No summary available.
የመ/ቁ. 4ዐ781 ሐምል 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ ፍቅረሥላሴ ካህሳይ - ጠ/ዲኛቸው ተስፊዬ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሮማን ታደሰ - ጠ/መንበረስላሴ በዛብህ ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ የቀረበው የፍቺ ጥያቄን የሚመለከት ጉዲይ ነው። ተጠሪ ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን ክስ ከማቅረባቸው በፉት በግራ ቀኙ መሐከል የነበረው ጋብቻ አውስትራሉያ አገር በሚገኝ ፍርድ ቤት በፍቺ በመፍረሱ የፍቺ ውጤት እንዱሰጥላቸው ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱ የፍቺ ውጤት ለመወሰን በቅድሚያ በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገው ጋብቻ ሉፈርስ ይገባል በማለት አመልካችን ሳይጠራ የተጠሪዋን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
ይህን ውሣኔ በመቃወም ተጠሪዋ ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ከዚህ በኋላ ነው ተጠሪ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ከአመልካች ጋር ጥር 16 ቀን 1984 ዓ.ም. የመሰረቱት ጋብቻ እንዱፈርስ ጥያቄ ያቀረቡት። አመልካች የተጠሪ አቤቱታ ደርሷቸው የተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ መቃወሚያቸውን ውድቅ አድርጎ በአመልካች እና በተጠሪ መሃከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ይፍረስ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ አመልካች ያቀረቧቸው ቅሬታዎች ቀደም ብለው በውሣኔ ያለቁ ናቸው በማለት ሳይቀበላቸው ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ፣ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ስልጣን የላቸውም፣ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን የለውም፤ ጉዲዩ ሉዲኝ የሚገባው በአውስትራሉያ ሕግ ነው፣ የኢትዮጵያ ፍ/ቤት ስልጣን አለው ቢባል እንኳን ጋብቻው በፍቺ ፈርሷል፤ የሚል ነው።
ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በአውስትራሉያ አገር ሲኖሩ በዚያው አገር መፊታታቸውን ግራ ቀኙ ሳይክደ በድጋሚ ፍቺ የመወሰኑ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ተጠሪም ቀርበው በቃል ባደረጉት ክርክር የአመልካች ቅሬታ ቀደም ሲል በውሣኔ ያለቀ ጉዲይ ነው በማለት ተከራክረዋል። ችልቱም ጉዲዩን ከያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካች በግራ ቀኙ መሃከል የነበረው ጋብቻ በአውስትራሉያ አገር በፍቺ ፈርሷል ስለዚህ ድጋሚ ፍቺ የሚወሰንበት ምክንያት የለም ሲለ ተጠሪ ደግሞ ይህ ክርክር ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ውድቅ ከተደረገ በኋላ በይግባኝ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ያፀናው ስለሆነ በውሣኔው ያለቀ ጉዲይ በመሆኑ ድጋሚ ላታይ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
እኛም ወደ ፍሬ ጉዲዩ ከመግባታችን በፉት በቅድሚያ ተጠሪ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡበት ጉዲይ ቀደም ሲል በፍርድ አልቋል በማለት ያቀረቡትን መቃወሚያ መመልከቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከግራ ቀኙ ክርክር እንደተደረዲነው ተጠሪ ቀደም ሲል የግራ ቀኙ ጋብቻ በአውስትራሉያ አገር በፍቺ በመፍረሱ የፍቺ ውጤት እንዱወሰንላቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። ፍ/ቤቱ ደግሞ የአውስትራሉያ ፍ/ቤት በፍቺ እንዱፈርስ የወሰነው ግራ ቀኙ በዛው አገር ያደረጉት ጋብቻ እንጂ አስቀድሞ በኢትዮጵያ የተደረገው ጋብቻ ስላልሆነ የመጀመሪያው ጋብቻ ሳይፈርስ የፍቺ ውጤት ሉጠየቅ አይገባም በማለት የተጠሪን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኝ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ይግባኛቸው ውድቅ ተደርጓል። ከክርክሩ ሂደት እንደተረዲነው ፍ/ቤቱ ይህንን ውሣኔ የሰጠው አመልካችን ሳይጠራ ነው። በመሆኑም በዚህ ክርክር አመልካች የክርክሩ ተካፊይ ስላልነበሩ አሁን አመልካች በሚያቀረቡት ክርክር ላይ ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሣኔ እንደሰጠ የሚያስቆጥረው አይሆንም። ምክንያቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መሰረት በድጋሚ ክስ እንዲያቀርብ ወይም ክርክር እንዲያቀርብ የሚከለከለው በክርክሩ ተካፊይ የሆነን ወገን ነው።
በልላ በኩል ግን ተጠሪ በኢትዮጵያ አገር የተደረገው ጋብቻ እንዱፈርስ ባቀረቡት ክስ አመልካች እነዚህን መቃወሚያዎች አቅርበው ፍርድ ቤቱ መቃወሚያዎቹን በብይን አልፍባቸዋል። አመልካች በብይኑ ላይ ይግባኝ ጠይቀው ይግባኙ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በኢትዮጵያ የተደረገው ጋብቻ ሉፈርስ ይገባል አይገባም የሚለው ጭብጥ ላይ ፍ/ቤቱ የመጨረሻ ውሣኔ የሰጠው በዚህ ሁኔታ የቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ነው። ምንም እንኳን አመልካች ባቀረቧቸው መቃወሚያዎች ላይ ብይን የተሰጠና ይህም ብይን በይግባኝ የፀና ቢሆን የፍቺ ጥያቄን አስመልክቶ የተሰጠ ውሣኔ ስለላለ በዚህ ላይ አመልካች ያቀረቡት ክርክር የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘና በድጋሚ ላታይ አይገባም ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተጠሪ አመልካች ያነሱት ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መሰረት ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም።
ወደ ፍሬ ጉዲዩ ስንመለስ ከክርክሩ ሂደት አመልካችና ተጠሪ ጥር 16 ቀን 1984 ዓ.ም. በባሕል ጋብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጋቡ መሆኑን እንዱሁም የካቲት 5 ቀን 1985 ዓ.ም. በአውስትራሉያ አገር የብሕራዊ ጋብቻ መፈጸማቸውን ተረድተናል። እንዱሁም የግራ ቀኙ ጋብቻ አውስትራሉያ አገር በሚገኘው የማጅስትሬት ፍ/ቤት በፍቺ መፍረሱንም ግራ ቀኙ አልተካካደም። እንደውም ተጠሪ ከአመልካች ጋራ ያላቸው ጋብቻ በፍቺ መፍረሱን ተቀብለው የፍቺ ውጤት እንዱወሰንላቸው አቤቱታቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው የነበረ መሆኑን ተገንዝበናል። በእርግጥ የከፍተኛ ፍ/ቤት በአውስትራሉያ አገር የፈረሰው ጋብቻ በዛው አገር የተደረገው እንጂ በአ/አበባ የተደረገው ጋብቻ ባለመሆኑ ይህ ጋብቻ ሳይፈርስ የፍቺ ውጤት ሉወሰን አይችልም በማለት የተጠሪን አቤቱታ ሳይቀበል አልፍታል።
ጋብቻ ማለት አንድ ወንድና ሴት ባልና ሚስት ሆነው አንድ ላይ ለመኖር የሚያደርጉት ሕጋዊ ስምምነት ነው።
በኢትዮጵያ ጋብቻ በሶስት ዓይነት መንገድ ሉፈፀም እንደሚችል የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 1 ያመለክታል።
በእነዚህ ስርዓቶች በአንደኛው ጋብቻ ከተፈፀመ በድጋሚ በልላኛው ስርአት ሉፈጸም የሚገባበት የሕግ ምክንያት አይኖርም። ድጋሚ ተደርጎ እንኳን ቢገኝ ጋብቻው ፀንቶ የሚቆየው የመጀመሪያው ጋብቻ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
በአንድ ወንድና ሴት መሃከል የሚደረግ ጋብቻ ፈርሶ እንደገና ካልተፈፀመ በቀር ጋብቻ አንድ እንጂ ሁለትና ከዚያ በላይ ላሆን አይችልም። በተያዘው ጉዲይ ግራ ቀኙ በኢትዮጵያ ውስጥ በባሕል ከተጋቡ በኋላ በድጋሚ በአውስትራሉያ ጋብቻ ማድረጋቸውን ከክርክር ሂደት ተገንዝበናል። በእርግጥ የሥር ፍ/ቤት እንዲለው አንድ ጊዜ ጋብቻ ከተመሰረተ ሁለተኛ ጋብቻ የሚፈፀምበት የሕግ መሰረት የለም። ተፈጽሞ እንኳን ቢገኝ ጋብቻው ውጤት የሚኖረው የመጀመሪያው ጋብቻ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ ነው። አንድ ጋብቻ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው የፍቺ ውሣኔ ሲሰጥ መሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 75/ሐ/ ያመለክታል። ጋብቻ አንድ እንደሆነ ሁለ ጋብቻው በፍቺ ሉፈርስ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ሁለት የጋብቻ ስርአቶች መከናወናቸውም ሁለት ጊዜ የፍቺ ውሣኔ እንዱሰጥ ምክንያት ላሆን አይችልም።
በመሰረቱ ፍቺ ማለት የሁለት ተጋቢዎችን የትዲር ግንኙት በሕግ መሰረት ማቋረጥ ማለት ነው። በመሆኑም ተጋቢዎቹ ግንኙታቸውን ማቋረጥ ከፈለጉ ጋብቻው በሁለት አይነት ስርአት ስለተፈፀመ ግንኙቱን ለማቋረጥ እያንዲንደን ጋብቻ አስመልክቶ የፍቺ ውሣኔ ላሰጥ የሚገባው አይሆንም። የሕጉም አላማ ይህ አይደለም። በተያዘው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤቶች ሁለተኛ ፍቺ ለመስጠት ምክንያት ያደረጉት በአውስትራሉያ የሚገኘው ፍ/ቤት ያፈረሰው ሁለተኛው እና በዛው አገር የተደረገውን ጋብቻ እንጂ በኢትዮጵያ የተደረገው ጋብቻን አይደለም። ሁለተኛው ጋብቻ ደግሞ አላስፈላጊና ውጤት የላለው ጋብቻ ነው በማለት ነው። በመሰረቱ ግራ ቀኙ ጋብቻቸውን መቀጠል ባለመፈለጋቸው ፍ/ቤት ቀርበው ጋብቻቸው በፍቺ እንዱፈርስ ጠይቀው አስወስነዋል። በግራ ቀኙ መሐከል የነበረው ጋብቻ አንድ ብቻ በመሆኑ አውስትራሉያ የተሰጠው የፍቺ ውሣኔ ይህን በመካከላቸው የነበረውን አንድ ጋብቻ እንደፈረሰ ተደርጎ ሉቆጠር ይገባል። ከላይ እንደተደገለፀው ግራ ቀኙ አውስትራሉያ አገር ከሄደ በኋላ ላላ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት መፈፀማቸው ሁለት ትይዩ /Parallel/ ትዲር ውስጥ ነበሩ ሉያሰኛቸው አይችልም። በመሆኑም በመካከላቸው የነበረው የጋብቻ ግንኙነት አንድ የመሆኑን ያሕል የሚፈርሰውም በአንድ የፍቺ ውሣኔ ነው። ለፍ/ቤቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ግራ ቀኙ አውስትራሉያ አገር ሄደው ሁለተኛ ሥነ-ሥርዓት በመፈፀማቸው ብቻ ሁለት የፍቺ ሥነ-ሥርዓት እንዱያከናውኑ ማድረጉ የቤተሰብ ሕግን አላማና መንፈስ የሚከተል አይደለም። ሁለተኛ ጊዜ የተደረገው ጋብቻ መፍረሱ ምናልባት በፍቺ ውጤት ላይ ክርክር የሚያስነሳ ካልሆነ በቀር የመጀመሪያው የጋብቻ ሥርዓት ባለመፍረሱ የግራ ቀኙ የጋብቻ ግንኙነት አልተቋረጠም ወደሚለው መደምደሚያ አይወስድም። ከላይ እንደተገለጸው ጋብቻው በሁለት አይነት ሥርዓት ተፈጽሞ ቢሆን እንኳን ጋብቻው በፍቺ ሉፈርስ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ እንጂ ሁለት የጋብቻ ሥርዓት በመፈፀሙ ሁለት አይነት ፍቺ ሉኖር አይችልም። ስለሆነም የመጀመሪያው ጋብቻ ሥርአት ሳይሆን ሁለተኛ የተደረገው ሥርዓት-በፍቺ መፍረሱ ተጋቢዎቹ እንደተፊቱ አያስቆጥርም በሚል ሁለተኛ የፍቺ ውሣኔ መስጠቱ የሕጉን አላማ የሳተና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካችና ተጠሪ አ/አበባ እና አውስትራሉያ ጋብቻ የፈፀሙ ቢሆንም ግራ ቀኙ የትዲር ግንኙነታቸውን በፍቺ ማቋረጥ ስለፈለጉ በአውስትራሉያ ፍርድ ቤት የፍቺ ውሣኔ አሰጥተዋል። ይህንንም ፍቺ ሁለቱም ተቀብለውት የራሳቸውን ሕይወት መኖር ቀጥለዋል። ተጠሪም ቢሆኑ የፍቺ ውጤት ውሣኔ እንዱሰጣቸው ለፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረባቸው በግራ ቀኙ መሃከል የነበረው ግንኙነት በፍቺ የተቋረጠ መሆኑን አምነው መቀበላቸውን ያሳያል።
ግንኙነቱ ከተቋጠ ደግሞ አ/አበባ የተደረገው ጋብቻ ለሁለተኛ ጊዜ በፍቺ ሉፈርስ ይገባል የሚባልበት የሕግ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም ከፍተኛ ፍ/ቤት አውስትራሉያ አገር በተደረገ የፍቺ ውሣኔ ሕልውና ያጣውን ጋብቻ ፍርድ ቤቱ ውሣኔ እስከሰጠበት ዔለት ድረስ እንደቀጠለ በማሰብ በ12/ዐ6/2ዐዐዐ ፈርሷል ማለቱ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ የፈረሰው የአውስትራሉያው ፍ/ቤት በመካከላቸው የመጨረሻ ውሣኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ላሆን ይገባዋል ብለናል። ከማኀደሩ ጋር ተያይዘው ከቀረቡት ሰነድች በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ የፈረሰው ሴፕቴምበር 2ዐ/2ዐዐ4 /መስከረም 1ዐ ቀን 1997 ዓ.ም/ መሆኑን ተረድተናል። በመካከላቸው የሚነሳ የንብረት ክርክር ካለም ይህን ቀን ታሳቢ ማድረግ አለበት ብለናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
በአመልካችና በመልስ ሰጪ መካከል የነበረው ጋብቻ ከመስከረም 1ዐ ቀን 1997 ዓ.ም. ጀምሮ ፈርሷል።
የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ከፍተኛው ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ይቀጥላል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.