No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 348ዐ3 ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- መ/ር መኳንንት ወረደ- ወኪል ጌታቸው ወረደ - ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡- 1/ መስከረም ዲኛው 2/ ሃይለየሱስ ዲኛው 3/ አዲነች ዲኛው ሞግዚት አቶ ጥጋቡ መኮንን - ቀርበዋል።
4/ ዙሪያሽወርቅ ዲኛው ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
አቤቱታው ላቀርብ የቻለው የደቡብ ጎንደር መስተደድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁ. 11282 ሰኔ ዐ4/1999 ዓ.ም. የሰጠውን ፍርድ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 13114 ጥቅምት 2ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም.
በሰጠው ፍርድ በመሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በሚል ነው።
የአሁኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች ተከሣሽና መልስ ሰጭ እንዱሁም የአሁን ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤቶች ከሳሾችና ይግባኝ ባዮች በመሆን እየተከራከሩ የመጡ ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ መሰረታዊ ይዘቱ ደግሞ በደቡብ ጎንደር መስተደድር ዞን በእብናት ከተማ ቀበላ ዐ1 የሚገኘውን የአውራሽ አባታችን አቶ ዲኛው አስፊው የሆነውን አዋሳኞቹ በምስራቅ የወ/ሮ እንዬ ጥጋቡ ቤትና ቦታ፣ በምዔራብ የአቶ አስማረ አየለ ቤትና ቦታ፣ በሰሜን የሉቀ ትጉሃን ፍስሃ እርቁዬ ቤትና ቦታ እንዱሁም በደቡብ የመልዛ አውራ መንገድ የሆነ ቤትና ቦታ ተከሣሽ በኪራይ እየተጠቀመበት ከቆየ በኋላ አባታችን ሲሞት ሉያስረክበን ስላልቻለ ቤቱን ያስረክበን ያልተከፈለ የቤቱ ኪራይም ይከፈለን የሚል ነው።
ስር ተከሣሹም በሰጡት መልስ የተጠቀሰውን ቤት ከሟች ዲኛው አስፊው ሃምላ ዐ4/1996 ዓ.ም. በተፃፈ የሽያጭ ውል በብር 725ዐ /ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ሸጠውልኝ ስሙን ሳያዞሩልኝ በስራ ምክንያት ወደ ሰሜን ጎንደር ተዛውረው እንደሞቱ በመግለጽ የከሳሾች ክስ ሕጋዊ ያልሆነ ጥቅምን ለማግኘት ታስቦ የቀረበ ስለሆነ በቂ ኪሣራ ተቆርጦልኝ በነፃ ልሰናበት ይገባል ብለዋል።
የስር ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገኖች ክርክር በሰውና በጽሁፍ ማስረጃዎች አጠናክሮ ከመረመረ በኋላ የደረሰበት ማጠቃለያ ስር ተከሣሽ ከከሳሾቹ አውራሽ አከራካሪውን ቤት ሐምል ዐ4/1996 ዓ.ም. በተፃፈ ውል በሕጋዊ መንገድ በብር 725ዐ /ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ እንደገዛና ገዢም ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ/ ወዱያውኑ ለሻጭ ማለትም ለአቶ ዲኘው አስፊው እንደከፈለና ቀሪው ብር 325ዐ /ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ ሻጭ የቤቱን ስም በገዢ ሲያዛውሩ እንደሚሰጥ እንደተዋዋለ ከገለፀ በኋላ ውለ በሕጋዊ መንገድ የተፈፀመ በመሆኑ ተከሳሹ ቤቱን ለከሣሾች የሚመልሱበት ምክንያት እንደላለ ነገር ግን ሳይከፍለ የቀሩትን ብር 325ዐ /ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ ለከሣሾቹ እንዱከፍለና ቤቱ በተከሣሹ ስም መዛወር እንዲለበት ወሰነ።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከላይ የቀረበውን ክርክርና ውሣኔ በይግባኝ ቀርቦለት ካከራከረ በኋላ በፍ/ይ/መ/ቁ. 13114፣ ጥቅምት 2ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ የግራ ቀኙ ወገኖች የቤት ሽያጭ ውል በሚመለከተው ውል አዋዋይ አካል ወይም በፍርድ ቤት ያልተደረገ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት ውል ነበር ማለት እንደማይቻል በአጠቃላይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 21448 በሰጠው ውሣኔ ያስቀመጠውን የሕጉን አተረጓጎም የሚፃረር የቤት ሽያጭ ውል በመሆኑ ውድቅ እንደሆነ በመግለጽ የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በመሻር ቤቱ ለስር ከሳሾች /ይግባኝ ባዮች/ ሉመለስላቸው ይገባል ብሎል።
ከላይ የሰፈረው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልካች ጥቅምት 23/2ዐዐዐ ዓ.ም. የተፃፈ አቤቱታ ወደ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በአመልካቹና በተጠሪዎቹ አውራሽ /አባት/ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል በተዋዋዮቹ ወገኖች መካከል እንደ ሕግ ስለሚቆጠር የምዝገባ አስፈላጊነት በ3ኛ ወገኖች ዘንድ ውጤትን እንዱያስገኝ ሲባል እንጂ የተደረገውን የሽያጭ ውል ሉያፈርስ አይገባም፤ ይህ ሃሣብም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 ተመልክቷል፤ በስር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ አመልካች ቤቱን በኪራይ መልክ እንደያዝኩ በማስመሰል እንድለቅላቸው የሚጠይቅ ሆኖ እያለ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን ከተያዘው ጭብጥ በመውጣት ውለ ዋጋ እንደላለው ለፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723 ትርጉም ሰጥቶ ማለፈ አግባብነት የለውም፤ ውለ ይፈርሳል እንኳ ቢባል አመልካች ለተጠሪዎቹ አውራሽ ማለትም ለሻጭ የከፈልኩት ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ ብር/ በምን ሁኔታ መተርጎም እንዲለበት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዝምታ ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው የሚል ነው።
ተጠሪዎችም በሞግዚታቸው በኩል የካቲት 14/2ዐዐዐ ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን አጭር ይዘቱም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ የሚነቀፍበት አንዲችም ምክንያት ባለመኖሩ እንዱፀናላቸው፤ አመልካች ለሟች አቶ ዲኘው አስፊው ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ ብር/ በቤቱ ሽያጭ ምክንያት ከፍለው እንደነበር ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ገንዘብ እንዱመለስላቸው መጠየቃቸው አግባብነት የለውም፤ ይልቁንስ አመልካች በኪራይ መልክ የያዙትን ቤት የ4 ዓመት ኪራዩን ብር 48ዐዐ /አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ ስላልከፈለ እንዱከፍለ ሆኖ ፍርድ ይሰጠን፤ ወጪና ኪሣራችንም ይታሰብልን የሚል ነው።
አመልካችም መጋቢት 12/2ዐዐዐ ዓም በሰጡት የመልስ መልስ ተጠሪዎች እርስ በርሱ የሚምታታ የኪራይ ጥያቄ ሉያቀርቡብኝ አይችለም ያለ ሲሆን ቀሪው በአቤቱታቸው ውስጥ የዘረዘሯቸውን ሃሣቦች የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ደግሞ መዘርዘር ሳያስፈልግ ታልፎል።
ይህ የሰበር ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ወገኖች የክርክር አመጣጥ ከላይ እንደተቀመጠው ከተገነዘበ በኋላ፡-
በአመልካችና የተጠሪዎች ወላጅ አባት በሆኑት በአቶ ዲኛው አስፊው መካከል ሐምል ዐ4/1996 ዓ.ም. የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም?
ውለ በሕግ መሰረት ያልተደረገ ነው የሚባል ከሆነ አመልካች በውለ መፈፀም ምክንያት ለተጠሪዎች አባት /አውራሽ/ የከፈለት ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ ብር/ ሉመለስላቸው ይገባል ወይስ አይገባም?
ተጠሪዎች በመልሳቸው አመልካች እንዱፍላቸው የጠየቁት የ4 ዓመታት የአከራካሪው ቤት ኪራይ ብር 48ዐዐ /አራት ሺህ ስምንት መቶ/ የሕግ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚለትን ጭብጦች በመመስረት ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ የግራ ቀኙን ወገኖች እያከራከረ ያለው ጉዲይ የቤት ሽያጭ ውል በመካከላቸው መኖር ወይም ያለመኖር ሲሆን አመልካች ከተጠሪዎች አባት /አውራሽ/ ሐምል ዐ4/1996 ዓ.ም. በተደረገ ውል በብር 725ዐ /ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ ቤት እንደገዙ የሚያመለክተው ጽሁፍ ወደሚመለከተው ውል የማዋዋል ስልጣን ያለው አካል ወይም ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ የተመዘገበ አይደለም። ምንም እንኳ ሻጭና ገዢ እንዱሁም ምስክሮች በውለ የፈረሙ ቢሆንም ይህ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ሕጋዊ ለመሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት ዘንድ ቀርቦ የመመዝገቡን አስገዲጅነት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 አስቀምጦታል። የምዝገባው ሂደት ባልተሟላበት ሁኔታ ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረቱ ሽያጭ ሕጋዊ ልባል እንደማይችል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ሚያዝያ 3ዐ/1999 ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ ግልጽ ትርጉም እንደሰጠበት ነው። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰጣቸው የመጨረሻ ፍርድችም በፋዳራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች ወይም የተለያዩ እርከኖቻቸው ተቀባይነት ሉያገኙ እንደሚገባ አዋጅ ቁጥር 454/1997 አስፍሯል። ከላይ የተጠቀሰው የሰበር ችልት ውሣኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1723/1/ እና 2878 ያላቸውን ልዩነት አስፍሯል። ይኸውም የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በአዋዋይ አካል ወይም በፍርድ ቤት ፉት እንዱደረግ የማድረጉ አስፈላጊነት በተዋዋይ ወገኖቹ መካከል የሚፀና ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 የተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ዓላማ ደግሞ ውለ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት ለማምጣት ሲባል ነው። ከዚህ የሕግ ይዘትና አተረገጓጎም አኳያ የአሁኑ አመልካች የሽያጭ ውለ በአዋዋይ አካል ወይም በፍርድ ቤት ፉት አለመፈፀሙ ከተጠሪዎች አባት /አውራሽ/ የገዛሁትን አከራካሪውን ቤት ውጤት የላለው አያደርግብኝም በማለት ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ተቀባይነት የለውም። ስለሆነም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ጭብጥ በሚመለከት የሰጠው ትንታኔ ትክክለኛ በመሆኑ በአመልካች ጥያቄ ላይ የፈፀመው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ ከላይ እየተጠቀሰ የመጣውን አከራካሪ ውል መሰረት በማድረግ አመልካች የተጠሪዎች አባት ለሆኑት ለአቶ ዲኛው አስፊው ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ/ እንደሰጧቸውና ብር 325ዐ /ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ቀርቷቸው እንደነበር የደቡብ ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰነድና በሰው ምስክር እንዲረጋገጠው ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል። ይሁን እንጂ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አከራካሪው ውል ሕጋዊ አይደለም የሚል ውሣኔ ሲሰጥ አመልካች ለተጠሪዎች አባት የከፈለት ከላይ የተጠቀሰው ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ ብር/ እንዱመለስላቸው አብሮ መወሰን አልነበረበትም ወይ? የሚለውን ነጥብ በተመለተ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 እንዲስቀመጠው ተዋዋይ ወገኖቹን ወደ ነበሩበት የመመለስ ተግባር መከናወን እንዲለበት ነው። ከዚህ ድንጋጌ አኳያ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪዎች አባት በአከራካሪው ውል ምክንያት የከፈለትን ብር 4ዐዐዐ /አሪት ሺህ ብር/ ተጠሪዎች እንዱመልሱላቸው አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው።
በመጨረሻም የተቀመጠውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ ተጠሪዎች በዚህ ሰበር ችልት በሰጡት መልስ አመልካች ያልከፈለትን የ4 ዓመት የቤት ኪራይ በጠቅላላ ብር 48ዐዐ /አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ ሕጋዊ አግባብነቱ ሲታይ ተጠሪዎቹ ይህንን ነጥብ በተመለከተ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ያቀረቡት ይግባኝ የለም። ይህንን ጥያቄ እያቀረቡ ያለት አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት እየተካሄደ ባለው ክርክር ነው። ይግባኝ ወይም አቤቱታ ባላቀረቡበት ሁኔታ የቤቱ ኪራይ እንዱከፈላቸው ተጠሪዎች መጠየቃቸው ሕጋዊ አካሄድን የተከተለ ባለመሆኑ ከዚህ አኳያ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 13114 ጥቅምት 2ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በአብላጫ ድምጽ ተሻሽሎል፤ ይፃፍ።
በአመልካችና የተጠሪዎች አባት /አውራሽ/ በሆኑት በአቶ ዲኛው አስፊው መካከል ሐምል ዐ4/1996 ዓ.ም.
የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 አኳያ ሲታይ ውል ለማዋዋል ስልጣን ከተሰጠው አካል ያልተመዘገበ ወይም በፍርድ ቤት ፉት ያልተፈፀመ በመሆኑ አመልካች ውለ እንዱጸናላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን በሽያጭ ውለ ምክንያት አመልካች ለተጠሪዎች አባት የከፈለትን ብር 4ዐዐዐ /አራት ሺህ ብር/ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 መሰረት ተጠሪዎች ሉመልሱላቸው ይገባል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.