No summary available.
ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሆኖ ተጠሪዎች ከሳሾች ሲሆኑ አመልካቾች ተከሳሾች ነበሩ። ክሱም የሟች ብርሃኑ ጫላና የእኔ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት የሞግዚት አድራጊዎቼ የውርስ ንብረት የሆነውን በወረዲ 25 ቀበላ 01 ቁጥሩ 714 የሆነውን መኖሪያ ቤት ከሕግ ውጪ የያዙበት ውል ፈራሽ ሆኖ ቤቱን እንዱያስረክቡ ይወሰንልን የሚል ነው።
አመልካቾችም የባልና ሚስት የጋራ ሀብት መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረቡም። ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ ኖረው አያውቁም፣ ሚስት ወ/ሮ ዘቢደር አናውጤ እንጅ ከሳሽ አይደለም ተጠቃሹ ቤት ወ/ሮ ገነት መኮንን ጋብቻ መሰረትን ከሚለት ከ1973 ዓ.ም በፉት አቶ ብርሃኑ ጫላና ባለቤታቸው ወ/ሮ ዘቢደር አናውጤ 1966 ዓ.ም የገዙት ለመሆኑ ማስረጃ አለ። ስለዚህ በፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) መሰረት ለመክሰስ ስለማይችለ ክሱ ይሰረዝ በማለት መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ8/2/2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ወ/ሮ ገነት መኮንን የሟች አቶ ብርሃኑ ጫላ ሚስት መሆናቸው በፍ/ቤት በመ/ ከተወሰነ በኋላ ወ/ሮ ዘብይደሩ አናውጤ ተቃዋሚ ሆነው ገብተው ተከራክረው ፍ/ቤቱ ወ/ሮ ገነትን ሚስትነት ስላፀናው ይግባኝ ቀርቦ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ ላይ በ30/5/98 ዓ.ም በዋለው ችልት የወ/ሮ ዘቢደሩ ምሥክሮች ተሰምተው እንደገና በመቃወሚያ አቤቱታው ላይ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን ለታች ፍ/ቤት የላከው ሲሆን ወ/ሮ ዘብይደሩ በክርክሩ ሳይቀጥለ ቀርተዋል። በመሆኑም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ወ/ሮ ገነት መኮንን የሟች ብርሃኑ ጫላ ሚስት ናቸው፤ሟች ወ/ሮ ገነት እና ሟች አቶ ብርሃኑ ሲጋቡ በ6-10-73 ዓ.ም ባደረጉት የጋብቻ ውል ላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የጋራ እንዱሆን ብለዋል። የእሳቸው ድርሻ ላይ ፈቃድ ሳይጠየቅ የተደረገ ውል ሉሰረዝ ይገባል በማለት የሽያጩ ውል ተሰርዞ ቤቱን ያስረክቡ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ በሆነው መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ጠበቃ ቀረቡ በሚስትነት ዙሪያ ያለው ክርክር ሁለቱም ተከራካሪዎች በሕይወት የላለ በመሆኑ አመልካቾች ወ/ሮ ገነት ሚስት አይደለም፣ ወ/ሮ ዘቢደር ሚስት ናቸው የሚል ክርክር የሕግ መሰረት የለም። ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1723 መሰረት በሕግ ፉት የሚፀና አይደለም በማለት ውሳኔውን በማጽናቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካቾች ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ያቀረቡት ቅሬታ፡-
ተጠሪዎች የሟች ብርሃኑ ጫላ ልጆችና ወራሾች መሆናቸው እና የወ/ሮ ገነት መኮንን ሚስትነት የተረጋገጠበት ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ተሰርዞ ጉዲዩ እንደገና ታይቶ እንዱወሰን ተብል የታዘዘ ቢሆንም ለሥር ፍ/ቤት እንዱያቀርቡ የታዘዘውን ማስረጃዎች ሳያቀርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው በሕግ ፉት የሚፀና የሚስትነት ውሳኔ አልተሰጠም።
ተጠሪዎችም የሟች ብርሃኑ ጫላ ልጆች ብልም ሕጋዊ ወራሾች መሆን የሚመሰረተው ሟች እናታቸው የሟች አቶ ብርሃኑ ጫላ ሚስት ናቸው ከሚል ከተረጋገጠ ፍሬነገር በመነሳትና በጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጆች አባት የእናታቸው ባል ነው በሚለው የሕግ ግምት መሰረት ነው። ሆኖም የእናታቸው ሚስትነት ሳይረጋገጥ የተጠሪዎች ወራሽነት ተረጋግጧል ለማለት ስለማይቻል የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል በማለት ውሳኔው እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።
ቅሬታውን መሰረት በማድረግ የተጠሪዎች እናት የሟች አቶ ብርሃኑ ጫላ ሚስት መሆናቸውና የተጠሪዎች ወራሽነት አልተረጋገጠም እየተባለ ለክርክሩ መንስኤ የሆነው ቤት ያለተጠሪዎች እናት ፈቃድ በሟች የተሸጠው በሕግ አግባብ አይደለም፣ ውለም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1723 ላይ የተቀመጠውን መስፈርት አያሟለም ተብል አመልካቾች ቤቱን ያስረክቡ የመባለን አግባብነት ለመመርመር ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ታዞ ግራ ቀኙ በዚህ ፍ/ቤት የጽሐፍና የቃል ክርክር አካሂደዋል። በተጠሪዎች በኩል የቀረበው ክርክር በአጭሩ በምሥክሮች መስማት ረገድ ለወ/ሮ ዘቢደር መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቁ አጋጣሚ ስለሚፈጠር ምስክሮች ቃል ይሰማ ተብል የተሰጠውን ውሳኔ አመልካቾች መከራከሪያ ሉያደርጉ አይችለም። እንደገና እንዱታይ መመለስ የመክሰስ መብትንና ጥቅምን አያሳጣም። በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የጋብቻ ውል ላይ ተለይቶ የተሰጠ ውሳኔ የለም በማለት ውሳኔው እንዱፀና ተከራክረዋል።
No topics extracted.
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር እንደሚከተለው መርምረናል።
በቀዲሚነት ላታይ የሚገባው የሕግ ነጥብ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ጉዲዩን መጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት እንደገና መልሶ እንዱያይ ጭብጥ ይዞ መመለስ የቀድሞውን ውሳኔ የመሻር ውጤት ይኖረዋል ወይንስ አይኖረውም? የሚለው ነጥብ መታየት የሚገባ ነው። የተጠሪዎች ክርክር በጥቅለ ሲታይ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ ቢመለስም የሚስትነትን ውሳኔ አልሻረውም የሚል ነው። የአመልካቾች ክርክር ደግሞ የቀድሞ ሚስትነት ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ክርክር ተካሂድ ውሳኔው ተሰርዞ ጉዲዩ እንደገና ታይቶና ማስረጃ ተሰምቶ እንዱወሰን በተባለው መሰረት እንዱያቀርቡ የታዘዙትን ምስክሮች ሳያቀርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው በሕግ ፉት የሚፀና የሚስትነት ውሳኔ የለም በማለት ነው።
እንግዱህ አንድ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ክርክር ተሰምቶ ጉዲዩ እንደገና መጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት መልሶ እንዱያየው ከተደረገ የቀድሞ ውሳኔ እንዲልተወሰነ ወይም በውሳኔው የተገኘው መብት እንደላለ ወይም እንደተሻረ የሚቆጠር ነው። በተያዘው ጉዲይ የተጠሪዎች እናት ሚስት ናቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ ማስረጃ ተሰምቶ እንዱወሰን ታች ወደ ወሰነው ፍ/ቤት ተመልሷል። በተመለሰው ውሳኔ መሰረት ክርክር ሳይደረግና የተባለው ምሥክሮች ክርክርም ሳይካሄድ የሚስትነታቸው ጉዲይ በእንጥልጥል ላይ ቀርቷል። በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች እናት ሞግዚትነት የተገኘው የሟች ሚስት ነበሩ ልጆችም የተወለደት ከሚስትነታቸው ነው ተብል በፍ/ቤት በተረጋገጠው ውሳኔ መሰረት ነው። ይህ ውሳኔ ደግሞ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንዲልተወሰነ ተደርጏ እንደገና ምሥክሮች ተሰምቶ እንዱወሰን ከተደረገና ክርክር ተካሂድበት ውሳኔ ካልተሰጠ በስተቀር በእንጥልጥል ላይ ያለ ጉዲይ ከሚሆን በስተቀር በሕግ ፉት የሚፀና ሚስትነትን የሚያረጋግጥ ውሳኔ አለ ለማለት አይቻልም። የጽሐፍ የጋብቻ ውልን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለይቶ አልወሰነውም የሚለውን ክርክር በተመለከተ የውሳኔው ይዘት ሲታይ በጽሐፍ ውል ላይ ብቻ ተንተርሶ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ያለአግባብ በመሆኑ የምሥክሮች ቃል በመስማት እንዱወሰን መባለ የጽሐፍና የሰው ማስረጃዎች ሁለቱም ተመዝኖ ሉወሰን የሚገባ መሆኑን የሚያመለክት እንጅ ውለን አልነካውም የሚያስብል የሕግ መሰረት አይኖርም። የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው በከፍተኛ ፍ/ቤት የሚስትነት ውሳኔ አልተሻረም በማለት ነው። ለሽያጩም ውል መፍረስ ምክንያት የሆነው ያለሚስት ፈቃድ የተደረገው የሽያጭ ውል ሉሰረዝ ይገባል በማለት የውሳኔው መሰረት ሚስትነት ነው። የሚስትነት ውሳኔ አልተሻረም የተባለው ውሳኔ ከፍ ሲል እንደተመለከተው እንዲልተወሰነ ወይም እንደላለ የሚቆጠር ውሳኔ ነው። ውሳኔው እንደላለ ወይም እንዲልተወሰነ የሚቆጠር ከሆነ ደግሞ ከዚህ የሚመነጭ መብትም ሆነ ጥቅም ሉኖር አይችልም። የሽያጩ ውል እንዱሰረዝ ለመቃወም መብት የተገኘው ከሚስትነት ነው። ሚስትነት ከላለ ደግሞ መቃወሚያ ማቅረብ አይቻልም። በመሆኑም አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) መሰረት ተጠሪዎች የመክሰስ መብት የላቸውም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ፍ/ቤቱ ባለመቀበል የሰጠው ውሳኔ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ማረም ሲገባው በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ8/2/2000 ዓ.ም እንዱሁም የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል። የፃፍ።
ተጠሪዎች የመክሰስ መብት የላቸውም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡን ዘግተናል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።