No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ አቶ ዓብደልዋሲቅ አርጋው - ጠበቃ ተስፊዬ ተገኘወርቅ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለውያ አባበሉስ - ወኪል ኑርአዱስ አርጋው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ህግን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በውርስ ማጣራት ሂደት ነው። የውርስ ማጣራቱን ሥራ የውርስ አጣሪው እንዱያከናውንና ሪፖርቱን ለፍ/ቤቱ እንዱያቀርብ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ተሰጥቶ የውርስ አጣሪው የሟች አቶ አራጋው ከድር የውርስ ንብረት አጣርቶ ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ ሪፖርት ለፍ/ቤቱ አቅርቦ ሪፖርቱ በፍ/ቤቱ ፀድቆ ተመዝግቧል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የሪፖርቱ ክፍል ደግሞ የውርስ አጣሪው በአ/ከ/ክ/ከተማ ቀበላ 02 የቤት ቁጥር 270 የሆነ የንግድ ሱቅ ድርጅት ተጠሪ ከመንግስት በ1986 ዓ.ም የተከራዩት ነው እንጂ ከሟች አቶ አራጋው ከድር ጋር በጋራ የተከራዩት ንብረት አይደለም በማለት ያቀረበው ነጥብ በፍ/ቤት መፅደቁ ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
አመልካቾች የበታች ፍ/ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚለበትን ምክንያት ጥር 05 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 5/አምስት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ አመልካቾች ክርክራችን ለማስረዲት ያቀረብናቸው ማስረጃዎች ሣይሰሙ ውሣኔ መስጠቱ ያላግባብ ስለሆነ የበታች ፍ/ቤቶች ትዛዞች ተሽረው ማስረጃዎቻችን ተሰምተው ተገቢው ውሣኔ እንዱሰጠን ይደረግልን የሚል ነው። የአመልካቾች አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ሚያዝያ 03 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 4/አራት/ ገፅ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ የስር ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ ውሣኔ የሰጡት ማጣራት አድርገውና ከህጉ ጋር አገናዝበው በመሆኑ ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለበትም ተብል ከውጪና ኪሣራ ጋር ሉፀና ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አመልካቾች በበኩላቸው የተጠሪ መልስ የሱቅ ድርጅቱ የተገኘበትን ህጋዊ መንገድ የማይገልፅ እና ተቀባይነት የላለው በመሆኑ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ሚያዝያ 28 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት የመልስ መልስ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የገለፀው ሲሆን ችልቱም የግራ ቀኙን የፁሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም ለክርክሩ መነሻ የሆነው የሱቅ ድርጅት በአመልካቾች የተቆጠሩት የሰው ምስክሮች ሣይሰሙ የተጠሪ የግል ንብረት ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች የሱቅ ድርጅቱ የንብረት ድርሻ ጥያቄ ያቀረቡት አውራሽ የሆኑት ሟች አባታቸው አቶ አራጋው ከድር የንግድ ድርጅት ነበር በማለት መሆናቸውን፣ የንግድ ድርጅቱ ወደ ተጠሪ የተላለፈው ተጠሪ የአመልካቾች ሞግዚትና ንብረት አስተዲዲሪ የነበሩ በመሆኑና ይህንንም በሰውና በሰነድ ማስረጃ ለማረጋገጥ አቤቱታ ማቅረባቸውን ቀድሞ የነበረው የሱቅ ንግድ ድርጅት በእሣት ቃጠል በ1980 ዓ.ም ወድሞም በተቃጠለው ሱቅ ምትክ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የንግድ ሱቅ ተጠሪ በዔጣ የወሰደ መሆኑንና ይህም ላሆን የቻለው ተጠሪ በወቅቱ በአቀረቡት የሞግዚትነትና የሚስትነት የፍርድ ውሣኔ መነሻ ስለመሆኑ አመልካቾች ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን ነው።
ተጠሪ በበኩላቸው ሱቁ የግል ንብረታቸው መሆኑ በአግባቡ ተጣርቶ መወሰኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል። እንዱሁም የውርስ አጣሪው ለክርክሩ መነሻ የሆነው የሱቅ ድርጅት ማህደር ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ቀርበው በመመልከት የቤት ቁጥር 270 የሆነው የሱቅ ድርጅት ከመንግስት የተከራዩት ተጠሪ ወ/ሮ አለውያ አባቢለስ መሆናቸውን፣ ጊዜውም በ1986 ዓ.ም ሟች አቶ አራጋው ከድር ከሞቱ ከሰባት ዓመት በኋላ መሆኑን ጠቅሰው ለስር ፍ/ቤት የውርስ ማጣራት ሪፖርቱን ማቅረባቸውን ተረድተናል።
በመሰረቱ የውርስ ማጣራት ስራ ተገቢው ሥርዓት ተጠብቆ የወራሾች ክርክርና ማስረጃ ተሰብስቦና ታይቶ የሚከናወን ስራ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 942 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የውርስ ማጣራት ስራ እንዱከናወን ትዕዛዝ የሰጠው ፍ/ቤትም የአጣሪውን ሪፖርት የሚያፀድቀው የማጣራቱ ተግባር በህጉ አግባብ መከናወኑን ከአረጋገጠ በኋላ ነው።
በተያዘው ጉዲይ የውርስ ማጣራቱ ስራ የተከናወነው በፍ/ብ/ህ/ቁ 950(1) መሰረት በፍ/ቤት በተሾመ አጣሪ ሁኖ አጣሪው ስራውን ያከናወኑት ግራ ቀኙ ወገኖች ባለበትና ተገቢው የማስረጃ ማሰባሰብ ስራ አከናውኜአለሁ ካለ በኋላ ነው። ይሁን እንጂ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ሱቅ በተመለከተ በአመልካቾች በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች ያልተሰሙበትን ምክንያት የውርስ አጣሪውም ሆነ የአጣሪውን ሪፖርት ያፀደቀው ፍ/ቤት በግልፅ አላስቀመጡትም። በአንድ ተከራካሪ ወገን የተቆጠረ ማስረጃ የማይሰማው ደግሞ ህጋዊ ምክንያት ሲኖር ብቻ ነው። የአመልካቾች ማስረጃዎች በውርስ አጣሪው ያልተሰሙት በህጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ አልተገለፀም። የአመልካቾች ክርክር በአባታቸው ስም ይታወቅ የነበረ ቁጥሩ 398 የሆነ የሱቅ ድርጅት እንደነበር፣ ይህ ሱቅ በቃጠል መውደሙንና በምትክ ደግሞ አሁን ክርክር ያስነሣውን ሱቅ ቁጥሩ 270 የሆነውን ተጠሪ ከመንግስት መረከባቸውን የሚያሣይና ይህንንም ፍሬ ጉዲይ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ስለመቆጠራቸው የሚያሣይ ነው። ለክርክሩ መነሻ የሆነው ሱቅ የተያዘበት መንገድ ከላይ የተገለፀው ስለመሆኑ አመልካቾች እየጠቀሡ የሱቁን ማህደር ብቻ በመመልከት ፍትሐዊ ወደሆነው ውሣኔ ለመድረስ አይቻልም። የውርስ አጣሪው የአመልካቾችን ማስረጃዎች አለመሰማቱ የማጣራቱን ሂደት የተሟላ ነበር ለማለት የማያስችል፣ የአመልካቾችን የመከራከር መብት ያጣበበ ሆኖ ተገኝቷል። የውርስ አጣሪውን ሪፖርት ያፀደቀው ፍ/ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤት የአመልካቾችን የማስረጃ ማሰማት መብታቸውን ሣያስተካክለ ማለፊቸው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 241 እስከ 270 እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 345 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ተሽሮ የአመልካቾች ማስረጃዎች ተሰምተው ተገቢ ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ለስር ፍ/ቤት ጉዲዩን መመለሱ አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 19 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ ታኅሣስ 23 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2/ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በአመልካቾች የተቆጠሩትን ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
3/ በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።