No summary available.
ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ቴዎድሮስ መንበሩ ተጠሪ፡- ገ/ሕይወት ታደሰ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የውርስ ንብረት ይገባኛል በሚል የቀረበውን ክስ መሰረት በማድረግ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበረው አመልካች ነው። አመልካቹ በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው ከሟች እናቴ ድርሻ ላይ በውርስ የማገኘውን ንብረት አካፍለኝ በማለት ነው። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም የንብረቱ ግምት ለመሬት ልማት አስተዲደር የላኩለት መሆኑን በመግለጽ ከዚሁ ላይ አመልካች ድርሻውን 1/4ኛ ይሰጠው በማለት አዞአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ባለመስማማት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ እንደገና የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ንብረቱን እንደገና በመሬት ልማት አስተዲደር በማስገመት አመልካች ከዚሁ ላይ ድርሻውን ¼ኛ እንዱወስድ ወስኖአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መስከረም 5 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች ስምምነቱን ሳይገልጽ በባለሙያ የቀረበው የንብረቱ (ቤት) ዋጋ መነሻ ተደርጎ ከዋጋው ግምት ¼ኛው አመልካች ይውሰድ በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አመልካች በእናቱ በኩል የሚገኘውን የውርስ ድርሻ እንዱሰጠው ነው የጠየቀው። የውርስ ክፍያ የተጠየቀበት ሃብት የከተማ ቤት ሲሆን፣ ቤቱ የአመልካች እናት እና ተጠሪ በጋብቻ አብረው ሲኖሩ ያፈሩት የጋራ ሃብት እንደሆነ በክርክሩ ተገልጾአል። የአመልካች እናት ከተጠሪ ሦስት ልጆች እንደወለደና አመልካችን ግን ከላላ ሰው የወለደት እንደሆነ አመልካች አረጋግጦአል። በመሆኑም ለውርስ ክፍፍል የሚቀርበው ቤቱ እንዲለ በሙለ ሳይሆን፣ ተጠሪ ግማሽ ድርሻውን ካነሳ በኋላ በሚቀረው የቤቱ ግማሽ ላይ ነው። ይህም ከሟች በተወለደ አራቱ ልጆች መካከል የሚከፊፈል ነው። በዚህ ምክንያትም ነው የአመልካች የውርስ ድርሻ ¼ ነው የተባለው።
ከስር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር እንዲየነው አመልካች ተቃውሞ ያነሳው በቤቱ ግምት ላይ ብቻ ነው። በሰበር አቤቱታው ግን ድርሻዬን መውሰድ ያለብኝ ቤቱ በሐራጅ ተሽጦ ነው የሚል የመከራከሪያ ነጥብ አንስቶአል። ይሁንና ከፍ ሲል እንደተገለጸው ቤቱ የመኖሪያ ከመሆኑም በላይ፣ ግማሹ የተጠሪ የግማሽ ¾ኛው ደግሞ የላልቹ ሦስት ልጆች ስለሚሆን፣ የ1/4 ድርሻ ላለው አመልካች ሲባል ቤቱን በሐራጅ እንዱሸጥ በማድረግ ተጠሪና ልጆቹን ቤት አልባ ማድረግ የሚመረጥ አይደለም። ከፍትሕ አኳያ ሲታይም ተገቢ አይሆንም። በመሆኑም ቤቱ በሃራጅ ሉሸጥ ይገባል የሚለው የአመልካች ክርክር ከጅምሩም ቢሆን ያልተነሳ እና ከፍትሕ አንፃር ሲታይም ተቀባይነት ሉኖረው ስለማይገባ ውድቅ አድርገዋል። በልላ በኩል ግን በመሬት ልማት አስተዲደር ቀረበ የተባለው የቤቱ ግምት የገበያ ዋጋን መሰረት ያደረገ ሳይሆን፣ የግንባታ ዋጋን መሰረት በማድረግ የተሰላ በመሆኑ ይህን ግምት መሰረት ተደርጎ የሚፈጸመው የውርስ ሃብት ክፍፍል ፍትሐዊ ልባል ይችላል ወይ? የሚለውን ነጥብ ማየቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአከራካሪው ቤት ላይ አመልካችም መብት እንዲለው አላከራከረም። ከዚህ ንብረት ላይ የውርስ ድርሻውን ማግኘት አለበት ከተባለ ደግሞ በክፍፍል ወቅት ሉጠበቅ የሚገባውን ሁኔታ በጥንቃቄ የሚታይ ነው የሚሆነው።
የአመልካች እናት ድርሻ የሆነው የቤቱ ግማሽ በአራቱም ልጆች መካከል ሲከፊፈል አራቱም ልጆች እኩል ነው የሚታዩት በልላ አነጋገር ክፍፍለ የአራቱም ልጆች የእኩልነት መብት ያረጋገጠ መሆን ይገባዋል ማለት ነው። በመሆኑም የእኩልነት መብቱ የሚረጋገጠው ክፍፍለ በምን አይነት መንገድ ቢፈጸም ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ አስፈላጊ ይሆናል። ከላይ እንደተገለጸው አከራካሪው ቤት የተገመተው የገበያን ዋጋ (የወቅቱን የገበያ ዋጋ) መሰረት በማድረግ ሳይሆን የወቅቱን የግንባታ ዋጋ መሰረት በማድረግ ነው። የግንባታ ዋጋ ማለትም ቤቱን ለመስራት ለሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መግዣ የሚወጣው እና ለሰራተኞች የሚከፈለው ገንዘብ ብቻ የሚያጠቃልል ነው የሚሆነው። የገበያን ዋጋ ስንመለከት ግን ከዚህም ያለፈ እንደሆነ ነው መገንዘብ የሚቻለው። የገበያ ዋጋ ከስሙ እንደምንረዲው ቤቱ ለገበያ /ለሺያጭ/ ቢቀርብ የሚያስገኘውን ዋጋ ነው የሚያመለክተው። የገበያ ዋጋ ለመገመትም ቤቱ የሚገኝበትን አካባቢ፣ በወቅቱ ክፍፍለ በሚደረግበት ወቅት ያለውን የገበያ ሁኔታ ወዘተ በተጨማሪነት እግምት ውስጥ ይገባለ። ይህ ደግሞ የቤቱን የወቅቱ ዋጋ በማስላት ረገድ የግንባታን ዋጋ ከሚሰላበት ዘዳ የተሻለ /የሰፊ/ መሰረት ያለው አካሄድ ነው። ሲጠቃለል ንብረቱን የሚከፊፈለ ወገኖች የእኩልነት መብት በተሻለ ሁኔታ ማረጋገጥ የሚቻለው ንብረቱ(ቤቱ) በገበያ ዋጋ ግምቱ ቢሰላ ነው ለማለት ይቻላል። በመሆኑም በያዝነው ጉዲይ የግንባታን ዋጋ መሰረት በማድረግ ክፍፍለ እንዱፈጸም በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ./99 ጥር 23 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 0172/2000 በ3/13/2000 የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
አከራካሪው ቤት ለክፍፍል በሚቀርብበት ወቅት በሚኖረው የገበያ ዋጋ መሰረት ግምቱ ከቀረበ በኋላ አመልካች ድርሻውን ¼ኛ ይሰጠው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በሚመለከት ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
በዚህ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረት ይፈጸም ዘንድ ለሥር ፍ/ቤቶች ይጻፍ። መዝገቡ ይመለስ።