No summary available.
ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሣሙኤል ፈረንጅ - ጠበቃ አበበ ታዬ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡- 1/ አቶ ግርማ ታፈሰ - ጠበቃ አብርሃም አሰፊ ቀርበዋል።
2/ ወ/ሮ አሰገደች በቀለ - ጠበቃ አብርሃም አሰፊ ቀርበዋል።
ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻው አመልካች ግንቦት ዐ4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት በፍ/ይ/መ/ቁ.33ዐዐ4/ የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 ይዘት ከምስክሮች አንደ ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሲባል በስጦታው /ኑዛዜው ፍርም ውስጥ የተመዘገበ ምስክር ከሆነ እንጂ ኑዛዜው ወይም ስጦታው በአዋዋዩ ወይም በዲኛው ፉት መከናወኑ ብቻ የምስክሮቹን ብዛት በተለየ ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881/2 ከሚፈለጉት 4 ምስክሮች ወደ ሁለት ዝቅ ማድረግ አይቻልም በማለት የያዘው የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርደ እንዱታረምላቸው ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ የጀመው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን በዚሁ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች አመልካ ች፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተጠሪ የነበሩ ሲሆን፤ አመልካ ቹ ጥር ዐ6/1988 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የሟች ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ ወራሾች መሆናቸውን በመግለጽ በወረዲ ዐ9/ቀበላ ዐ6 ክልል የሚገኘው የቤት ቁጥር 579 የሆነውና በቤቱ ውስጥ የሚገኙ ቁሣቁሶች እንዱሁም ግሮሰሪ የሟች አውራሻቸው ንብረቶች መሆናቸውን በመግለጽ የውርስ አጣሪ እንዱሾምላቸው የጠየቁ ሲሆን በስር ፍ/ቤቱ ተጠሪ የነበሩ የአሁኑ አመልካችም መጋቢት ዐ5/1988 ዓ.ም በተፃፈ መልሣቸው አመልካ ቹ ያቀረቡት ጥያቄ ሐቅነት እንደላለው በመግለፃቸው ፍ/ቤቱም የውርስ አጣሪ ሾሟል፣ ውርስ አጣሪውም ሚያዚያ 2ዐ ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ ሪፖርት ለፍ/ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም አከራካሪው ቤት ተጠሪው ከሟች በስጦታ የተላለፈላቸው እንደሆነና ይህንንም የስር አመልካ ቹ እንደማይቀበለት የሚገልፀው መሰረታዊ ነጥብ ሲሆን የስር ፍ/ቤቱም ቤቱ ለተጠሪው በሥጦታ እንደተላለፈላቸው በማረጋገጥ አመልካ ቹ በዚሁ ተቃውሞ ካላቸው የስጦታ ይፍረስልኝ ጥያቄ ከሚያቀርቡ በስተቀር ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንደላለው ወስኗል።
አመልካ ቹም የስር ፍ/ቤቱ በኮ/ቁ. 22789፣ ጥር 12 ቀን 1998 ዓ.ም ከላይ የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም የግራና ቀኙን ክርክር ካኪያሄደ በኋላ በኮ/መ/ቁ. 45348፣ ሐምል 17 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ይግባኝ ባዮቹ በተለየ መዝገብ የስጦታው ይፍረስልን ጥያቄ ማቅረብ ሣያስፈልጋቸው በውርስ አጣሪው በተደረገው የማጣራት ስራ የስጦታው ሕጋዊ ያለመሆን ክርክር ከማቅረብ የሚከለከለበት ምክንያት እንደላለ ካሰፈረ በኋላ አከራካሪው ስጦታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443፣ 881 እና 882 እንደተገለፀው በአራት ምስክሮች ፉት ያልተደረገ እንደሆነና መጋቢት 18 ቀን 1987 ዓ.ም ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ ለመልስ ሰጭው አደረጉት በተባለው ስጦታ የሰፈሩት ሁለት ምስክሮች እንጂ በሕጉ መሰረት አራት እንዲልሆኑ፣ ስጦታው በአዋዋይ ፉት መከናወኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 እንደተጠቀሰው የምስክሮቹ ብዛት ወደ ሁለት አያስቀንሰውም፤ በዚሁ ዓንቀጽ መሰረት ምስክሮቹ ሁለት ሰዎች ብቻ በቂ የሚሆኑት ከምስክሮቹ አንደ ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ወይም ዲኛ ሆነው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ሲሆን ነው፤ በዚህ የስጦታ ጽሁፍ ግን ምንም እንኳ ስጦታው የተደረገው በአዋዋይ ፉት ቢሆንም ከሁለቱ ምስክሮች አንደ ራሱ አዋዋዩ ባለመሆኑና በሕግ የሰፈረውን አባባል ስለማያሟለ ተደረገ የተባለው ስጦታ ተቀባይነት የለውም፤ ይግባኝ ባዮቹ በቤቱ ላይ ድርሻ አላቸው በማለት የስር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
348/1/ መሰረት ሽሮታል።
የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልትም ከላይ የሰፈረውን የከፍተኛ ፍ/ቤቱ አተረጓጎም ተቀባይነት ያለው መሆኑና የአሁኑ አመልካች ያቀረቡለትን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 ተቀባይነት እንደላለው በፍ/ይ/መ/ቁ. 33ዐዐ4 የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ አረጋግጧል።
አመልካቹም ግንቦት ዐ4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው´አከራካሪው ቤት ከወ/ሮ ጥሩነሽ አበበ በስጦታ እንደተላለፈላቸውና የስጦታ ውለም በውልና ማስረጃ ጽህፈት ቤት ቀርቦ በቁጥር 167/87 በ26/ዐ7/1987 ዓ.ም ተመዝግቦ ከ12 ዓመታት በላይ በይዞታዬ ስር ሆኖ እያለና የስር ፍ/ቤቱ ስጦታው በአግባቡ የተከናወነ ነው ብል እያለ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውለ በውልና ማስረጃ ፉት ቢፈፀምም በጽሁፈ ውስጥ አራት ምስክሮች አልተጠቀሱም አዋዋዩ ራሱ በውለ ውስጥ በምስክርነት እስካልተጠቀሰ ድረስ ሁለቱ ምስክሮች በቂ አይደለም በማለት የስጦታ ውለን ማፍረሱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነውና ውሣኔው ይሻርልኝ ብለዋል።
No topics extracted.
ተጠሪዎቹም ጥቅምት 11/2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በስጦታ ውለ የተጠቀሱት ሁለት ተራ ሰዎች እንጂ አንዲቸውም አዋዋይ ባለመሆናቸው በሕጉ የተቀመጠው የአራት ምስክሮች መሟላት በላለበት ሁኔታ ስጦታው ሕጋዊ ላሆን አይችልም፤ ስለሆነም የከፍተኛው ፍ/ቤት እና የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔዎች ተገቢውን አተረጓጎም የተከተለ በመሆናቸው ሉፀድቁ ይገባል የሚል ነው።
ይህ የሰበር ችልትም የግራ ቀኙ ወገኖች የክርክር አመጣጥ ከላይ በሰፈረው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ መጋቢት 18 ቀን 1987 ዓ.ም ለአመልካች ያደረጉት ስጦታ ተገቢውን ፍርማሉቲ ያሟላ ነው ወይስ አያሟላም?
የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
የአሁኑ ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ጥያቄ በቀድሞ ወረዲ ዐ9፣ ቀበላ ዐ6 የሚገኘው ቁጥሩ 579 የሆነውን ቤት የአውራሻቸው ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ እንደሆኑ በመግለጽ በውርስ አጣሪ ተጣርቶ ድርሻቸውን እንዱከፈላቸው ሲጠይቁ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ከላይ የተጠቀሰው ቤት ሟች ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ በውልና ማስረጃ ጽህፈት ቤት ቀርበው የሰጧቸው እንደሆነና የውርስ መጣራቱ አካል ላሆን እንደማይገባው የሚጠቁም መልስ ሰጥተዋል። በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ የተሾመው ውርስ አጣሪ አካል ባደረገው ማጣራት አከራካሪው ቤት ለአመልካቹ በስጦታ የተላለፈ እንደሆነና በውርስ ክፍፍለ መካተት የለበትም የሚል የውሣኔ ሃሣብ ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱም ይህንን የማጣራት ውጤት ተቀብል አጽድቆታል። በአሁኑ ተጠሪዎች ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የስጦታው ሕጋዊነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443፣ 881/2/ እና 882 አኳያ ከሚፈለገው ፍርማሉቲ አንፃር ጉዲዩን በማጤን ምንም እንኳ ስጦታው በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተከናወነ ቢሆንም ውል አዋዋዩ በስጦታው ጽሁፍ እንደ አንድ ምስክር ሆኖ እስካልተጠቀሰ ድረስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 የተጠቀሰው የሁለት ምስክሮች ልዩ ሁኔታ ተሟልቷል ልባል አይችልም፤
በፍ/ብ/ህ/ቁ.881/2/ በተጠቀሰው መሰረት በስጦታ ውለ አራት ምስክሮች መጠቀስ ሲገባቸው ሁለት ምስክሮች ብቻ መዘርዘራቸው በቂ ባለመሆኑ ስጦታው በሕግ አስገዲጅነት ያለውን ፍርማሉቲ አላሟላም በማለት ተቀባይነት የለውም ብሎል፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልትም የከፍተኛውን ፍርድ ቤት አተረጓጎም በመቀበል አመልካቹ ያቀረበለትን ይግባኝ ሣይቀበለው ቀርቷል። ይሁን እንጂ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 አተረጓጎም በሚመለከት ይህ የሰበር ችልት ካሁን በፉት በ
ጥቅምት 25/2ዐዐ1 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ሲሆን ይኸውም የኑዛዜ ወይም የስጦታ ውል የተፈፀመው ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፉት ከሆነ አዋዋዩ በኑዛዜው ወይም በስጦታ ውለ ውስጥ እንደ ምስክር ሆኖ ባይፃፍም ምስክር አይደለም ተብል ሉተረጎም እንደማይገባ ነው፤ የኑዛዜው ወይም የስጦታው ሂደት ያለምንም ተጽእኖ በነፃነት እንዱከናወን በማድረግ የምዝገባውን ሂደት የመራ እስከሆነ ድረስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 መሰረት ኑዛዜው ወይም ስጦታው ተቀባይነት እንዱኖረው ሁለት ምስክሮች በቂ ናቸው፤ በተያዘው ጉዲይም ወ/ሮ ጥሩነሽ ቦጋለ አከራካሪውን ቤት በውልና ማስረጃ ጽህፈት ቤት ማለትም ስራውን በማከናወን በነበረ አዋዋይ ፉት ቀርበው ለአመልካች መስጠታቸውን ሁለም የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ነው፤ ስለሆነም አዋዋዩ በስጦታው ሰነድ ስሙ በምስክርነት ባይፃፍም የስጦታ ሂደቱ ሲከናወን የነበረ ምስክር ነው። በመሆኑም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የስጦታ ውለ አራት ምስክሮች ያልፈረሙበት ወይም ደግሞ ከምስክሮቹ አንደ ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ወይም ዲኛ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 45348፣ ሐምል 17 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል፤ ይፃፍ።
2/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት በፍ/ይ/መ/ቁ 33ዐዐ4 የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ ተሽሯል፤ ይፃፍ።
3/ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ.መ.ቁ. 22789፣ ጥር 12 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 348/1/ መሰረት ፀንቷል፤ ይፃፍ።
4/ አከራካሪው የስጦታ ውል ስራውን ሲያከናውን በነበረ ውል አዋዋይ ፉት በመቅረብ የተከናወነ በመሆኑ ምንም እንኳ አዋዋዩ በስጦታ ውለ ውስጥ በምስክርነት ባይጠቀስም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 በተጠቀሰው መንገድ እንደ ምስክር ስለሚቆጠር ስጦታው ተገቢውን የምስክሮች ብዛት /ፍርማሉቲ/ ያሟላ ነው ብለናል።
5/ ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ፤ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።