No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሀ ወርቅነህ አብደልቃድር መሐመድ አሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ዝናሽ በቀለ ማንደፍሮ - አልቀረቡም።
መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ሐረገወይን በቀለ - ቀርበዋል።
በዚህ መዝገብ የተደረገውን የሰበር አቤቱታና ክርክር መሰረት አድርገን ቀጥል ያለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን አተረጓጎም የሚመለከት ነው። ለጉዲዩ መነሻ የሆነው ነገር ሟች አቶ በቀለ ማንደፍሮ ለአሁንዋ አመልካች በአርሲ ነገላ የሚገኘውና በ1967 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁ. 47/67 የተወረሰውን ቤት በኑዛዜ መስጠታቸው ኑዛዜውን ፈራሽ ማድረግ አለማድረጉን የሚመለከት ነው። የአሁን አመልካች ኑዛዜው ሉፈፀም የማይችልና ከላልች ወራሾች ጋር እኩል የመካፈል መብቴን የሚነካ በመሆኑ ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለት ከሥር ጀምሮ የተከራከረች ሲሆን መልስ ሰጪ ደግሞ በቤቱ ላይ ሟች አበል ይቀበለበት ስለነበር ኑዛዜው ፈራሽ የሚሆንበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክራለች። የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ነጥብ ላይ የተለያየ ውሣኔ ሰጥተዋል። ጉዲዩን መጀመሪያ የተመለከተው የወረዲ ፍ/ቤት ኑዛዜው ይፀናል ሲል ይግባኙ የቀረበላቸው የከፍተኛና የጠቅላይ ፍ/ቤቶች ኑዛዜው ሉፈርስ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥተዋል። የይግባኝ ፍ/ቤቶቹ ኑዛዜው ሉፈርስ ይገባዋል በማለት ውሣኔ ለመስጠት የቻለት በኑዛዜው የተጠቀሰውና በአርሲ ነገላ የሚገኘው ቤት የከተማ ትርፍ ቤት ለመንግሥት እንዱሆን በወጣው አዋጅ የተወረሰ በመሆኑ የኑዛዜው ውጤት የአመልካች ከውርስ መነቀልን የሚያስከትል ነው፤ ይህ ደግሞ አመልካች ከወራሾች እኩል እንዲትካፈል የሚያደርግ ነው በማለት ነው። ጉዲዩን መጨረሻ ላይ ያየው የደቡብ ሕዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት በልላ በኩል ኑዛዜው የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የክልለን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ሽሮአል። የሰበር ችልት ኑዛዜው ይጸናል የሚል ውሣኔ ለመስጠት ኑዛዜው የሚመለከተው አርሲ ነገላ የሚገኘው ቤት የተወረሰ ቢሆንም ሟች አበል ይቀበለበት ስለነበር ኑዛዜው አበለን አስመልክቶ ተፈፃሚ ላሆን ይችላል፤ ከዚህም ላላ ቤቱ የተወረሰ ቢሆንም ሉመለስ የሚችልበት እድል የለም ልባል ስለማይችል ኑዛዜው ሉፈፀም በማይችል ጉዲይ ላይ የተረገ ነው ልባል አይችልም፤ የአመልካች ሕጋዊ ወራሽ መሆን የኑዛዜውን ፈራሽነት የሚያስከትል አይደለም፤ የሚለትን ምክንያቶች ሰጥቷል የሰበር ችልቱ አመልካች ኑዛዜው ይፍረስልኝ የሚል አቤቱታ ሳታቀርብ ከፍተኛውና ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ኑዛዜው እንዱፈርስ ውሣኔ መስጠታቸው ባልቀረበላቸው ጉዲይ ላይ ውሣኔ መስጠታቸውን ስለሚያመለክት ሂደቱ ግድፈት የነበረበት መሆኑንም በፍርደ አትቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰበር ችልት ውሣኔ በመቃወም ነው። የሰበር አቤቱታው ዝርዝር ሃሣቦችን ያጠቃለለ ሲሆን በዚህን ፍርድ ቤቱ ከያዘው ዋነኛው ነጥብ ጋር ግንኙነት ያለው ቅሬታ በተወረሰ ቤቱ ላይ የተሰጠው ኑዛዜ እንዱፀና መደረጉ የአመልካችን የወራሽነት መብት የሚጎዲ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ለቀረበው የሰበር አቤቱታ የጽሁፍ መልስ ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። የመልሱ ዋነኛ ፍሬ ሃሣብ ኑዛዜው የፀና ነው መባለ የሕግ ስህተት አይደለም በመሆኑም የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ሉፀና ይገባዋል የሚል ነው። የመልስ መልሱ የሰበር ማመልከቻውን የሚያጠናክር ነው።
ይህ ችልት የቀረበለትን ጉዲይ ከውርስ ሕጉ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ መርምሮአል።
የሚከተለትን ጭብጦች አስመልክቶ ሕጉ የሚለውን መመልከት ለውሣኔ አስፈላጊ ሆኖም አግኝቶታል።
1/ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በመንግሥት የተወረሰን ቤት የሚመለከት መሆኑ በኑዛዜው የሚያስከትለው የሕግ ውጤት ምንድነው?
2/ ኑዛዜው ይፀናል ከተባለ በክፍፍለ ላይ የሚኖረው ውጤት ምንድነው?
እነዚህን ሁለት ነጥቦችና ላልች ተጓዲኝ ጥያቄዎች በቅደም ተከተል ከዚህ ቀጥል እንመለከታለን።
ከሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔዎች ለመገንዘብ እንደቻልነው አርሲ ነገላ የሚገኘውና ለአሁን አመልካች በኑዛዜ የተተወው ቤት በመንግሥት የተወረሰ መሆኑ አላከራከረም። በመሆኑም ሟቹ የተናዘዙት የራሳቸው ባልሆነ ንብረት ነው ማለት ነው። አንድ ሰው በራሱ ባልሆነና ሉያዝበት በማይችል ንብረቱ የተናዘዘ እንደሆነ ኑዛዜው የሚኖረው ሕጋዊ ሁኔታ ምንድነው? የሚለው ጥያቄ በውርስ ሕግ በግልጽ ምላሹ ያገኘ ነው። የውርስ ሕግ ውስጥ ይህንን ጉዲይ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 1ዐ47 እንዱህ ይነበባል።
1/ “በኑዛዜው የተደረገው ስጦታ በተለየ ነገር እንደሆነና ሟቹ በሞተበት ቀን በዚህ ነገር ላይ አንዲችም መብት የላለው እንደሆነ የኑዛዜው ስጦታ ፍርስ ነው።
2/ ስለሆነም ሟቹ ይህን ሁኔታ እያወቀ በኑዛዜው ሰጥቶ እንደሆነ ስጦታው ዋጋ ያለው ይሆናል።
3/ እንደዚህ በሆነ ጊዜ አጣሪው በኑዛዜ የተሰጠውን እቃ ዋጋ መስጠት አለበት” ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው በመርህ ደረጃ ማንም ሰው ምንም መብት በላለው ንብረት ላይ የተናዘዘ እንደሆነ የተሰጠው ኑዛዜ ዋጋ አይኖረውም። በሕግ ፉት የሚፀና ኑዛዜ ለመስጠት ሟቹ ኑዛዜ በተደረገበት ንብረት ላይ መብት ሉኖረው ይገባል በልላ በኩል በንዐስ አንቀጽ /2/ በግልጽ እንደሰፈረው ሟቹ ኑዛዜ በሚያደርጉበት ንብረት ላይ ምንም መብት የላለው መሆኑን እያወቀ ስጦታ የሰጠው እንደሆነ በስጦታው ሕጋዊነት የፀና ይሆናል። በመሆኑም ኑዛዜ አድራጊው መብት ያለው መሆን አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ስለዚህ ጉዲይ የነበረው ግንዛቤ በኑዛዜው ፍርስ መሆን አለመሆን ላይ ውጤት ይኖረዋል። ኑዛዜው ፍርስ የሚሆነው ተናዛዡ ስጦታ ባደረገበት ንብረት ላይ መብት እንደላለውና ይህም ያውቅ እንዲልነበረ ሲታወቅ ብቻ ነው። ይህ መደምደሚያ የሚገኘው ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ ሁለት ንዐስ ቁጥሮችን አጣምሮ በማንበብ ነው።
አሁን በቀረበልን ጉዲይ ተናዛዥ አርሲ ነገላ በነበረውና ለአሁን አመልካች በስጦታ በሰጡት ቤት ላይ የባቤትነት መብት አልነበራቸውም። ቤቱ በአዋጅ የተወረሰ በመሆኑና አበልም ይቀበለበት ስለነበር ሟቹ ቤቱ ላይ መብት እንደላላቸው እያወቁ ኑዛዜ ማድረጋቸው ግልጽ ነው። በመሆኑም ኑዛዜው የተሰጠበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ 1ዐ47 /2/”ን” መስፈርት የሚያሟላ ነው። በመሆኑም ምንም እንኳ ቤቱ የተወረሰ በመሆኑ ምክንያት ሟቹ በቤቱ ላይ መብት ባይኖራቸው የኑዛዜ ስጦታውን ያደረጉት ይህ መብት እንደላላቸው እያወቁ በመሆኑ ኑዛዜው ሉፈርስ የሚባው አይደለም። ኑዛዜው ፍርስ ላሆን ይችል የነበረው ሟቹ በቤቱ ላይ መብት እንደላላቸው የማያውቁ መሆኑ ማስረጃ ቢቀርብ ነበር።
በመሆኑም የደቡብ ብሕር ብሕረሰቦች ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት የኑዛዜ ስጦታው ይፀናል በማለት ያቀረበው ምክንያት ትክክል ባይሆንም ውጤቱ ግን ይህም ችልት የሚስማማበት ነው። ስለዚህ የአሁን አመልካች በተወረሰ ቤት ላይ የተደረገ ኑዛዜ በመሆኑ ብቻ ኑዛዜ ፍርስ ላሆን ይገባል በማለት ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ያለው አይደለም። ጉዲዩን የተመለከቱት የሥር ፍርድ ቤቶች ኑዛዜው በተወረሰ ሀብት ላይ የተሰጠ በመሆኑ የአመልካችን ከውርስ መነቀል ያስከትላል በማለት የኑዛዜ ስጦታውን ፍስር ማድረጋቸው የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ መሻሩ አግባብ ነው። አንድ ወራሽ አለአግባብ ተነቀለ የሚባል ቢሆን በውርሱ አከፊፈል ላይ የሚታይ እንጂ በአግባቡ የተሰጠን ኑዛዜ ፈራሽነት የሚያስከትል አይደለም።
ቀጥል መታየት ያለበት ግን የኑዛዜ ስጦታው የፀና መሆን በወርስ ክፍፍለ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው?
የሚለው ጥያቄ ነው። ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ተያያዥነት ያላቸውን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች መዲሰስ ያስፈልጋል። በቅድሚያ ከላይ የጠቀስነው የአንቀጽ 1ዐ47/3/ ይዘት መመርመር ተገቢ ነው። የዚህ ድንጋጌ መልእክት አንድ ሰው በአንድ ንብረት ላይ መብት የላለው መሆኑን እያወቀ የተናዘዘ እንደሆነ ኑዛዜው የሚፀና ከመሆኑም ባሻገር የውርስ አጣሪው የዚህ ንብረት ግምት መስጠት እንዲለበት የሚያስገነዝብ ነው። በዚህ ደንብ መሰረት ተናዛዥ በስጦታ የሰጠው ንብረት በውርሱ ሀብት እንኳን ባይኖር ከውርሱ ሀብት በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ ንብረት ወይም ገንዘብ ለስጦታ ተጠቃሚው መስጠት ሕጉ ያስቀመጠው ሥርዓት ነው። ሆኖም ይህ ደንብ ተፈፃሚ የሚሆነው ለውርስ ስጦታ /legacy/ ብቻ ነው። በመሆኑም አንድ ኑዛዜ ውስጥ ያለው የተናዛዡ ቃል የውርስ ስጦት /legacy/ መሆን አለመሆኑን መለየት ለዚሁ ድንጋጌ አፈፃፀም መሰረታዊ ነው። አንድ የኑዛዜ ቃል የውርስ ስጦታ መሆን አለመሆኑን ለመለየት ላልች የውርስ ሕጉን ድንጋጌዎች መመልከት ያስፈልጋል። አሁን ከያዝነው ጉዲይ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 913 ነው።
913 የኑዛዜ ስጦታና የክፍያ ደንብ የኑዛዜው ቃል የተናዛዥን ተቃራኒ ሐሣብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሃብት አንድ ድርሻን ወይም አንድ ንብረትን ሟቹ ለወራሾች መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብል አይቆጠርም።
የዚሁ አንቀጽ የእንግሉዝኛ ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል።
913 Legacies and rules of partition An Assignment of a portion of the succession or of property forming part of such succession made by the testator to one of her heirs shall not be deemed to be a legacy but a mere rule for partition, unless the contrary in tension of the testator emerges from the disposition.
ከዚህ ድንጋጌ ለመገንዘብ የሚቻለው በኑዛዜው የሚከናወኑ ተግባሮች የኑዛዜ ስጦታ /legacy/ ወይም የክፍያ ደንብ /Rule of Partition/ ሉሆኑ እንደሚችለ ነው። በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ከውርስ ሀብቱ መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ አያሰኘውም። ይልቁንም ይህ አይነት ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ ነው። በመሆኑም አንድ አውራሽ ለወራሹ አንድን ንብረት ቢናዘዝለት የኑዛዜው አፈፃፀም የስጦታ /legacy/ አፈፃፀምን በመከተል ሳይሆን የክፍያ ደንብ /Partition/ በመከተል የሚከናውን ይሆናል።
ኑዛዜው ስጦታን /legacy/ የሚመለከት ከሆነ በፍትሀብሕር ሕጉ አንቀጽ 942 ጀምሮ ባለ አንቀፆች መሰረት በማጣራት /liquidation/ ሥርዓት የሚከናወን ሲሆን ክፍያ ግን ክፍፍልን /partition/ በሚመለከቱና ከአንቀጽ 1ዐ6ዐ ጀምሮ ባለ ድንጋጌዎች መሰረት የሚስተናገድ ነው።
አሁን በቀረበልን ጉዲይ በአርሲ ነገላ የሚገኘው ቤት በኑዛዜው ይሰጥልኝ የተባለው የሟች ልጅ መሆንዋ ለተረጋገጠው ለአሁንዋ አመልካች ነው። አመልካች ወራሽ በመሆንዋ ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ 913 መሰረት ኑዛዜው የስጦታ ውል ሳይሆን የክፍያ ሥርዓት የያዘ ነው ማለት ነው ኑዛዜው የስጦታ ነው የሚባል ቢሆን ኖሮ በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥሮች 1ዐ37-1ዐ51 መሰረት እንዱሁም 1ዐ47/3/ መሰረት የተጠቀሰው ንብረት ወይም ግምቱ ለስጦታ ተጠቃሚው በቅድሚያ ይሰጣል። ሆኖም ከላይ እንደተጠቀሰው የአሁን አመልካች ወራሽ በመሆንዋ የኑዛዜው ቃል ክፍፍልን በሚያመለክቱ ድንጋጌዎች መሰረት የሚስተናገድ ነው። በዚህ ረገድ ከአንቀጽ 1117 ጀምሮ ያለት ድንጋጌዎች አግባብነት አላቸው አንቀጽ 1ዐ17 አባትና እናት ወይም ላልች ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸውና ለላልች ተወላጆች ሀብታቸውን ለመስጠትና ለማከፊፈል እንደሚችለ ይደነግጋል። ይህ ክፍፍል ሥርዓት አንድን ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዲት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፊፈለ እንዱቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደማይችል በአንቀጽ 1123 ተደንግጎአል። አንቀጽ 1123/1/ እና በስጦታ አከፊፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከላለ በቀር ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንደ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዲት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፊፈለ አንዱቀር ለመጠየቅ ይችላል” ይላል።
ከቀረበልን ጉዲይ ለመገንዘብ እንደቻልነው ሟቹ ኑዛዜአቸው ላይ ያለዋቸውን ቤቶች ለልጆቻቸው አከፊፍለዋል።
የዚህ ዓይነት ክፍፍል ሕጉ የሚደግፈው ቢሆንም ማንኛውም ልጅ ከአንድ አራተኛ በላይ ጉዲት የሚያደርስ ከሆነ የክፍፍል ሥርዓቱ እንዱፈርስ መጠየቅም ሆነ በዚህ መሰረት ውሣኔ መስጠት ይቻላል። ከመዝገቡ ጋር ከተያያዘው የኑዛዜ ኮፒ ለመገንዘብ እንደቻልነው አውራሹ የነበሯቸውን ቤቶች ሲያከፊፍለ ለአሁንዋ አመልካች የሰጡት አርሲ ነገላ የሚገኘውና ተወረሰ የተባለውን ቤት ሲሆን ለመልስ ሰጪ የሰጡት ላላ በሆሳዔና የሚገኘውን ቦታና ሲኖሩበት የነበረውን ቤት ነው። ለአመልካች የተሰጠው ቤት የተወረሰ መሆኑ በመረጋገጡ ለአመልካቿ በንብረት ክፍፍል የሚደርሳት ሀብት ከአንድ አራተኛ በላይ የሚጎዲት ከሆነ ክፍፍለ በአንቀጽ በ1123 መሰረት መስተካከል ይኖርበታል። አመልካች ይህን አንቀጽ ባትጠቅስም ኑዛዜው እንዱፈርስላት የጠየች በመሆኑና ትክክለኛውን አንቀጽ መጥቀስ የማይጠበቅባት በመሆኑ ያቀረበችው ጥያቄ ከዚህ ድንጋጌ አንፃር መስተናገድ ነበረበት። የሥር ፍርድ ቤቶች ይህን አላደረጉም፣ በመሆኑም ውሣኔአቸው ከላይ በተሰጠው ዝርዝር ምክንያት ሉለወጥ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የደረሰባት ጉዲት ምን ያሕል መሆኑ በሥር ፍርድ ቤቶች ያልተጣራ በመሆኑ ለወራሾች የተከፈለው ንብረት ግምት አስልተው ለአሁን አመልካች የንብረቱ አንድ አራተኛ እንዱሰጡ መደረጉ አግባብ ሆኖ አግኝተነዋል።
ለማጠቃለል የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ኑዛዜው ይፀናል በማለት የሰጠው ውሣኔ ከላይ በተሰጠው ዝርዝር ምክንያት ሉሻሻል የሚገባው ነው። ኑዛዜው የአሁንዋን አመልካች ከአንድ አራተኛ በላይ ስለሚጎዲት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይህን የጉዲት መጠን የሚያስተካክል የአከፊፈል ሥርዓት ሉከተል ይገባል።
ው ሣ ኔ 1/ የደቡብ ብሕር ብሕረሰቦች ጠቅላይፍ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ 5ዐ17
No topics extracted.