No summary available.
የሰ/መ/ቁ 3652ዐ ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ነገረ ፈጅ ሂሩት አስራት ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ይብራህ ግርማይ - ጠበቃ አቶ አበበ ኃይላ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 22 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ. 32556 ታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በመጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች በከሳሽነት በመቅረብ በሥር በተከሣሽነት የተከራከረው ተጠሪ ንጉሴ ግርማይ ላይ ባቀረበው ክስ የአሁን ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 16 ቀበላ 11 የቤት ቁ. 834 የሆነውን ቤት ጥር 1 ቀን 199ዐ ዓ.ም. በተፈረመ የኪራይ ውል በብር 175 /አንድ መቶ ሰባ አምስት ብር/ ተከራይቷል፤ ሆኖም ይህንን ቤት ከአከራዩ ፈቃድና ዔውቅና ውጭና የኪራይ ውለን በሚጥስ ሁኔታ ለንጉሴ ግርማይ አሳልፍ የሰጠ በመሆኑ የኪራይ ውለ ፈርሶ ቤቱን እንዱያስረክብ ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ በቤቱ ውስጥ የምኖረው እኔ ነኝ፤ ለአቶ ንጉሴ ግርማይ አሳልፋ አልሰጠሁም፤ የሚል ክርክርና ይህንን ያስረደልኛል የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች አቅርበዋል። የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረባቸውን ሁለት ምስክሮች ከሰማና በተከሳሽ በኩል የቀረበውን ማስረጃ ከመዘነ በኋላ የኪራይ ውለ ፈርሶ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክቡ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የኪራይ ውለ የሚቋረጠው /ይግባኝ ባይ/ ተጠሪ ቤቱን ለመኖሪያ ቤት ሣይሆን ለንግድ ቢጠቀምበት ነበር፤ ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የለውም በማለት ወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን ሽሯል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የለም በማለት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች በኪራይ ውለ አንቀጽ 6/2/ መሰረት ተጠሪ ቤቱን ራሱ ሉገለገልበት እንጂ ለላላ ሰው አሳልፍ ለማከራየት ወይም ለመስጠት እንደማይችል ተመልክቷል፤ ተጠሪ ቤቱን ለላላ ሰው አሳልፍ የሰጠ በመሆኑ በኪራይ ውለ አንቀጽ 11/3/ መሰረት ውለ ይቋረጣል፤ ይህ ሆኖ እያለ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለኪራይ ውለ አንቀፆች ያልሆነ ትርጉም በመስጠት መወሰኑና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኛችንን መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠው ከቀበላ የተፃፈለትን ማስረጃና የሁለት ምስክሮች ቃል ሰምቶ ነው፤ ማስረጃው ቀጥተኛ ማስረጃ ሣይሆን የሰሚ ሰሚ ማስረጃ ነው፤ የሰሚ ሰሚ ማስረጃ ተቀባይነት የላለው ማስረጃ ነው፤ በተቃራኒው እኔ በቤቱ ውስጥ እንደምኖር የቀበላ መታወቂያ ደብተርና ደብዲቤ በማቅረብ አስረድቻለሁ፤ ከዚህ በተጨማሪ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ለኪራይ ውለ አንቀጽ 6/1/ የሰጠው ትርጉም ተገቢነት ያለው ነው፤ ስለዚህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ምንም አይነት የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ተጠሪ የማስረጃ ተዓማኒነትና ተቀባይነትን አስመልክቶ ያቀረበው ክርክር ተገቢነት የላለው ነው፤
የውለን አተረጓጎም በተመለከተ ያቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት የለውም በማለት የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካችና ተጠሪ በሰበር ያደረጉት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ ላደረጉት የኪራይ ውል የሰጠው ትርጉም ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መጣራት ያለበት ሆኖ አግኝተዋል። ከላይ ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት ስለውል ድንጋጌዎች አተረጓጎም በፍትሐብሕር ሕግ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መመልከት ያስፈልጋል።
ከዚህ አንፃር ስንመዝነው የውል ድንጋጌዎች መተርጎም ያለባቸው በተዋዋዮቹ መካከል ሉኖር የሚገባውን ቅንነትና የመተማመን ግንኙነት መሰረት በማድረግና በጉዲዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ ሥርዓት በመከተል በቅን ልቦና መተርጎም ያለባቸው ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1732 የተደነገገ ሲሆን የውል ቃል የሚያሻማ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የተዋዋዮች ሃሣብ ምን እንደነበረ በመፈለግና መሰረት በማድረግ ሉተረጎም እንደሚገባ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1734 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። አመልካች የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው። አመልካች የተቋቋመው የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ አገልግልት ለመስጠት ነው። ከዚህ አንፃር የአመልካችን አገልግልት ያገኘና የኪራይ ውል የተዋዋለ ሰው ቤቱን በኪራይ ውለ ከተገለፀው አገልግልት ውጭ እየተገለገለበት ከተገኘ ውለ ፈራሽ እንደሚሆን ከኪራይ ውለ አንቀጽ 6 እና አንቀጽ 11/3/ ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
በመሆኑም ቤቱን እራሱ በመኖሪያ ቤትነት ለመገልገል ተስማምቶ የተከራየ ተከራይ በተከራይ አከራይነት ቤቱን ላላ ሰው ለመኖሪያ ቤትነት እንዱገለገልበት አከራይቶ ቢገኝ ወይም ከአከራይ ስምምነትና ፈቃድ ውጭ በልላ በማናቸውም መንገድ ቤቱን ለላላ ሦስተኛ ወገን አሳልፍ ሰጥቶ ቢገኝ ቤቱን አከራይ በውለ ከገለፀው አገልግልት ውጭ እንደተጠቀመበት ተደርጎ መተርጎም ይገባዋል። ምክንያቱም አመልካች የመኖሪያ ቤት የተከራይ አከራይነት መብት በመጠበቅ ውል ያልተዋዋለ በመሆኑ፣ ይህም የአመልካች ሀሣብ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1732 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1734 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት መታየት ያለበት ነው።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ከላይ የተገለጹትን መሰረታዊ የውል ሀይለቃል አተረጓጎም ድንጋጌዎች በመተላለፍና ውለን አመልካች ከነበረው ሀሣብ በላይ በማስፊት አመልካች የኪራይ ውለን ለማፍረስ የሚችለው ተጠሪ ቤቱን ከተገለፀው ተግባር ውጭ ለንግድ ድርጅትነት ሲጠቀምበት ብቻ ነው በማለት የሰጠው ትርጉምና ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንን ስህተት አለማረሙ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለውን የኪራይ ውል በመተርጎም በኩል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአተረጓጎም ስህተት የተጋራ መሆኑን ያመለክታል በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 22 ቀን 1999 ዓ.ም. እና የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል፣ ይፃፍ።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር የገቡትን የኪራይ ውል ያላከበሩ በመሆኑ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቤቱን ለአመልካች ያስረክቡ በማለት
No topics extracted.