No summary available.
ሰኔ 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ዘውዳ ወኪል ጌታቸው ታደሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች መጋቢት 25 ቀን 1992 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ መስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ መኖሩን ገልፀው ይኸው ኑዛዜ በፍ/ቤት ፀድቆላቸው የኑዛዜ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዱሰጣቸው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ሲሆን፣ የአሁኑ ተጠሪዎችም በተቃዋሚነት ቀርበው አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ጥር 22 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ሟች መስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም እና ግንቦት 05 ቀን 1988 ዓ.ም ያደረጓቸው ኑዛዜዎች ሟች የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ የተሻሩና የተተኩ በመሆኑ ኑዛዜው ሉፀድቅ አይገባም በማለት የተከራከሩ ሲሆን፣ የአሁኑ ሦስተኛ ተጠሪ ግን መጋቢት 08 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አመልካች እንዱፀድቅላቸው የጠየቁት ኑዛዜ ቢፀድቅ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።
የስር ፍ/ቤትም ሟች ከመስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም በኋላ ሁለት የተለያዩ ኑዛዜዎች ማድረጋቸውን፤አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ደግሞ ሟች የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፀድቅላቸው ጥያቄ አቅርበው የአሁኗ አመልካች እና የአሁኑ ሦስተኛ ተጠሪ በተቃዋሚነት ቀርበው ይኸው ኑዛዜ በመ/ቁ. 1169 የካቲት 10 ቀን 1997 ዓ.ም በፍ/ቤቱ መጽደቁን፣ መስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም በተደረገው ኑዛዜ ሟች በወረዲ 3 ቀበላ 44 የቤት ቁጥር 220 የሆነውን ቤታቸውን ለወ/ሮ የውብዲር እና ለወ/ሮ አልማዝ ዘውዳ መስጠታቸውን፣ በሙከጡሪ ከተማ ያለውንም ቤት ወ/ሮ አልማዝ ዘውዳ በራሷ ገንዘብ የገዛችው መሆኑን ገልፀው ማንም እንዲይጠይቃት የተናዘዙ መሆኑን፣ ሆኖም እነዚህን ንብረቶች ወ/ሮ እቴቱ ዘውዳ እንዱወስደ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ መናዘዛቸውን ዘርዝሮ መስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም ተደረገ የተባለው ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 859/2/ መሰረት በሟች ተለውጧል፤ የሚል ምክንያት በመያዝ የአመልካችን የኑዛዜ ይጽደቅልኝ ጥያቄ ሣይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ውሣኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበውም ይኸው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ወኪል ጥር 04 ቀን 2000 ዓ.ም አሻሽለው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም ባጭሩ ሟች የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ በግልጽ ቀኑን ጭምር ጠቅሰው የሻሩት ግንቦት 05 ቀን 1988 ዓ.ም ያደረጉትን ብቻ እንጂ አስቀድሞ በ26/1/1984 ዓ.ም የተፃፈውን ኑዛዜ አለመሆኑን፤ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ሟች ኑዛዜ ሲያደርጉ የእድሜ ባለጠጋ እንደነበሩና ኑዛዜ ያደረጉበት ንብረትም የግላቸው ባልሆነው መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 865/2/ መሰረት ኑዛዜው ሉፈፀም የማይችል መሆኑን እንደሚያሣይ፤ አመልካች ከሟች ውርስ ያላግባብ መነቀላቸውን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ ሟች በ26/1/84 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ፀድቆ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች ቀርበው መልሣቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ጥቅምት 03 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት የመልስ ማመልከቻ ሟች አመልካችን ከውርስ በምክንያት የነቀሎቸው መሆኑን፤ ሟች ኑዛዜ ባደረጉበት ወቅት አእምሯቸው ጤነኛ እንደነበርና የአመልካች ቅሬታ በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን፤ ቤቱም በሟች የግል ገንዘብ የተገዛ መሆኑን፤ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም የተደረገውን ኑዛዜ የተቀበለት መሆኑን በኮ/መ/ቁ. 463 የተደረገው ክርክር እንደሚያሣይና ይኸው ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.895/3/ መሰረት ተቀባይነት ያለው መሆኑን በመዘርዘር የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ከበቂ ወጪና ኪሣራ ጋር ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ሦስተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ሟች አመልካችን ከውርስ የሚነቅለበት አንዲችም ምክንያት ሣይኖር መንቀላቸውና በአመልካች ስም የሚታወቀውን ቤታቸውን የሟች አስመስለው በኑዛዜ ለላላ አሣልፈው መስጠታቸው ያላግባብ መሆኑን በመዘርዘር የመስከረም 26 ቀን 1984 ዓ.ም ኑዛዜ ቢፀድቅ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ገለፀው ተከራክረዋል። አመልካች ኀዲር 05 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎችን መልስ በመንቀፍ፣የሦስተኛ ተጠሪን መልስ ደግሞ ተቀባይነት ያለው መሆኑን በመዘርዘር የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ በሙከጡሪ ከተማ 01 ቀበላ ይገኛል በተባለው ቁጥሩ 139 በሆነው ቤት አደረጉ የተባለው ኑዛዜ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ነው።
ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ መስከረም 26 ቀን 1984፣ ግንቦት 05 ቀን 1988 እና የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ኑዛዜ ማድረጋቸውን፤ በኑዛዜዎቹም የንብረቶችን ምንጭ ከዓይነታቸውና ብዛታቸው ጋር መግለፃቸውን፤ የውርስ ንብረቶቹ ሉተላለፈለት የሚገባውን ወራሽ፣ ለአሁኗ አመልካች ከውርስ ድርሻ ሣይሰጡ ያለፈበትን ምክንያት እንዱሁም በኋላኛው ኑዛዜ የትኛውን ኑዛዜ እንደሻሩ መጥቀሣቸውን፤ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ተደረገ የተባለው ኑዛዜ በፍ/ቤት መጽደቁንና ከዚህ በኋላም የአሁኗ አመልካች በ26/01/1984 ዓ.ም ተደረገ የተባለው ኑዛዜ እንዱጸድቅላቸው ለፍ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተገንዝበናል።
ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ የመጨረሻው ሲሆን በዚህ ኑዛዜ ለአመልካች የሰጡት የውርስ ድርሻ ካለመኖሩም በላይ ግንቦት 05 ቀን 1988 ዓ.ም ያደረጉትን ኑዛዜ በዚሁ በየካቲት 12 ቀን 1989 የሻሩት መሆኑን፤ ለአመልካች በሙከጡሪ ከተማ 01 ቀበላ ውስጥ የሚገኘውን ቤት የተናዘዙላት ቢሆንም አመልካቿ ልትንከባከባቸውና ልትጦራቸው ባለመቻሎና ከኑዛዜው በኋላ በቤቱ ውስጥ እንዲይኖሩ ያባረረቻቸው ከመሆኑም በላይ በቤት ውስጥ የነበራቸውን ሐብትና ንብረት ሁለ የእለት ልብስ ሣይቀራቸው ቀምታ በችግር ላይ እንዲለ በመግለጽ ያለፈ ስለመሆኑ የኑዛዜ መሻሪያ ሰነደ ያሣያል። እንግዱህ የየካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም ኑዛዜ አመልካች የክርክሩ ተካፊይ በሆኑበት ሂደት በፍ/ቤት የፀደቀ ከመሆኑም በላይ በሕግ ረገድ ፍርማሉቲውን ያልጠበቀ ነው ልባል የሚችል አይደለም። በመሆኑም ኑዛዜው ሕጋዊ ፍርማሉቲውን የጠበቀ መሆኑን ተገንዝበናል። ሕጋዊ ፍርማሉቲው አጠያየቂ ካልሆነ መታየት ያለበት የኑዛዜው ይዘት ነው። አመልካች የኑዛዜውን ይዘት በተመለከተ ያቀረቡት ክርክር ከውርስ የሚነቅላቸው መሆኑን በመጥቀስ ነው። በእርግጥ ሟቹ ለአመልካች በኑዛዜው የሰጧቸው የውርስ ድርሻ የለም። ይህንኑ ሉያደርጉ የቻለበትን ምክንያት በኑዛዜው መሻሪያ በግልጽ አስፍረዋል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 838/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች ስር እንደተመለከተው ተናዛዡ ልጆቹን ወይም ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆቹን ሲነቅል ከውርስ የነቀለበትን ምክንያት በግልጽ ማስፈር እንደሚገባውና ዳኞች የምክንያቱን እውነትነት በመያዝ ተናዛዡ ተወላጆቹን ለመንቀል የሰጠው ምክንያት ከውርስ ለመንቀል የሚያበቃ ነው ወይስ አይደለም በማለት ለመመርመር እንደሚችለ ተገልጿል። በመሆኑም ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ አመልካችን ከውርስ ሐብት ድርሻ እንዲያገኙ ያደረጉበት ምክንያት በኑዛዜው መሻሪያ ላይ በግልጽ የተቀመጠና ተወላጅን ለመንቀልም የሚያበቃ ምክንያት ሆኖ ስለተገኘ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ ባደረጉት ኑዛዜ በሙከጡሪ ከተማ 01 ቀበላ ውስጥ ይገኛል የተባለውንና ቁጥሩ 139 የሆነው ቤት ከአመልካች ውጪ ላለት ወራሾች እንደሚገባ ዘርዝረው የማከፊፈላቸውን ሕጋዊነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
865/2/ እና ተዛማጅነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በመሰረቱ ኑዛዜ በባህርይው ተራ የሐሣብ መግለጫ ቢሆንም በተናዛዡ በግለ ብቻ ሉፈፀም የሚገባው ተግባር ነው። ኑዛዜ በይዘቱ ንብረትን ከማስተላለፍ ተግባር ጋር የተያያዘ ሲሆን ህጋዊ ጥበቃ የሚደረገውም ተናዛዡ የራሱ የሆነውን ህጋዊ ንብረት ለማስተላለፍ ህጋዊ ኑዛዜ አድርጏ ሲገኝ ስለመሆኑ የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች ያሣያለ። ተናዛዡ ህጋዊ ንብረቱ ባልሆነው ላይ ኑዛዜ ቢያደርግና ይኸው ኑዛዜ በፍ/ቤት ቢፀጽቅ የኑዛዜ ሰነደ ዋጋ የሚያገኝበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስም ሟች ባደረጓቸው የተለያዩ ኑዛዜዎች ሙከጡሪ ከተማ ውስጥ ይገኛል የተባለውን ቤት በተመለከተ በማን ገንዘብና ለማን እንደተገዛ የተለያየ ሐሣብ እንደነበራቸው የኑዛዜ ሰነድቹ ያሣያለ። በ26/01/84 ዓ.ም ተደረገ በተባለው ኑዛዜ ቤቱ በአመልካች ገንዘብ መገዛቱን ጠቅሰዋል። በላልች የኑዛዜ ሰነድች ግን ቤቱ የተገዛው በሟች ገንዘብ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ በ02/01/84 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል በውጫላ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
G/F/4028/89 በቀን 07/04/90 ዓ.ም ተረጋግጧል። ቤቱን የገዙትም አመልካች ስለመሆናቸው ይኸው የፍ/ቤቱ ሰነድ ያሣያል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው በሙከጡሪ ከተማ ውስጥ ይገኛል የተባለው አከራካሪው ቤት ህጋዊ ባለቤት አመልካች እንጂ ተናዛዡ አለመሆናቸውን ነው። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ቤቱ የሟች ነው የሚለበት ምክንያት አመልካች በወቅቱ የነበራቸውን እድሜ መሰረት በማድረግ ገቢ ስላልነበራቸው ቤቱን ሉገዙ አይችለም በሚል ነው።
ሆኖም ምክንያታቸው ህጋዊ ተቀባይነት የላለው ነው። በመሆኑም አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ ያደረጉት የኑዛዜ ሰነድ ዋጋ ሉሰጠው የሚገባው ሆኖ ስላልተገኘ በዚህ ረገድ ኑዛዜው የፀደቀበት አግባብ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 01183 የካቲት 03 ቀን 1997 ዓ.ም ተሰጠቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 38849 ግንቦት 09 ቀን 1999 ዓ.ም የፀናውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አሻሽለናል።
ሟች ባላምባራስ ዘውዳ ደምሴ በሙከጡሪ ከተማ 01 ቀበላ ውስጥ በሚገኘው ቁጥሩ 139 በሆነው ቤት ላይ ያደረጉት ኑዛዜ ፈራሽ ነው፤ቤቱን አመልካች የገዙት በመሆኑ የግል ንብረታቸው ነው ብለናል።
አመልካች ከሟች ውርስ ያላግባብ ተነቅያለሁ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።