No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ዱያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ወንድም ሲያምረኝ - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ የሺ ተፈሪ (2 ሰዎች) - ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በዚህ ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ አንደኛ ተጠሪ ናቸው። በክሣቸው ከአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪ ጋር ባልና ሚስት ሆነው በጋራ የሰሩት የእሣቸው ፈቃድ ሣይኖር ሁለተኛ ተጠሪ ለአመልካች መስጠታቸውን በመግለጽ የሽያጩ ውል ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ጋር የሚቃረንና ሕጉ የሚጠይቀውን ፍርማሉቲ ያልተከተለ በመሆኑ ፈራሽ ነው እንዱባልላቸው ጠይቀዋል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም የሽያጭ ውለ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723(1) መሰረት በህግ የሚጠይቀውን የአፃፃፍ ስርአት አልተከተለም በማለት ውለ እንዱፈረስ ውሣኔ ሰጠ። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ መልስ ሰጪን መጥራት ሣያስፈልግ ይግባኙን ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሣኔ በመቃወም ነው። የአመልካች ዋነኛ ቅሬታ የስር ከሣሽ ያቀረቡት ክስ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አ/ቁ. 213/92 አንቀጽ 69/2/ መሰረት በይርጋ የታገደ ነው የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ ይገባል በማለቱ ተጠሪዎች ቀርበው ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብ ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው በስር ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት አንደኛ ተጠሪ ክስ ያቀረቡት ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት የጋራ ቤታቸውን ሁለተኛ ተጠሪ ያለ እሳቸው ፈቃድ ለአመልካች ከመሸጣቸውም በላይ ውለ በሕግ የተመለከተውን የአፃፃፍ ስርአት ስለማያሟላ እንዱፈርስላቸው ነው። አመልካች የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል የሚልና ላላም መቃወሚያ እንዱሁም ለዋናው ጉዲይ በአማራጭ ሙለ መልስ ሰጥተዋል። በመሆኑም አመልካች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ በቅድሚያ ላታይ ይገባል።
ከመዝገቡ ላይ በአመልካችና በሁለተኛ ተጠሪ መሐከል የሽያጭ ውል የተደረገው ኀዲር 1 ቀን 1995 መሆኑና የስር ከሣሽ ወይም የአሁኗ አንደኛ ተጠሪ ክስ የመሰረቱት በ09/08/1999 ዓ.ም መሆኑን ተረድተናል። አንደኛ ተጠሪ ክሱን የተቃወሙት ውል የተደረገበት ቤት ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር ያፈሩት የጋራ ንብረት በመሆኑ ነው። በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 68 ፉደል “ሀ” ስር የጋራ የሆነውን የማይንቀሣቀስ ንብረት ለመሸጥ የሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት አስፈላጊ ነው። ይህ ስምምነት ሣይኖር የተደረገ ሽያጭ ውጤቱ ምን እንደሆነ በዚህ ህግ አንቀጽ 69 ስር ተቀምጧል አንደኛው ተጋቢ በልላኛው ተጋቢ ስምምነት ሣይኖር የጋራ የሆነውን የማይንቀሣቀስ ንብረት የሸጠ እንደሆነ ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ ውለ እንዱፈርስ ሲጠይቅ እንደሚችልና ፍ/ቤቱ ውለን ማፍረስ እንደሚችል ተገልጾአል።
በተያዘው ጉዲይ አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ በጋብቻ ጊዜ ያፈሩት የጋራ ቤት የአንደኛ ተጠሪ ፈቃድ ሣይኖር ተሸጦ ከሆነ ተጠሪዋ ውለ እንዱፈረስ ጥያቄ ሉያቀርቡ ይችላለ። በልላ በኩል ግን ግዳታው እንዱፈርስ የሚቀርበው ጥያቄ ጠያቂው ወገን ግዳታው መገባቱን ከአወቀበት ቀን ጀምሮ ከ6 ወር በኋላ በልላ በማናቸውም ሁኔታ ግዳታው ከተገባ ከሁለት ዓመት በኋላ ላቀርብ እንደማይችል በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2/ ስር ተደንግጓል። ከፍ ሲል እንደተገለፀው በሁለተኛ ተጠሪና በአመልካች መሐከል የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው 01/03/95 ሲሆን አንደኛ ተጠሪ ክስ ያቀረቡት ደግሞ በ09/08/99 ከአራት አመት በኋላ ነው። የስር ፍ/ቤት የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረገው የስር አንደኛ ተከሣሽ ከሣሽ በሆኑበት መዝገብ አንደኛ ተጠሪ ተከሣሽ ሆነው ቀርበው ተከራክረው ከተወሰነ በኋላ ፍ/ቤቱ የአንደኛ ተጠሪን ክስ የማቅረብ መብት የጠበቀላቸው በመሆኑና ይህም ውሣኔ ከተሰጠ ጀምሮ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ክሱ በመቅረቡ ይርጋው ተቀባይነት የለውም በማለት ነው። አንድ ክስ ለማቅረብ በህጉ የተመለከተው በይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክስ ማቅረብ የማይቻል ቢሆንም ነገር ግን አሁንም ህጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ምክንያቶች የይርጋው ጊዜ ሉቋረጥ እንደሚችልና አዱስ የይርጋ ዘመን መቆጠር እንደሚጀምር የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1852/1/ ያመለክታል። ወይም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1853 ስር የተመለከተው ሁኔታ ሲያጋጥም ፍ/ቤቱ የይርጋን መቃወሚያ አልቀበልም ለማለት ይችላል። ይርጋ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች የሚባለት የባለእዲው እዲው ማመኑ፣ ወለድ ወይም ከእዲው ላይ ከፉለን መክፈለ፣ መያዣ ወይም ዋስ መስጠቱ ወይም ደግሞ ባለገንዘቡ መብቱ እንዱታወቅለት በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ባለእዲውን ማሣወቁ መሆናቸው ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851(1)(2) መረዲት ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ የሽያጭ ውለ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አንደኛ ተጠሪ ክስ እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስ 4 አመት ያለፈው በመሆኑ ክሣቸው በተሻሻለው ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69/2/ መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል። በዚህ አራት አመት ውስጥ ይርጋውን የሚያቋርጡ ሁኔታዎች (በህጉ በተመለከቱት አይነት) ስለማጋጠማቸው የቀረበ ነገር የለም። ፍ/ቤቱ በጠቀሰው መዝገብ ላይ የአንደኛ ተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት ያላቸው መሆኑ መገለጽ የይርጋውን ጊዜ ለማቋረጥ የሚበቃ ምክንያት አይሆንም። በልላ በኩል በተጠቀሰው መዝገብ አንደኛ ተጠሪ ተከሣሽ እንጂ ከሣሽ ለመሆናቸው መብታቸው እንዱታወቅላቸው በፍ/ቤት ክስ አቅርበዋል ልባል የሚችለ ባለመሆናቸው በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851/ለ/ መሰረት የይርጋው ጊዜ ተቋርጧል ለማለት አይቻልም። በመሆኑም ውለ ከተደረገ ከ4 አመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ ሉቋረጥ ሲገባ የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ማደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት ብለናል።
ው ሣ ኔ
44809 በ27/11/99 የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የከሣሽ የዲኝነት ጥያቄ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቁጥር 69/2/ መሰረት በይርጋ ይቋረጣል ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.