አመት ለአመልካች/ተከሣሽ ያስያዙት ሲሆን የከሣሾች አባት በ21/6/89 ዓ.ም ከሞቱ በኋላ አመልካች ገንዘባቸውን ወስደው ቤቱን እንዱያስረክቡን ብንጠይቃው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ገንዘቡን ተቀብለው ቤቱን ያስረክቡን፣ ማስጠንቀቂያ ከደረሣቸው ጊዜ ጀምሮ የቤቱን ኪራይ እንዱከፍለ በማለት ጠይቀዋል።
የሥር ተከሣሽ የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ፤ በ3/13/198ዐ የተደገውን ውል መሰረት በማድረግ የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል፣ 8 ዓመት ያለፈ የቤት ኪራይ ጥያቄም ቢሆን በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው። ይህ ቢታለፍ ግን በ3/13/198ዐ የወለድ አገድ ውል ተደርጎ ቤቱንና ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድች ተረክቤአለሁ። ከዚህ በኋላም ለግለሰብ ቤት እንዱሸጥ ስለፈቀደ የተጠሪዎች ወላጅ አባትና ባለቤታቸው ነሐሴ ዐ6/1988 በተፃፈ ውል በአ.አ ከተማ መስተዲድር የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ተፈራርመን የቤት ሽያጭ ውል ፈጽመናል፣ ስለሆነም የወለድ አገድ ውለ በሽያጭ ውል ስለተተካ ሉከሱኝ አይችለም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የሽያጭ ውለ በ6/12/88 መደረጉን ቢገልፁም የተመዘገበው ግን 17/ዐ3/1991 ነው። ውለ በተመዘገበበት ቀን ደግሞ የከሣሾች አውራሽ በህይወት አልነበሩም በመሆኑም አመልካች ባቀረቡት የሽያጭ ውል ላይ የተጠሪዎች አባት ሉፈርሙ የማይችለ በመሆኑ የሽያጭ ውል ፈርመናል የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም። የግራ ቀኙ ግንኙነት በ3/13/8ዐ ዓ.ም የተደረገው የመያዣ ውል ነው በማለት ተጠሪዎች የሚፈለግባቸውን ብር 29,ዐዐዐ(ሃያ ዘጠኝ ሺህ) ለአመልካች ሲከፍለ አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ፤ የሽያጭ ውል የተፃፈው በ6/12/1988 ሲሆን የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርቦ በኃላፉ የተመራበትና የተፈረመበት የተዋዋይ ወገኖች የምስክሮች ፊርማና መታወቂያ የተረጋገጠው በዚሁ ቀን ቢሆንም የዔዲና እገዲ እስከሚሰራ የፍርማሉቲ ስርዓቱና ክፍያ መፈፀሚያው ተቋርጦ እንደገና ማጣራት ተደርጎ በ1991 ዓ.ም ተረጋግጦ ወጭ ሆኗል ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ውል በፉቱ ሲደረግ አረጋጋጭ እንጂ ውል መዝጋቢ አካል ባለመሆኑና ውል በፉቱ ቀረቡ ጠበቃ መኯንን አምቦ የተደረገው በ6/12/1988 ዓ.ም በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሯል። አመልካች ቤቱን በሕጋዊ ውል የያዙት በመሆኑ ሉያስረክቡ አይገባም፤ በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች ደግሞ በዚህ ውሣኔ ላይ ቅር ተሰኝተው ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔን በመሻር የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። ይህ ችልትም የሽያጭ ውል የተደረገው መቼ ነው የሚለውን ጉዲይ ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረግ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታውን የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው ተጠሪዎች በአመልካችና በተጠሪዎች አውራሽ መሃከል ያለው የወለድ አገድ ውል ነው ሲለ አመልካች ደግሞ ከወለድ አገድ ውለ በኋላ የቤት ሽያጭ ውል ተደርጓል በማለት ተከራክረዋል ተጠሪዎች የሽያጩ ውል ተደረገ የተባለው አውራሻችን ከሞቱ በኋላ በመሆኑ የሽያጭ ውል የለም ሲለ አስተባብለዋል። ችልቱም የሽያጭ ውለ መቼ ነው የተደረገው የሚለውን አግባብ ካለው ሕግ ጋር አናዝቦ መርምሯል።
አንድ ውል ፍፁም ነው የሚባለው ተዋዋዮቹ በተስማማ አኳኋን መፍቀዲቸውን ገልፀው ሲገኙ መሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 168ዐ/1/ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም ውል አቅራቢው በቃልም ሆነ በጽሁፍ በማያጠራጥር ሁኔታ ግዳታ ለመግባት መፍቀደን ካሣወቀና ውል ተቀባዩም በተመሣሣይ መልኩ የውል ድርድሩን መቀበለን ካሣወቀ በሁለቱ መሐከል ስምምነት መደረጉን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1681 መረዲት ይቻላል በእርግጥ ጉድለት የላለበት ፈቃድ ከመስጠት በተጨማሪ ሕጉ ልዩ የሆነ የሚጠበቅ አፃፃፍ ፍርም እንዱኖር ካስገደደ ይኸው የአፃፃፍ ሥርዓት መሟላቱ ለውለ ሕጋዊነት ላላው መሰረታዊ ነገር ነው። ስለሆነም ተዋዋዮች ነፃ ፈቃዲቸውን ከመስጠታቸው በተጨማሪ ውለን ሕጉ በሚያዘው የአፃፃፍ ሥርዓት ሉመሰርቱ ይገባል። ለምሣላ የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ውለ በጽሁፍ ከመደረጉ በተጨማሪ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ወይም በዲኛ ፉት መደረግ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723/1/ ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም ሕጋዊ ውጤት እንዱኖረው የቤት ሽያጭ ውል መደረግ ያለበት በጽሐፍ ብቻ ሣይሆን ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ወይም በዲኛ ፉት ጭምር ነው። ውለ በአዋዋይ ወይም በዲኛ ፉት እንዱደረግ ያስፈለገበት ዋነኛ አላማም የተዋዋዮቹ ማንነት ያላቸው ችልታና መብት ነፃ ፈቃዲቸውን መስጠታቸውን ውለ የተደረገበትን ቀንም ለማረጋገጥ ነው።
No topics extracted.
በተያዘው ጉዲይ የተጠሪዎች አውራሽ እና አመልካች ውላቸውን በ6/12/1988 ዓ.ም በተፃፈ ሰነድ አዘጋጅተው ሁለቱም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት ቀርበው መፈረማቸው የምስክሮቹም ማንነትና ፊርማ በዚሁ ውለ በተፃፈበት ቀን መረጋገጡን ከክርክሩ ሂደት ተረድተናል። በመሆኑም የተጠሪ አውራሽና አመልካች የቤት ሽያጭ ውለን ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያደረጉት በ6/12/1988 መሆኑን ተገንዝበናል። በእርግጥ ግራ ቀኙ ውለን በ6/12/1988 የፈፀሙ ቢሆንም ቤቱን የሚመለከቱ ዔዲና እገዲ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውለ ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የþሮቶኯል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ማለፈን ተመልክተናል። ነገር ግን አንዲንድ አስተዲደራዊ ጉዲዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውለ ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የþሮቶኯል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውለ እንዲልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም።
በልላ በኩል ሰነደን የፃፈው ወይም የተቀበለው የመንግሥት መ/ቤት ከሆነ ሰነደ የተፃፈበት እርግጠኛ ቀን ነው የሚባለው የፃፈበት ወይም የተቀበለበት ቀን በመሆኑ /የፍ/ብ/ህ/ቁ.2ዐ15/ሀ/”ን” ይመለከቷል/ የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የሽያጩን ውል ያፈራረመበትና ሰነደን የተቀበለበት