No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ ለገሰ ቢራቱ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ደረጀ ጅማ ገርግሶ - ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ የቀረበው የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ጉዲይ ነው። ጉዲዩ የጀመረው በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።
የአሁኑ ተጠሪ አባት አቶ ጅማ ጌርጏሶ አመልካች ላይ በነበረባቸው እዲ ምክንያት እሣቸው በመሞታቸው ተጠሪን ጨምሮ በሟች ባለቤትና ወራሾች ላይ ክስ ተመስርቶ ተፈርድባቸዋል። ይህንንም ፍርድ ለማስፈፀም አመልካች በባለእዲዎቹ ላይ የአፈፃፀም ክስ አቅርበዋል። ለውሣኔው ማስፈጸሚያም እንዱሆን አሁን ክርክር የተነሣበት ቤት በ25/04/98 በተደረገ ጨረታ በብር 38,200 (ሰላሣ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ብር) አሸናፉ የተገኘ ቢሆንም አሸናፉው ገንዘቡን ባለመክፈላቸው አመልካች ቤቱ በድጋሚ ጨረታ እንዱሸጥ አመልክተዋል። በዚህን ጊዜ የአሁኑ ተጠሪ በ28/04/98 በተፃፈ አቤቱታ በሐራጅ እንዱሸጥ የታዘዘው ቤት የግል ቤታቸው በመሆኑ ጨረታው እንዱቆም ሲለ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት መቃወሚያ አቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም የተጠሪን ጥያቄ መርምሮ ተጠሪ አቤቱታውን ያቀረቡት ቤቱ በጨረታ በ25/04/98 ተሸጦ በ03/05/98 ስለሆነና የዘገዩበትን ምክንያትም ስላልገለፁ እንዱሁም የባለንብረትነት ማስረጃም ስላላቀረቡ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጏታል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ ጥያቄ ያቀረቡት አመልካች በመሆናቸው ቤቱ የተጠሪ አባት መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለባቸው አመልካች ናቸው፤ነገር ግን ቤቱ የተጠሪ አባት መሆኑን አላረጋገጡም፣ተጠሪም የወራሽነት መብታቸውን ተጠቅመው አባታቸውን የወረሱ ለመሆኑም አልተረጋገጠም፣ተጠሪ የግብር ደረሰኝና የቀበላ ማ/ፍ/ቤት ውሣኔ በማስረጃነት አቅረበዋል በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል።
አመልካች በተራቸው በዚህ ውሣኔ ላይ አቤቱታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅረበዋል።
ችልቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ፤ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት መቃወሚያ ያቀረቡት የመጀመሪያው ጨረታ ከመደረጉ በፉት ነው፣በመሆኑም አቤቱታቸው ሉስተናገድ ይገባል፣ክርክር የተነሣበት ቤት የተጠሪ አባት ቤት ለመሆኑ ተገቢው ማስረጃ ቀርቦ በአግባቡ ተጣርቷል ወይ? የሚለው ከመታየቱ በፉት ግን ዋናው ውሣኔ የተሰጠው በአቶ ጅማ ጊርጏሶ ወራሾች ላይ በመሆኑ አፈፃፀሙ ሉቀጥል የሚገባው በወራሾች ንብረት ላይ ነው። የሟች ንብረት ለወራሾች ከተላለፈ የሟች ንብረት ተብል ላቀርብ የሚችል የለም። አመልካችም በተጠሪ ንብረት ላይ አፈፃፀሙ እንዱቀጥል ያቀረቡት ክርክር የለም። የቀረበው ክርክር ከሟች ንብረት ጋር የተያያዘ ነው። በሟች ንብረት ደግሞ አፈፃፀም ሉቀጥል ስለማይችል የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም በልላ በኩል ግን ተጠሪ የሟች ወራሽ ለመሆናቸው አልተረጋገጠም የተባለው ዋናውን ውሣኔ የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትን ውሣኔ አሻሽሎል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም የተጠሪ አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል።
ከላይ እንደተመለከተው ተጠሪ በስር ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት በሐራጅ እንዱሸጥ የታዘዘው ቤት የግል ንብረታቸው በመሆኑ ሐራጁ እንዱቆምላቸው ሲሆን መሰረት ያደረጉትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 ድንጋጌ ነው። ይህ ድንጋጌ በአፈፃፀም ምክንያት ንብረት እንዱያዝ ሲታዘዝ በዚሁ ንብረት ላይ ተቀዲሚ መብት አለኝ የሚል ተቃዋሚ ሲቀርብ የሚያገለግል ነው። በመጀመሪያ ክርክር ላይ ተካፊይ ባይሆኑም በሚያዘው ንብረት ላይ መብት አለን የሚለ ወገኖች የሚያቀርቡትን መቃወሚያ ፍ/ቤቱ ሉመረምር የሚገባው ቢሆንም ተቃዋሚዎቹ መቃወሚያውን በቂ ባልሆነ ምክንያት አዘግይተው ከሆነ ግን መቃወሚያው ላይመረመር እንደሚችል ድንጋጌው ያመለክታል። የአመልካችም አቤቱታ ቢሆን ተጠሪ ተቃውሞውን አዘግይተው ያቀረቡ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ሉመረምረው አይገባም ነበር። የሚል ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጨረታው የወጣው በ25/04/98 ሲሆን መቃወሚያው የቀረበው በ03/05/98 በመሆኑ አላግባብ ዘግይቶ የቀረበ ሲሆን ለመዘግየቱም በቂ ምክንያት መኖሩን ተጠሪ አላስረደም በሚል የተጠሪን ጥያቄ ውድቅ ቢያደርገውም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ሰበር ችልት ጥያቄው የቀረበው ከጨረታው በፉት ነው በማለት አረጋግጧል። መቃወሚያው መቼ ቀረበ? የሚለው ነጥብ ደግሞ በማስረጃ የሚረጋገጥ ፍሬ ነገር በመሆኑ በዚህ ችልት ሉስተናገድ የሚችል አልደለም።
በልላ በኩል ግን ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 በሚጠይቀው መሰረት ተቀባይነት ያለው መቃወሚያ ለማቅረባቸው የስር ፍ/ቤቶች በአግባቡ መርምረዋል ወይ? የሚለው መታየት የኖርበታል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰ/ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ ለመሻር መሰረት ያደረገው በሐራጅ እንዱሸጥ የታዘዘው ቤት የተጠሪ አባት ቤት ነው ያለት አመልካች ስለሆኑ ይህንኑ በቅድሚያ የማረዲት ሸክም ያለባቸው አመልካች ናቸው። ነገር ግን አላስረደም በማለት ነው። ይሁን እንጂ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418/3/ ተቃዋሚው ወይም መብት አለኝ ባዩ ከመቃወሚያ ማመልከቻ ጋር በንብረቱ ላይ ያለውን ተቀዲሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የጽሁፍ ማስረጃ አያይዞ በማቅረብ በቅድሚያ መብቱን የማስረዲት ሸክም ያለበት ለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። ፍ/ቤቱ ግን በቅድሚያ ሉመረምር የሚገባው የአመልካች ማስረጃ ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ የተጠቀሰውን የሥነ-ሥርአት ህጉን የተከተለ አይደለም። በዚህም ምክንያት ተጠሪ ክርክር የተነሣበት ቤት የራሣቸው እንጂ የአባታቸው ያለመሆኑን በቂ ማስረጃ ያቀረቡ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሣያጣራ አልፍታል።
በልላ በኩል ተጠሪ በዋናው መዝገብ የተከሰሱት የአባታቸው ወራሽ በመሆናቸው ሲሆን በዚህ መዝገብም ተወስኖባቸዋል። ይህንን ውሣኔ አባታቸውን የወረሱ ባለመሆኑ ውሣኔው ሉሻር ይገባል። ብለው በይግባኝ ውሣኔ የኦሮሚያ ጠቅላይ ሰበር ችልት በዋናው መዝገብ ከተሰጠው ውሣኔ ጋር ይቃረናል በማለት ሽሮታል። ይህን በተመለከተ ተጠሪ ያቀረቡት አቤቱታ የለም። በመሆኑም ተጠሪ የሟች አባታቸው ወራሽ መሆናቸውን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ነገር ግን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በአንድ በኩል ተጠሪ የአባታቸው ወራሽ በመሆናቸው በአባታቸው እዲ ተከሰው የተፈረደባቸው ለመሆኑ እያመነ በልላ በኩል ግን የተወሰነው በወራሾች ላይ በመሆኑ አፈፃፀሙ ሉቀጥል የሚገባው በወራሾች ንብረት ላይ እንጂ በሟች ንብረት ላይ አይደለም በማለት ወስኗል።
በመሰረቱ በሟች መሞት ምክንያት የሚቋረጡ ካለሆነ በቀር የሟቹ መብትና ግዳታዎች ለወራሾቹና ለኑዛዜ ባለስጦታዎች እንደሚተላለፍ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 826/2/ ተመልክቷል። በመሆኑ ወራሾች የአውራሻቸውን ግዳታ በወረሱት የሟቹ ንብረት ወይም ሐብት መጠን እንዱወጡ ይገደዲለ። በተያዘውም ጉዲይ ተጠሪ እና ላልቹ የሟች ወራሾች ተከሰው የተፈረደባቸው በአባታቸው እዲ ምክንያት ነው። በመሆኑም እዲውን እንዱከፈለ የሚጠየቁት ከአባታቸው በወረሱት ሐብት መጠን ነው። ስለሆነም ለእዲው መክፈያ በአፈፃፀም ሉያዝ የሚገባው ከአባታቸው በውርስ ያገኙት ንብረትና ሐብት እንጂ የወራሾቹ የግል ሐብት ላሆን አይገባም። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግን የተወሰነው በወራሾች ላይ በመሆኑ ብቻ አፈፃፀሙ ሉቀጥል የሚችለው በወራሾች ንብረት ላይ እንጅ በሟች ንብረት ላይ አይደለም የደረሰበት መደምደሚያ የተሣሣተ ሆኖ አግኝተነዋል። እዚህ የተሣሣተ መደምደሚያ ላይ በመድረሱም ክርክር የተነሣበት ቤት ተጠሪ አባት ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ቀርቦ በአግባቡ መጣራቱን በተመለከተ የያዘውን ጭብጥ ውሣኔ ሣይሰጥበት አልፍታል።
በአጠቃላይ የኦሮሚያ የጠቅላይ ፍ/ቤትም ሆነ የሰበር ችልቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 በሚያዘው መሰረት በቂ የጽሁፍ ማስረጃ መቅረብ አለመቀረቡን ሳያጣሩ የተጠሪን መቃወሚያ ተቀብለው የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠሪን ጥያቄ ውድቅ ካደረገበት ምክንያት አንደ ተጠሪ መብታቸው ለማረጋገጥ ማስረጃ አላቀረቡም የሚል ነው። ይህ ችልትም ከግራ ቀኙ በቃል እንዲጣራውም ቢሆን ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418/1/ መሰረት መቃወሚያ ሲያቀርቡ በቤቱ ላይ ባለመብት ለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ የግብር ደረሰኝና የቱለ ሚልኪ ከተማ 01 ቀበላ ቤቱ የተጠሪ ለመሆኑ የሰጠው ማረጋገጫ ነው። እነዚህ ደረሰኞች ደግሞ ክርክር የተነሣበት ቤት ባለቤት ተጠሪ ለመሆናቸው ማስረዲት የሚችለ በቂ ማስረጃዎች እንዲልሆኑ ተገንዝበናል። በዚህም ምክንያት ነው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው። ስለሆነም ተጠሪ የቀዲሚነት መብት ያላቸው መሆኑን የሚያስርዲ በቂ ማስረጃ ባላቀረቡበት ሁኔታ ቤቱ በሃራጅ እንዲይሸጥ መከልከለ አግባብ ሆኖ አላገኘውም።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 38529 በ09/02/2000 ዓ.ም እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 45292 በ04/09/2000 ዓ.ም ክርክር የተነሣበት ቤት በሐራጅ እንዲይሸጥ የሰጡት ውሣኔ ተሽራል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 07488 በ18/05/98 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ጸንቷል።
ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት ያቀረቡት መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም። ቤቱ በሐራጅ ሉሸጥ ይገባል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.