No summary available.
ሚያዝያ 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የወ/ሮ ገነት ዲምጤ ወራሾች - ጠበቃ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- እነ አቶ ይስማ አስፊው - ጠበቃ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የውርስ ሀብት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 11 ቀበላ 17 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 847 የሆነውን ቤት ጥቅምት 19 ቀን 1962 ዓ.ም. ሟች ወ/ሮ ተካበች ሀብተወልድ ባደረጉት ኑዛዜ ለከሣሾችና የተከሣሽ ባለቤት ለሆነው ወንድማችን ሰጥተዋል። ከዚህ በተጨማሪም አውራሻችን ወ/ሮ ተካበች ሀብተወልድ በባንክ ያስቀመጡትን ብር 4,666(አራት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት) ወንድማችንና የተከሳሽ ባለቤት የሆኑት ወስደው አላካፈለንም።
ስለዚህ ተከሣሽ ከላይ የተጠቀሰውን ቤትና አብረውት ያለትን ቤቶች እንደዚሁም ከገንዘቡ እንዱያካፍለን ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽ /የአሁን አመልካቾች አውራሽ/ ቀርበው በሰጡት መልስ ከሳሾች አውራሻችን የሚሎቸው ወ/ሮ ተካበች ሀብተወልድ ከሞቱ በኋላ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1ዐዐዐ ላይ እንደተቀመጠው በ3 ዓመት ጊዜ የውርስ ሀብት ይገባናል በማለት ጥያቄ ያላቀረቡ ስለሆነ አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ለፍሬ ጉዲዩም ሙለ መልስ ሰጥተዋል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤትም የይርጋ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም ካለ በኋላ ክስ የቀረበበት ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት ስለሆነ 2/3ኛውን ከሣሾች ቀሪውን 1/3 ደግሞ ተከሣሽ እንዱወስደ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሽ በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት ይግባኙን ባለመቀበል ውሣኔውን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ በሥር ፍ/ቤት በአመልካቾች አውራሽ በኩል የተነሳው የይርጋ መቃወሚያ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተጠሪዎች ባለበት ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከክርክሩ መገንዘብ እንደተቻለው ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት ተጠሪዎች ሟች ወ/ሮ ተካበች ሀ/ወልድ በኑዛዜ ሰጥተውናል የሚለት በ1962 ዓ.ም. ሲሆን ወ/ሮ ተካበች ሀ/ወልድ ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ1968 ዓ.ም.
ነው። የውርስ ንብረቱ ድርሻችንን የአመልካቾች አውራሽ ሉያካፍለን ይገባል በማለት ክስ የመሰረቱት በ1994 ዓ.ም.
ነው።
በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የአመልካቾች አውራሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1ዐዐዐ ላይ የተመለከተውን በመጥቀስ ነው። የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ እንዲሰፈረው አንድ እውነተኛ የሆነ ወራሽ ትክክለኛው ወራሽ መሆኑ ታውቆለት ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው የውርሱን ንብረት በእጁ ያደረገው ሰው የውርሱን ንብረት እንዱለቅ ክስ በሚያቀርብበት ጊዜ ነው። ነገር ግን በተያዘው ጉዲይ በአመልካቾች አውራሽ ላይ ክስ ቀርቦ የነበረው ምንም ዓይነት መብት ሳይኖራቸው ይዘውት የሚገኘውን የውርስ ሀብት ድርሻችንን ትልቀቅልን በማለት ስለሆነ የተጠቀሰው ድንጋጌ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት አይኖረውም።
ተጠሪዎች በዚህ መልኩ ያቀረቡት አቤቱታ በምን ያሕል ጊዜ መቅረብ እንዲለበት በውርስ ሕጉ ላይ አልተመለከተም። የውርስ ሕጉ በዚህ ረገድ ክፍተት ካለበት ወደ ጠቅላላ ሕግ በመሄድ ለጉዲዩ እልባት መስጠት በሕግ አተረጓጎም መርህ /principles of legal interpretation/ የተፈቀደ ነው። በዚሁ መሰረትም ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሕጉ ጠቅላላ ስለውልች ከተደነገገው አንፃር ተመልክተነዋል። በዚህ ክፍልም ግዳታዎች ከውል የተገኙ ባይሆንም በውል ሕግ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት እንዲላቸው በቁጥር 1677/1/ ላይ ተመልክቷል። በውል ሕግ ደግሞ ዋናው የይርጋ ድንጋጌ በቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የ1ዐ ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎች በውርስ የተላለፈልንን ድርሻ ንብረታችንን ሉለቁልን ይገባል በማለት በአመልካቾች አውራሽ ላይ ክስ የመሰረቱት ከላይ እንደተመለከተው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን ኑዛዜውን አድርገዋል የተባለት ግለሰብ በሞት የተለዩት ደግሞ በ1968 ዓ.ም. ነው። ኑዛዜው ከሟች ሞት በኋላ ውጤት የሚኖረው እንደመሆኑ መጠን ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በ1ዐ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠሪዎች አቤቱታውን ማቅረብ ሲገባቸው ከ26 ዓመት በኋላ ጥያቄውን ማቅረባቸው በይርጋ የማይታገድበት ምክንያት አይኖርም።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1ዐዐዐ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት አይኖረውም ማለታቸው ተገቢ ቢሆንም ነገር ግን ከ26 ዓመት በኋላ የቀረበን የውርስ ንብረት ክፍያ ጥያቄ ከጠቅላላ ሕግ አኳያ በይርጋ የታገደ ሆኖ ሳለ ከዚህ አንፃር የይርጋ ክርክሩን ሳይመለከቱት መቅረታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 18669 በ24/ዐ1/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ21/9/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብል ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.