No summary available.
ኀዲር 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ አምዳ - ጠበቃ አስናቀ ከፊለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥላሁን አርምዳ ከጠበቃ ሰብስቤ ባልቻ ጋር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ተጠሪ የወንድሜ ልጅ በመሆኑ ከባለቤቴ ሞት በኋላ አብሮኝ እንዱኖር በወረዲ 23 ቀበላ 1ዐ በሚገኘው ቁጥር 19ዐ በሆነው ቤት አስጠግቼው ሲኖር የግል ሀብቴን ለመውሰድና ለመጠቀም አስቦ ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም አሞኝ በነበረበት ወቅት እንደማላነብና መሐይም መሆኔን በማወቅ የስጦታ ውል አዘጋጅቶ አስፈርሞኛል። ከዚያም በጥር ወር 1991 ዓ.ም ቤተክርስትያን ሄጄ ስመለስ ወደ ቤቴ እንዲልገባ ከልክልኛል ስለሆነም ነሐሴ 9/1984 ዓ.ም የተደረገው የስጦታ ውል ፈራሽ ነው ተብል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪም ቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና ሙለ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱት ክርክርም በዚህ ጉዲይ አስቀድመው በከተማ ነክ ፍ/ቤት ክስ አቅርበው ተቀባይነት ሣያገኝ የቀረ ሲሆን በዚያው ጉዲይ በድጋሚ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም። የስጦታ ውለ ይሻርልኝ ተብል የቀረበው አቤቱታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 181ዐ መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚለ ናቸው። በፍሬ ጉዲይ ክርክር ረገድም የስጦታ ውለ በሕግ አግባብነትና በአመልካች ሙለ ፈቃደኛነት እንደተደረገ ጠቅሰው ሉሻር ይገባል ተብል የቀረበ አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ አስቀድሞ ጉዲዩ ውሣኔ አግኝቷል በማለት ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ አስቀድሞ ለከተማ ነክ ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረው አቤቱታ ሁከት ይወገድልኝ በማለት እንጂ የስጦታ ውለ ይፍረስልኝ በማለት ስላልሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 5 መሰረት መቃወሚያው ተቀባይነት የለውም ብሎል።
ይርጋን አስመልክቶ ተጠሪ ያቀረቡትን መቃወሚያ በተመለከተም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 181ዐ መሰረት የይርጋ መቃወሚያ ማቅረብ የሚቻለው ውለ ሲመሰረት የችልታና የፈቃድ ጉድለት አለበት በሚባልበት ጊዜ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ውለ እንዱፈርስ የጠየቁት ችልታና ፈቃድ መሰረት አድርገው ሣይሆን መሐይም ነኝ በማለት ስለሆነ የዚህ ዓይነቱ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 181ዐ ሥር ስለማይሸፈን አቤቱታው በይርጋ ቀሪ አይሆንም በማለት ሣይቀበለው ቀርቷል።
የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን መርምሮ የማይንቀሣቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረግበት ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 መሰረት ግልጽ ኑዛዜ በሚደረግበት ሥርዓት ላደረግ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443 ላይ የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን በማስረጃነት የቀረበው የስጦታ ውል ሲታይ ግን ስጦታ አድራጊውና ምስክሮች ባለበት ከተነበበ በኋላ የተፈረመ ስለመሆኑ ስለማያስረዲ ፈራሽ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለተውም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ ይግባኝ ባይ የስጦታ ውለ እንዱፈረስ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1810 ላይ የተመለከተው የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤት በይርጋ ቀሪ አልሆነም ማለቱ ተገቢነት በላለው ሁኔታ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በአመልካች በኩል የቀረበለትን ይግባኝ መርምሮ ግራቀኙን በማከራከር የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙ አከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረቡት የስጦታ ውል ይፍረስልኝ አቤቱታ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይርጋ ቀሪ ሆኗል መባለ በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከዚሁ ጭብጥ አኳያም አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከፍ ብል እንደተጠቀሰው አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ያቀረቡት ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም ታምሜ በነበረበትና መሐይም መሆኔንም በማወቅ የመኖሪያ ቤት የስጦታ ውል ያስፈረመኝ ስለሆነ ይሄው የስጦታ ውል ፈራሽ ነው ይባልልኝ በማለት ነው።
ስጦታ እንዱቀነስ ወይም እንዱሻር የሚቀርብ አቤቱታ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ለዳኞች ካልቀረበ ዋጋ እንደላለው / በይርጋ እንደሚቋረጥ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441/1/ ላይ ተደንግጓል።
No topics extracted.
አመልካች የስጦታ ውለ ተፈርሟል የሚለት ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም ሲሆን ይሄው የስጦታ ውል ፈራሽ ነው ይባልልኝ በማለት ክስ ያቀረቡት ደግሞ ሰኔ 1 ቀን 1993 ዓ.ም ዘጠኝ ዓመት ሉሞላው ጥቂት ወራት ሲቀር ነው።
አመልካች ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም የተፈረመው ሰነድ የስጦታ ውል መሆኑን ያወቅሁት የካቲት 8 ቀን 1991 ዓ.ም ለሚመለከታቸው ክፍልች አቤቱታ ሣቀርብ ነው ያለትን በመውሰድ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እንኳ ክስ እስካልቀረቡበት ሰኔ 1 ቀን 1993 ዓ.ም ያለው ሲታሰብም 2 ዓመት እንዲለፈው መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩልም የፋዳራል ከፍ/ቤት አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል ያለው በፍ/ብ/ቁ. 181ዐ ላይ እንደተመለከተው በ2 ዓመት ጊዜ አልቀረበም በማለት ነው።
በግራ ቀኙ መካከል ተደርጓል የተባለው የስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ ግንኙነት በተለይ የሚገዛው በፍ/ብሕር ሕጉ ስጦታን አስመልክቶ በተደነገጉት ድንጋጌች መሰረት ሲሆን ወደ ጠቅላላ የውልች ሕግ ድንጋጌዎች መሄድ የሚቻለው በልዩ ሕግ ላይ ተመስርቶ ለጉዲዩ ዔልባት ለመስጠት ካልተቻለ ነው። በዚሁ መሰረትም የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት ጉዲዩን ከስጦታ ውል ድንጋጌዎች አኳያ መርምሮ ለይርጋ ክርክሩ እልባት መስጠት ሲገባው ስለ ውልች በጠቅላላው በሚለው ምዔራፍ ሥር የተደነገገውን የይርጋ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሣኔ መስጠቱ ከሕግ አተረጓጎም መርህ አንፃር ተገቢነት የላለው ከመሆኑም በላይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.181ዐ ላይ የተመለከተውና ውለ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ ከ2 ዓመት በኋላ የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ አይቀርብም ተብል የተመለከተውም ውለ በችልታና በፈቃድ ረገድ ጉድለት በሚኖረው ጊዜ ነው። መሐይምነትን ወይንም ዓይነስውርነትን አስመልክቶ የሚቀርብ የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ከውለ የአፃፃፍ ሥርዓት /ፍርም/ ጋር ተያይዞ እንደሚነሣ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1719 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል እንደመሆኑ መጠን የዚህ ዓይነቱ ጥያቄም በይርጋ የሚታገደው በቁጥር 1845 እንጂ በቁጥር 181ዐ ላይ እንደተደነገገው ስላልሆነ በዚህ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ለድንጋጌው የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት መሆኑን ተገንዝበናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 64 በ17/6/95 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ተሽሯል።
2/ የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 18957 ጥር 23 ቀን 1998 ዓ.ም አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የሰጠው ውሣኔ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ሲሆን ከውጤት አኳያ የሚነቀፍ ስላልሆነ እንደዚሁም የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 23712 ጥር 29 ቀን 1999 ዓ.ም ይህንኑ ውሣኔ ማጽናቱ ከውጤት አኳያ በአግባቡ ስለሆነ አጽንተነዋል።
3/ አመልካች የስጦታ ውል ይፍረስልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441/1/ መሰረት በ2 ዓመት ጊዜ ስላልቀረቡ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ወስነናል።
4/ ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
5/ መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።