No summary available.
ጥቅምት 6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ መሐመድ ካሣሁን - ጠበቃ አረጋኸኝ መርዔድ ተጠሪ፡- አቶ ሣልሀዱን ኑር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በሰሜን ጎንደር መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪ በአመልካችና በሥር አንደኛ ተከሣሽ የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ አቶ ኑር ሁሴን ካሴ ከተባለት ሸሪኬ ጋር በመሆን በደንቢያ ወረዲ ልዩ ስሙ "ዋዋ" በተባለ ቦታ መሬት ለማልማት በነበረን ፍላጎት 17 ሄክታር መሬት በኪራይ ተሰጥቶን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተን ከሸሪኬ ከአቶ ኑርሁሴን ካሴ ጋርም ሰኔ 5 ቀን 1988 ዓ.ም የህብረት ሽርክና ውል ተፈራርመን ከዚያም በተፈቀደልን መሬት ላይ አስፈላጊ የሆነውን የማለስለስና የማዘጋጀት ሥራ ሰርቼ በተዘጋጀው መሬት ላይ የተለያየ እህል ዘርቼበት እንዲለ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የውለ ጊዜ ሣይደርስ መሬቱን ከተዘራው እህልና ከተለያዩ የግብርና መሣሪያዎች ጋር አንደኛ ተከሣሽ የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በመውሰድ ለሁለተኛ ተከሣሽ አሣልፍ ሰጥቷል፤ በማለት፣ ይገባናል ያለትን የእህልና የጉልበት ዋጋ በመዘርዘር በድምሩ ብር 71.99ዐ እንዱከፈላቸውና መሬቱም እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ በአንደኛ ተከሣሽና በአቶ ኑርሁሴን ካሴ መካከል በተደረገው የመሬት ኪራይ ውል መሰረት ውለ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንደና ዋናው በኪራይ ውለ አንቀጽ 11/ለ/ መሰረት ተከራዩ ለአከራዩ መክፈል የሚገባውን የመሬት ኪራይ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ሣይከፈል በሚቀርበት ጊዜ እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ተከራዩም በውለ በገቡት ግዳታ መሰረት የመሬት ኪራዩን መክፈል ሲገባቸው ባለመክፈላቸው አንደኛ ተከሣሽ ውለን እንዲቋረጠ ፍ/ቤቱ ስለተገነዘበ በተቋረጠ ውል ላይ በመመስረት ከሣሽ ያቀረቡት ክስ አግባብነት የለውም በማለት ሣይቀበለው ቀርቷል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ፣ በተደረገው የመሬት ኪራይ ውል መሰረት ተከራዩ መክፈል የሚገባውን የመሬት ኪራይ በየጊዜው ሲከፍል እንደነበር በአስረጂነት የቀረቡት ሰነድች የሚያረጋግጡ ሆኖ ሣለ የሥር ፍ/ቤት ውለን ሉያቋርጥ የሚችል ነገር መኖሩን ሣያረጋግጥ በአንደኛ መ/ሰጭ /የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት/ የቀረበውን መከራከሪያ ብቻ በመቀበል በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል ተቋርጧል በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የላለው ነው በማለት ሽሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው መሬት ለይግባኝ ባይ /ለአሁን ተጠሪ/ እንዱመለስለት በማለት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን የክፍያ ጥያቄውን በተመለከተ ግን የሥር ፍ/ቤት በማስረጃ አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን ወደ ሥር ፍ/ቤት መልሷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ችልትም የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ አመልካች /የሥር ሁለተኛ ተከሳሽ/ ከወረዲው ገጠር ልማት ጽ/ቤት ጋር ባደረገው ውል ያገኘውን መሬት ለተጠሪ እንዱያስረክብ መወሰኑ ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሁፍ አከራክሯል። ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች ከሥር አንደኛ ተከሣሽ ከደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ጋር ባደረጉት ውል መሰረት የያዙትን መሬት ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መወሰኑ አግባብነት አለውን? የሚለው ነው። ከዚሁ ጭብጥ አኳያም የሰበር አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ተጠሪ በአመልካችና በሥር አንደኛ ተከሣሽ የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ላይ ክስ ያቀረቡት በኪራይ ውል መነሻነት የተያዘውን 17 ሄክታር መሬት አንደኛ ተከሣሽ ለሁለተኛ ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ ያለአግባብ አሣልፍ የሰጠ ስለሆነ መሬቱን መልሰው ያስረክቡኝ ኪሣራም እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
የመሬት ኪራይ ውለ ተደርጎ የነበረው በአቶ ኑርሁሴን ካሴና በወረዲው ግብርና ልማት ጽ/ቤት በኩል የነበረ ቢሆንም እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ በየዓመቱ ውለ ሲታደስ የነበረው በተጠሪ በአቶ ሣልሀዱን ኑር ስም ስለነበር ይህ ሁኔታ ተጠሪን ተዋዋይ ወገን እንዲደረጋቸው ስለሚያስገነዝብ ውለ በተጠሪ ላይ የመብትም ሆነ የግዳታ ምንጭ ላሆን ስለሚችል ይህንኑ ውል መሰረት በማድረግ ክስ ማቅረባቸው ክስ ባቀረቡበት ነገር መብትና ጥቅምት /vested interest/ እንዲላቸው ለመገንዘብ ተችሎል።
ተጠሪ ክስ ባቀረቡበት ነገር መብትና ጥቅም አላቸው ከተባለ ውለን አስገድድ ለማስፈፀም /forced performance/ ያቀረቡት ክስ ከሕጉ አኳያ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ መርምረናል።
No topics extracted.
የሥር አንደኛ ተከሣሽ የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የውለ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፉት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ከተጠሪ ላይ በመውሰድ ለአመልካች ስለማከራየቱ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የመሬት ኪራይ ውለን በተናጠል መሰረዙ /unilateral cancellation/ አግባብነት የለውም ቢባል ውለ የተሰረዘበት ወገን በውለ መሰረዝ ምክንያት የደረሰበት ኪሣራ ቢኖር ይህን ከመጠየቅ አልፍ የውለን ቃል በመፃረር የሰራውን ሥራ እንዱያፈርስና እንደ ውለ ተገድ እንዱፈጽም መጠየቅ ስለመቻለ ከሕጉ አንፃር ተመልክተነዋል።
በዚህም መሰረት ውልን አስገድድ ለማስፈፀም በሚቀርብ አቤቱታ በውለ አለመከበር የተነሣ በባለገንዘቡ ላይ የደረሰው ወይም ይደርሣል ተብል የሚገመተው ኪሣራ ከባለእዲው ቀጥተኛ የውል አፈፃፀም በስተቀር በጉዲት ኪሣራ መልክ ፈጽሞ ሉካስ የማይችል በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ እንደዚሁም እንደ ውለ ይፈፀምልኝ ብል ለሚጠይቀው ተዋዋይ ወገን የተለየ ጥቅም በሚሰጠው ጊዜና አፈፃፀሙም የባለእዲውን የግል ነፃነት የማይነካ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1776 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ የውለ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፉት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይሄው 17 ሄክታር መሬት ከተጠሪ ያለአግባብ ተነጥቆ ለአመልካች ተሰጥቷል ቢባል እንኳን በተጠሪ ላይ የደረሰው ወይንም ወደፉት ይደርሣል ተብል የሚጠበቀው ኪሣራ በጉዲት ኪሣራ መልክ ሉካስ የሚችል በመሆኑ ተጠሪ ኪሣራ ከመጠየቅ አልፈው መሬቱን ተከሣሾች ተገደው ሉያስረክቡኝ ይገባል በማለት ያቀረቡት ክስ በውል አፈፃፀም የተለየ ጥቅም /special interest/ ሣይኖራቸውና በአጠቃላይም ሕጉ ውልን አስገድድ ስለማስፈፀም ከደነገገው መርህ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሥር ተከሣሾች መሬቱን ለሥር ከሣሹ ሉያስረክቡ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ 1/ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ8167 ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት የሥር ተከሣሾች ለሥር ከሣሽ ሉያስረክቡ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለተፈፀመበት ይህንኑ የውሣኔውን ክፍል በመሻር የኪሣራ ክፍያ ጥያቄውን በተመለከተ በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በኩል ታይቶ እንዱወሰን ጉዲዩን ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለሱ በአግባቡ ስለሆነ አጽንተነዋል።
2/ አመልካችም ሆነ የሥር አንደኛ ተከሣሽ የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ለተጠሪ ሉያስረክቡ አይገባም ተብል ተወስኗል። ይፃፍ።
3/ ይህ ፍርድ የሰበር አቤቱታ ባላቀረበው የደንቢያ ወረዲ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ላይ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 331 መሰረት ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
4/ ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።