No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ታደለች ዋለልኝ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 41 መሰረት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን በአሁን አንደኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መካከል የነበረውን የጋብቻ ክርክር ፍ/ቤቱ ተመልክቶ በአዱስ አበባ ከተማ በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀበላ 01/05 ክልል የሚገኝ ቁጥር 242 የሆነው ቤት የሁለቱ የጋራ ሐብት ነው በማለት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ይህ ውሳኔ መብቴን የነካ ስለሆነ ሉሰረዝ ይገባል ሲለ የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው መዝገቡ ከተከፈተ በኋላ የአሁን አመልካችም በበኩላቸው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 41 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው ከሁለተኛ የመቃወም ተጠሪ/ከአሁን ሦስተኛ ተጠሪ/ ጋር በትዲር እያለን በጋራ ያፈራነው መኖሪያ ቤት የመቃወም ተጠሪዎች ነው ተብል መወሰኑ መብቴን ስለነካ ይህ ውሳኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ጣልቃ ገብ ከሁለተኛ የመቃወም ተጠሪ ጋር ጋብቻ የፈጸሙት በ26/3/2000 ዓ.ም እንደሆነ በማስረጃነት ያቀረቡት የጋብቻ የምስክር ወረቀት የሚገልጽ ሲሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የመቃወም ተጠሪዎች የጋራ ሐብት ነው ተብል የተወሰነው ደግሞ ጣልቃገብና ሁለተኛ የመቃወም ተጠሪ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፉት በ29/10/99 ዓ.ም ስለሆነ ጣልቃገብ ከሁለተኛ የመቃወም ተጠሪ ጋር ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፉት የመቃወም ተጠሪዎች የጋራ ሐብት ነው ተብል በዚህ ፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠበት ንብረት የጣልቃገብ እና የሁለተኛ የመቃወም ተጠሪ የጋራ ሐብት የሚሆንበት የሕግ አግባብ የለውም። በማለት አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
አመልካች በዚሁ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ከሦስተኛ ተጠሪ ጋር በባህል የተጋባነው በ1992 ዓ.ም ነው እያለ የስር ፍ/ቤት ክርክር የተነሳበት ንብረት የተፈራው አመልካችና ሦስተኛ ተጠሪ ከመጋባታቸው በፉት ነው በማለት የአመልካችን አቤቱታ ሳይቀበል መቅረቱ ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን ጠርቷል።
ይሁንና አንደኛ ተጠሪ የፍ/ቤቱን መጥሪያ አልቀበልም ስለማለታቸው በአመልካች ቃለ መሐላ በመረጋገጡ ሁለተኛ ተጠሪም በምትክ መጥሪያ ተጠርተው ባለመቅረባቸው ክርክሩ በላለበት እንዱታይ ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ሦስተኛ ተጠሪ ቀርበው ከአመልካች ጋር በባህል የተጋቡት በ1992 ዓ.ም እንደሆነ ገልጸው በአቤቱታው መሰረት ቢወሰን ተቃውሞ የለኝም ብለዋል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
እንደመረመርነውም አመልካች ከሦስተኛ ተጠሪ ጋር በ1992 ዓ.ም በባህል መጋባታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ በአስረጅነት ለስር ፍ/ቤት ማቅረባቸውን ተገንዝበናል። የስር ፍ/ቤት አቤቱታቸውን ሳይቀበለው የቀረው ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ክርክር የተነሳበት ንብረት የተፈራው አመልካችና ሦስተኛ ተጠሪ ከመጋባታቸው በፉት ስለሆነ በንብረቱ ላይ መብት የላቸውም በማለት ነው። ለዚህም ውሳኔ መሰረት ያደረገው አመልካችና ሦስተኛ ተጠሪ የፈጸሙት ጋብቻ በ26/3/2000 ዓ.ም በክብር መዝገብ ሹም የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጠውን የጋብቻ የምስክር ወረቀት በመመልከት ነው።
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 28/1/ ላይ ጋብቻው የተፈጸመው በማንኛውም የጋብቻ አፈጻጸም ስርአት ቢሆንም አግባብ ባለው የክብር ሹም መመዝገብ እንዲለበት የተደነገገ ሲሆን ጋብቻው ሕጋዊ ውጤት የሚኖረው ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ጋብቻው ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ በዚህ አንቀጽ 28/3/ ላይ ተመልክቷል።
በአመልካችና በሦስተኛ ተጠሪ መካከል የተፈጸመው ጋብቻ ተመዝገበው በ26/3/2000 ዓ.ም ቢሆንም ከዚህ ቀን በፉት ጋብቻው የተፈጸመ መሆኑ ከተረጋገጠ ሕጋዊ ውጤት ሉኖረው ስለሚችል በዚሁ መሰረት ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ጋብቻው የተመዘገበበትን ቀን መሰረት በማድረግ ከዚህ በፉት ጋብቻ ስለላለ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የፋዳራል ከ/ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
የፍደራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19258 በ7/1/2001 ዓ.ም የሰጠው ከፉል ውሳኔና የፍደራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 73407 በ23/3/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በአመልካችና በሦስተኛ ተጠሪ መካከል የባህል ጋብቻ መፈጸሙን በማጣራት ክርክር በተነሳበት ንብረት ላይ እንዱወሰን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 343/1/ መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።