No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ት ማርታ አድማሱ - ጠበቃ ወርቅዬ ዓባይነህ ተጠሪ፡-
አቶ በረከት ሰብስቤ - ቀረቡ።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - አልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች በ1ኛ ተጠሪና በሥር በአንደኛ ተከሣሽ አቶ ዲዊት ጌታሁን ላይ ባቀረቡት ክስ ንብረትነቱ የሁለተኛ ተከሣሽ /የአሁን አንደኛ ተጠሪ/ በሆነና በአንደኛ ተከሣሽ ሹፋርነት ሲሽከረከር በነበረው “ካቻማሉ” የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተሳፍሬ ከድሬዲዋ ወደ አዱስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለሁ ሹፋሩ በፈጸመው ጥፊት መኪናው በመገልበጡ የአካል ጉዲት የደረሰብኝ ስለሆነ ይህንኑ ጉዲት በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለመታከም፣ የተቋረጠ ደመወዝ፣ ለሕክምና እና ለመድኃኒት መግዣ ወጭ የሆነ፣ ለትራንስፖርት ለአልሚ ምግብና እንደዚሁም በእጄ ላይ በደረሰብኝ ጉዲት ምክንያት ወደፉት መሥራት ስለማልችል ይሄው ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ዘርዝረው በድምሩ ብር 581,4ዐ2.25(አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አራት መቶ ሁለት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም) ተከሣሾች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ንብረትነቱ የሁለተኛ ተከሣሽ የሆነው አውቶቡስ መኪና በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ/ በኩል የመድን ሽፊን የተገባለት መሆኑን በማረጋገጡ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 43 መሰረት የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን ወደ ክርክሩ በማስገባት ግራ ቀኙን አከራክሮ በከሣሽና የመኪናው ባለንብረት በሆኑት ሁለተኛ ተከሣሽ መካከል የአጓዥነት ውል መኖሩ የተረጋገጠ ስለሆነና በን/ሕ/ቁ. 595 መሰረት በተሳፊሪ ላይ ለሚደርስ ጉዲት ኃላፉ የሚሆነው አጓዡ እንደሆነ ስለተመለከተ አንደኛ ተከሣሽ የመኪናው አሽከርካሪ እንጂ አጓዥ ስላልሆነ በከሣሽ ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለበትም በማለት አንደኛ ተከሣሽን ከክሱ አስወጥቷል።
ሁለተኛ ተከሣሽን በተመለከተም የመኪናው ባለንብረት ስለሆነ በከሣሽ ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት ካለ በኋላ በንግድ ሕግ ቁጥር 597/1/ መሰረት በጉዞ ላይ ጉዲት ለደረሰበት መንገደኛ የሚከፈለው ካሳ ከብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የማይበልጥ ሲሆን እስከ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የካሣ ክፍያ ለማግኘትም ቢሆን በአደጋው የደረሰው ጉዲትና የጉዲት መጠን በማስረጃ ተደግፍ መቅረብ እንዲለበት በውሣኔው ላይ አስፍሮ ነገር ግን ከሣሽ በግራ እጄ ላይ በደረሰው የነርቭ ጉዲት በውጭ አገር ለመታከም ብር 2ዐዐ,000( ሁለት መቶ ሺህ) ያስፈልጋል፣ እንደዚሁም በሰውነቴ ላይ ለደረሰ ጉዲት ለሕክምና ብር 25,000(ሃያ አምስት ሺህ ብር) ያስፈልጋል በማለት የጠየቁትና የኮምፒዩተር ሙያ ለመማር የተከፈለ ክፍያና ወደፉት በኮምፒዩተር ሙያ አገልግልት ሉገኝ የሚችል በማለት የጠየቁት የካሣ ክፍያ በማስረጃ ተደግፍ ያልቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ብሎል። ከዚህም በተጨማሪ ከሣሽ በአደጋው ምክንያት ለ4 ወር የመምህርነት ሥራዬ የተቋረጠ ስለሆነ የ4 ወር ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት የጠየቁትንም በተመሣሣይ ከሣሽ በመምህርነት ሙያ የምታገለግል ስለመሆኗና በአደጋው ምክንያት ደመወዝ የተቋረጠባት ስለመሆኑ በማስረጃ አላረጋገጠችም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ለጥርስ ማስተከያና ለሕክምና፣ ለመድኃኒት ለአልሚ ምግብና ለትራንስፖርት የተጠየቀውን የካሣ ክፍያ በተመለከተም መጠኑ የተጋነነ መሆኑን በውሣኔው ላይ አመላክቶ ለጥርስ ሕክምናና ማስተከያ ብር 6,000(ስድስት ሺህ) ፤ ለሕክምና፣ ለመድኃኒት፣ ለአልሚ ምግብና ለትራንስፖርት ብር 2,000(ሁለት ሺህ) በድምሩ ብር 8,000(ስምንት ሺህ ) ሉከፈላት ስለሚገባ ይህንኑ ገንዘብ ሁለተኛ ተከሣሽና ለሁለተኛ ተከሣሽ መኪና የመድን ሽፊን የሰጠው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት /3ኛ ወገን ተከሣሽ/ በአንድነትና በነጠላ ለከሣሽ ይክፈለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከሣሽ በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ሲሆን ይህ ሰበር ችልትም አቤቱታውን መርምሮ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
No topics extracted.
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተጠቀሰው ሲሆን የዚህን ችልት ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች ደርሶብኛል ለሚለት የአካል ጉዲት ያቀረቡት የካሣ ክፍያ ጥያቄ የማስረጃ ድጋፍ የላለው ነው በሚል በሥር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ከሕጉ አኳያ አግባብነት አለውን? የሚለው ነው በዚሁ ጭብጥ መሰረት የሰበር አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
አመልካች የአካል ጉዲት የደረሰባቸው ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ በሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በመጓዝ ላይ እያለ ስለሆነ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ እንዲሰፈረው በግራ ቀኙ መካከል የአጓዠነት ውል /Contract of carriage/ ስላለ ይህንኑ የግራ ቀኙን ግንኙነት የሚገዛው የንግድ ሕጉ ስለሆነ ጉዲዩን ከዚሁ የንግድ ሕጉ አኳያ መመልከቱ አግባብነት ይኖረዋል።
በዚህም መሰረት መንገደኞች ከአንድ ሥፍራ ወደ ላላ ሥፍራ በሚጓዙበት ጊዜ በጉዞ ላይ የሞት ወይንም የአካል ጉዲት አደጋ ቢደርስባቸው አጓዡ ኃላፉነት እንዲለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 595 ላይ የተደነገገ ሲሆን አጓዡ ከኃላፉነት ነፃ ላሆን የሚችለው ጉዲቱ ሉደርስ የቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ /force majeure/ በሚሆንበት ጊዜ ወይንም በ3ኛ ወገን ድርጊት ወይም በእራሱ በተሳፊሪው ጥፊት መሆኑን ካሣየ እንደሆነ በቁጥር 596 ላይ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ ጉዲቱ በዚህ መልኩ የደረሰ መሆኑን አጓዡ /አንደኛ ተጠሪ/ ያላሳዩ በመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የኃላፉነት ውሣኔ መሰጠቱ አግባብነት ነበረው።
በልላ በኩልም አንድ ተሳፊሪ በጉዞ ላይ እያለ የሞት ወይንም የአካል ጉዲት አደጋ ቢደርስበት ሉከፈለው የሚችለው የካሣ ክፍያ መጠን ከብር 4ዐ,000(አርባ ሺህ) እንደማይበልጥ በዚሁ የንግድ ሕግ በቁጥር 597/1/ ላይ ተመልክቷል። ይሁንና በአንድ ተሳፊሪ ላይ ለደረሰው የሞት አደጋም ይሁን የአካል ጉዲት የሚከፈለው የካሣ መጠን ከብር 4ዐ,000(አርባ ሺህ) ሉበልጥ እንደማይችል በንግድ ሕጉ ላይ ከመመልከቱ በስተቀር የካሣው መጠን የሚሰላው በደረሰው ጉዲት ልክ ብቻ ወይንም ወደፉት በእርግጠኛነት ሉደርስ ይችላል ተብል የሚታመን ጉዲትን ጨምሮ ስለመሆኑና በአጠቃላይ የካሣ መጠን አወሳሰን /Damage Assessments/ በንግድ ሕጉ ላይ አልተመለከተም። ይህ ሁኔታ በልዩ ሕጉ ካልተሸፈነ ደግሞ የጠቅላላ ሕግ ድንጋጌዎችን መፈተሽና በዚሁ ላይ ተመስርቶ ለጉዲዩ እልባት መስጠት እንደሚገባ ከሕግ አተረጓጎም መርህ መገንዘብ ስለሚቻል በዚሁ መሰረት በፍትሐብሕር ሕጉ ጠቅላላ ስለ ውልች የሚለውን ክፍል ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም በውል ግዳታ ውስጥ ባለዔዲ የጉዲት ኪሣራ ከፊይ የሚሆነው ውለን አሟልቶ ባለመፈጸሙ ወይም ውለን ከስምምነቱ ውጭ አዘግይቶ በመፈጸሙ በባለገንዘቡ ወይም በልላው ተዋዋይ ወገን ላይ በገንዘብ የሚተመን ኪሣራ የደረሰበት መሆኑ ሲታወቅ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 179ዐ እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም ላላ ሉከፈል የሚችለው የኪሣራው መጠን ልኩ ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኃላፉነት በተደነገገው የፍትሐብሕሩ ምዔራፍ ሥር ባለ ድንጋጌዎች እንደሚመራም በፍ/ብሕር ሕግ ቀጥር 179ዐ/2/ ላይ ተመልክቷል።
ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኃላፉነት የጉዲት ኪሣራ አከፊፈልና ልኩ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ9ዐ ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎች በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ መሆኑ በሕግ የታወቀው ሰው የሚከፍለው የጉዲት ካሣ ኃላፉነቱን ያመጣው ጉዲይ በተበዲዩ ላይ ካደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን እንዲለበት፣ ለወደፉት ሉደርስ ይችላል ተብል የሚገመተው ጉዲት የተረጋገጠ ሲሆን እስኪፈጸም ድረስ ሳይጠበቅ ካሣ ሉከፈለው እንደሚገባም በቁጥር 2ዐ91 እና 2ዐ92 ላይ ተቀምጧል።
በልላ በኩልም ጉዲት የደረሰበት ወገን የደረሰበትን ጉዲት ልክና ጉዲት አድራሹ ካሣ በመክፈል ረገድ ያለበትን ግዳታ ማስረዲት እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2141 ላይ የተመለከተ ቢሆንም ተጎጂው ጉዲት የደረሰበት መሆኑን አረጋግጦ ነገር ግን የካሳውን መጠን ለመገመት አስቸጋሪ ሁኔታ በሚያጋጥም ጊዜ በቁጥር 21ዐ2 መሰረት ዳኞች የካሣውን መጠን በርትዔ ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው በመሆኑ በተያዘው ጉዲይ አመልካች በመኪናው መገልበጥ ምክንያት ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን ባቀረቡት ማስረጃ መረጋገጡን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለልም አመልካች ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ በሆነ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ተሳፍረው ሲጓዙ መኪናው በመገልበጡ ምክንያት በግራ እጃቸው ላይ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑና በአጠቃላይም በሰውነታቸው ላይ የተለያየ ጉዲት ስለመድረሱ በማስረጃ የተረጋገጠ እንደመሆኑ መጠን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ጉዲት ከፍ ብል እንደተጠቀሰው በንግድ ሕጉ ያለውን ክፍተት ወደ ጠቅላላ ሕግ በመሄድ በፍ/ብሕር ሕጉ ጠቅላላ ስለ ውልች ከሚለውና ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኃላፉነት ድንጋጌዎች ጋር አያይዞ በመመልከት የካሣውን መጠን በርትዔ መወሰን ሲገባው የካሣ ክፍያ ጥያቄው የማስረጃ ድጋፍ የለውም በማለት በተወሰነ ደረጃ ሳይቀበለው መቅረቱና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የሰጠውን ትዕዛዝ በከፉል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ በማሻሻል በሥር ፍ/ቤት ከተወሰነው የብር 8ዐዐዐ /ስምንት ሺህ/ ክፍያ በተጨማሪ ብር 22,000 /ሃያ ሁለት ሺህ/ አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ በጠቅላላ ከተወሰነው ብር 3ዐ,ዐዐዐ /ሰላሳ ሺህ/ ላይ ሁለተኛ ተጠሪ ለአንደኛ ተጠሪ መኪና በሰጠው የመድን ሽፊን መሰረት ብር 1ዐ,0ዐዐ /አሥር ሺህ/ ለአመልካች እንዱከፍል ቀሪውን ብር 2ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺህ/ አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍል ተወስኗል።
የዚህን ችልት ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።