No summary available.
መ/ቁ. 3571ዐ ታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ እፀገነት እሸቱ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰላማዊት ንጉሴ - ጠበቃ ይልማ ቻኔ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ ለሰበር ችልቱ ላቀርብ የቻለው የአሁኗ አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአሁኗ ተጠሪ ግንቦት 15 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ሟች ዘነበ ንጉሴ ታህሣሥ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ንብረታቸውንና የሕፃን ናትናዓል ዘነበን አሣዲጊነትና ሞግዚትነት በተመለከተ ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፀድቅላቸው ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዲኝነት ጠይቀው ይኸው ፍ/ቤትም የተጠሪን አቤቱታ በመቀበል ኑዛዜው የፀደቀ መሆኑን በመግለጽ ሐምል ዐ7 ቀን 1997 ዓ.ም ወስኗል። ከዚህ በኋላም የአሁኗ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ባቀረቡት የተቃውሞ አቤቱታ ሟች ኑዛዜውን ያደረጉት በጋብቻ የጋራ ድርሻ ባለበት ንብረት መሆኑን፣ የሞግዚትነት ስልጣን ከእናት ለመውሰድም ሕጋዊ ክልከላ ያለ ስለመሆኑ፣ ኑዛዜው ግልጽነት የጎደላቸውን ቃላት የያዘ መሆኑን በመዘርዘር ሟች አደረጉ የተባለው ኑዛዜ የፀደቀው ያላግባብ በመሆኑ ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት ዲኝነት ጠይቀው ተቃውሞ የቀረበለት ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ኑዛዜው ከንብረት ክፍፍለ በፉት በጋብቻ የጋራ ንብረት መደረጉን፣ የእናት ሞግዚትነትም ከሕግ የሚመነጭ ሆኖ እያለ አባት በኑዛዜ ለሕፃን አክስት እንዱሆን ማድረጋቸው ተገቢነት የላለው መሆኑን፣ ኑዛዜው ግልጽ ያልሆነ አሻሚ ቃል ይዞ መገኘቱም ፈራሽ የሚያደርገው ስለመሆኑ የሚለትን ነጥቦችን በምክንያትነት ጠቅሶ የአመልካችን ተቃውሞ በመቀበል ቀደም ሲል ኑዛዜውን በማጽደቅ የሰጠውን ውሣኔ ሰርዞታል። ጉዲዩን በይግባኝ ደረጃ የተመለከተው የከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። ጉዲዩ በሰበር የቀረበለት የከተማው አስተዲደር ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ መዝገቡን በመመርመር በርካታ ምክንያቶችን በፍርደ ላይ በማስፈር የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ከሻረ በኋላ ሟች ታኀሣሥ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረጉት ግልጽ ኑዛዜ የአሁኗን ተጠሪንና ሕፃን ናትናኤል ዘነበን ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ በማድረግ የተውት በመሆኑ ኑዛዜው ፈራሽ አይደለም በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ተጠሪን ያስቀርባል ተብል ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን ሲያቀርቡ አመልካች በበኩላቸው ሐምል 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
ከዚህም በኋላ ግራ ቀኙ በችልት የቃል ጥያቄ ተደርጎላቸው መልስ ከሰጡ በኋላ ሕፃን ናትናኤል ዘነበ በችልት ቀርቦ ሐሣቡንና ፍላጎቱን እንዱሰጥ ተደርጎ ቃለ ተመዝግቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር፣ የሕፃን ናትናዓል ዘነበን አስተያየት የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ሟች አቶ ዘነበ ንጉሴ ታህሣሥ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረጉት ግልጽ ኑዛዜ የተጠሪና የሕፃን ናትናኤል ዘነበን ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ በማድረግ የተውት ኑዛዜ ፈራሽ አይደለም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች አቶ ዘነበ ንጉሴ እና የአሁኗ አመልካች በጋብቻ ተሣስረው ሲኖሩ ቆይተው ጋብቻው በፍቺ ውሣኔ ታኀሣሥ 22 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ መፍረሱን፣ በዚህ ወቅትም ፍቺው በልጆች አስተዲደግና በንብረት ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ስምምነት እንዱያቀርቡ፣ መስማማት ካልተቻለ አንዲቸው አቤቱታ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ተሰጥቶ መብት ከተጠበቀ በኋላ የፍቺ ጥያቄ የተስተናገደበት መዝገብ መዘጋቱን ነው።
ከዚህም በኋላ የንብረት ክርክር ተደርጎ የጋራ መሆናቸው የተረጋገጡን ዔቃዎች ግራ ቀኙ እንዱካፈለ፣ በመኖሪያ ቤቱ ላይ የአሁኗ አመልካች ያላቸው ድርሻ 1ዐ,171.78/ አስር ሺህ አንድ መቶ ሰባ አንድ ብር ከሰባ ስምንት ሣንቲም/ መሆኑ ተረጋግጦ ሟች አቶ ዘነበ ንጉሴ እንዱከፍለ ተብል መጋቢት 21 ቀን 1997 ዓ.ም በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ7941 ተወስኗል። ላላው ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ኑዛዜ ያደረጉት ታኀሣሥ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ሆኖ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሚያዝያ 3ዐ ቀን 1997 ዓ.ም መሆኑን፣ የአሁኗ አመልካች የሕፃን ናትናኤል ሞግዚትና አስተዲዲሪ እንዱሆኑ በፍ/ቤት የተወሰነው ግንቦት 27 ቀን 1997 መሆኑን የአሁኗ ተጠሪ ሟች ያደረጉትን ኑዛዜ በፍ/ቤት እንዱፀድቅ ግንቦት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ አቅርበው ሐምል ዐ7 ቀን 1997 ዓ.ም በፍ/ቤት ፀድቆ መወሰኑን፣ ይኸው ውሣኔ እንዱሰረዝ በአሁኗ አመልካች በኩል የተቃውሞ አቤቱታ የቀረበው ጥቅምት ዐ4 ቀን 1998 ዓ.ም እና የአሁኗ አመልካች በመኖሪያ ቤቱ ላይ ያላቸው ድርሻ በውሣኔው መሰረት ያልተከፈላቸው መሆኑን ጭምር ነው።
በልላ በኩል የአዱስ አበባ ከተማነክ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሟች አቶ ዘነበ ንጉሤ ኑዛዜ በሕፃኑ ሞግዚትነትና አሣዲሪነት ላይ የተደረገ መሆኑ እየተገለፀለት የአሁኗን ተጠሪንና ሕፃን ናትናኤል ዘነበን የሟቹ ጠቅላላ ወራሾች የሚያደርገው ኑዛዜ ፈራሽ አይደለም በማለት የሞግዚትነትን ጉዲይ በተመለከተ ግልጽ ውሣኔ አለማስፈሩን ከውሣኔ አሰጣጡ ሂደት ተገንዝበናል።
እንግዱህ በሟች አቶ ዘነበ ንጉሤ ኑዛዜ የተገለፀው የሕፃኑ ሞግዚትነትና ኑዛዜው በጠቅላላው የሟች ንብረት ላይ ያለውን ዋጋ ከሕጉ ጋር አገናዝቦ መመልከትን የግድ ይሎል። በቅድሚያ ሉመረመር የሚገባው ነጥብ ለሕፃን ናትናኤል ዘነበ አክስቱ የሆነችው የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት እንዱሆኑ ሟች ዘነበ ንጉሴ በኑዛዜ መወሰናቸው ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነው።
እንደሚታወቀው ሕፃናት የተለየ ድጋፍና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ አካል ናቸው። የዚህም መነሻ ሀሣብ ሕፃናቱ ከእድሜያቸው ለጋነት በተያያዘ ለአደጋ የተጋለጡ የሕብረተሰብ አካላት /vulnerable groups/ የመሆናቸው ጉዲይ ነው። ይህንኑ አደጋ ለመከላከል እና የተለየ ድጋፍና እንክብካቤ የማድረጉ ሥራ የተሣካ ይሆን ዘንድም የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍልች መብትና ደህንነት በሚመለከት የተለዩ ስምምነቶች በአለምና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተፈርሞ እየተገበሩ ይገኛለ። ከስምምነቶቹ ውስጥም የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን እና የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር ተጠቃሾች ናቸው። ሐገራችን ኢትዮጵያ የሕፃናት መብቶች ኮንቬሽንን ህዲር 29 ቀን 1984 ዓ.ም፣ የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር ደግሞ እ.ኤ.አ ኦክቶበር ዐ2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም አጽድቃለች። ከዚህ በተጨማሪ የሕፃናትን መብትንና ደህንነት በሚመለከት የፋዳራለ ሕገ-መንግሥት፣ የክልል ሕግጋተ- መንግሥታት እና ላልች ሕጎች አለ። በዓለም አቀፍ በአህጉርና በአገር ደረጃ ሕፃናትን አስመልክቶ በስራ ላይ ያለ እነዚህ ሕጎች ደግሞ መሰረታዊ መርሆዎችን የያዙ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን መሰረታዊ ከሆኑት መርሆዎች ውስጥ አንደ ሕፃናትን በሚመለከቱ ጉዲዮች ለሕፃናት ጥቅምና ደህንነነት /the best interest of the child/ ቅድሚያ መስጠት የሚለው ስለመሆኑ የአንቀጽ 3.1 ድንጋጌ ሲያሣይ የአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተርም በአንቀጽ 4.1 ድንጋጌ ስር ይህንኑ አካትቶ ይዟል። የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥትም ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን የዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የአገሪቱ የሕግ አካል መሆናቸውን በአንቀጽ 9/4/ ስር ከመደንገጉና በሕገ-መንግሥቱ በስፊት ሽፊን የተሰጣቸው መሰረታዊ የመብቶችና የነፃነቶች ድንጋጌዎች ሀገሪቱ ከተቀበለቻቸውና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግጋት፣ ስምምነቶች ወይም ሰነድች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም የግድ ስለመሆኑ በአንቀጽ 13/2/ ከማስቀመጡም በተጨማሪ የሕፃናትን ልዩ ችግር ከግምት ያስገቡ የተለያዩ ንዐስ ድንጋጌዎችን የያዘ ድንጋጌ በአንቀጽ 36 አስፍሯል። በተለይም የአንቀፁ ንዐስ አንቀጽ ሁለት ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰደበት ጊዜ ሁለ የመንግሥታዊ ወይም የበጎ አድራጎት ተቋማት እንዱሁም ፍ/ቤቶችና የአስተዲደር ባለስልጣናት ወይም የሕግ አውጪው አካላት የሕፃናትን ደህንነት በቀድሞ ትጋት ሉያስቡበት የሚገባ ስለመሆኑ አጽንኦት ባለው መንፈስ፤ በአስገዲጅነት ደንግጓል። ሕገ-መንግሥቱንም ተከትለው የወጡ ፖሉሲዎችና ሕጎዎች አቀራረጽ ይዘትና መንፈስ ሲታይም የሕፃናትን መብትና ደህንነት የማስከበር ዓላማ ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ መሆኑን ለመገንዘብ አያዲግትም።
የሕፃናትን ጥቅምንና ደህንነት ቀደምትነት ከሚለው መርህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍና በአህጉራዊ ሰነድችና ስምምነቶች ውስጥ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ላላው መሰረታዊ መርህ የሕፃናት ተሣትፍ መርህ ነው። የዚህ መርህ ዓይነተኛ ይዘት በዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን በአንቀጽ 12 የተመለከተ ሲሆን የአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተርም በአንቀጽ 4.2 ስር በግልጽ ሰፍሯል። አጠቃላይ የዚህ መብት አድማስ ሲታይም ሕፃናት ህይወታቸውን በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ በውሣኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ተሣትፍ ማድረግ እንደሚችለ፣ በተጨማሪም ጥቅማቸውን በሚመለከቱ ውሣኔዎች ላይ የራሣቸውን ተጽእኖ የማሣረፍ መብት ያላቸው መሆኑ፣ይህም ስፊት ባላቸው የፍርድ ጉዲዮች እንዱሁም መደበኛ የውሣኔ አሰጣጥ በሚመለከቱ በጤና፣ በትምህርትና በአከባቢ ጉዲዮች ሁለ ሉካተት የሚገባ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ድንጋጌዎቹ ሕፃናት በጉዱፍቻ ወቅት፣ በወላጆች መለያየትና ፍቺን ተከትል የትኛው ወላጅ ጋር ማደግ እንደአለባቸው ውሣኔ ሲሰጥ እና በመሣሰለት ጉዲዮች ላይ አስተያየት መስጠትና ሉደመጡ እንደሚገባ እንዱሁም አስተያየታቸው ከመደመጡ ባሻገር ተገቢው አፅንኦት ሉሰጠው የሚገባ መሆኑን ያስረዲለ። የሕፃናቱ ሀሣብና አስተያየት ተገቢውን አፅንኦት የሚያገኘውም የሕፃኑን እድሜንና የአስተሣሰቡን የብስለት ደረጃ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መሆኑንም የሚያጠያይቅ አይሆንም።
እንግዱህ ሕፃንን የሚመለከት አንድ ጉዲይ ሲወሰን ሉታሰብባቸው የሚገባቸውን የተወሰኑ መሰረታዊ መርሆዎችን የሕግ ማቀፊቸውንና የድንጋጌዎችን ዝርዝር ይዘትና መንፈስ ምን እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል። እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስም የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አካለ መጠን ያልደረሰን ልጅ የሚጠብቁትን ተቋሟትንና ቅደም ተከተለን ከአንቀጽ 219-238 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች አስቀምጧል። በድንጋጌዎቹ መሰረት ወላጆች ከላላው ሰው በቅድሚያ የአስተዲዲሪነትና የሞግዚትነት ሥልጣን ያላቸው መሆኑ፣ አሣዲሪ ወይም ሞግዚት በልጁ ወላጅ በኑዛዜ ቃል የሚመረጥ መሆኑ፣ ይህም በፍ/ቤት ሉሻር ወይም ሉሻሻል የሚችል መሆኑ፣ ወላጆች ወይም የወላጅ ኑዛዜ ከላለ ሦስተኛው መንገድ ከዘመድቹ መካከል በዝምድና ቅደም ተከተል የአሣዲሪነትና የሞግዚትነት ሥልጣን ላሰጥ እንደሚገባ፣ በመጨረሻም በሕግ የሚመረጡ ዘመድች ከላለ ይኸው ሥልጣን በፍ/ቤቱ በሚመረጥ ሰው ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ ተገልጿል። ሆኖም የእነዚህ ድንጋጌዎች ቅደም ተከተል ተግባራዊ ሲደረግ ሁልጊዜ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ቁልፈ ነጥብ በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የሕፃኑ ደህንነት መብት ቀደምትነት ስለመሆኑ ሉረሣ የማይገባው ነው። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ የተመለከቱት ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎችም ሆነ በአንቀጽ 113/2/ ስር የተመለከተው ድንጋጌ አቀራረፅ፣ ይዘትና መንፈስ ሲታይ ፍ/ቤቶች አካለመጠን ያልደረሰን ልጅ አሣዲሪነትና ሞግዚትነት በተመለከተ ውሣኔ ሲሰጡ በሕጉ የተሰጣቸውን ሰፉ ሥልጣን መጠቀም ያለባቸው መሆኑንና የሕፃናትን መብትና ጥቅም የማስከበር ኃላፉነታቸውን መወጣት ግዳታ ያለባቸው መሆኑን ያስረዲል። በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 13/1/ ስር የተመለከተው ድንጋጌም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። የሕፃናትን ደህንነትና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚችል ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ደግሞ የሕፃናቱ ሀሣብ ሉደመጥና ተገቢው ክብደት ሉሰጠው የሚገባ ነው ይህንኑ የሚቃረኑ ልማዲዊ አሰራሮችን ተቀባይነት የላላቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 9/1/ ድንጋጌ በግልጽ ያሣያል።
በዚህም መሰረት የዚህ መዝገብ ጉዲይ ሲታይ ሕፃን ናትናኤል ዘነበ አስተዲዲሪነትና ሞግዚትነትን በተመለከተ የሟቹ ኑዛዜ የሕፃኑን ደህንነትና ጥቅም ቀደምትነት መርህ ለማስከበር እና ተግባራዊ ለማድግ በሚያስችል መልክ የተከናወነ ሆኖ አልተገኘም። ሕፃን ናትናኤል ዘነበ በዚህ ችልት ሲደመጥም ከአክስቱ ጋር የመኖር ፍላጎት የላለው መሆኑንና ከወላጅ እናቱ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገለት በማደግ ላይ ያለ ስለመሆኑ አስተያየት ሰጥቷል። ሕፃኑ ከአባቱ ሞት በኋላ በአክስቱ በኩል ተገቢው ክትትልና እንክብካቤ ያልተደረገለት ስለመሆኑም አረጋግጧል። የሕፃኑ እድሜ ሲታይም አስር መሆኑንና አስተሣሰቡም የበሰለ ልባል የሚችል መሆኑ ይህ ችልት የተገነዘበው ሲሆን ይህም ለአስተያየቱ ተገቢው ክብደት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የሚያሣይ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች መሰረት ሟች አቶ ዘነበ ንጉሤ ስለሕፃን ናትናኤል ሞግዚትነት የተውት ኑዛዜ ፈራሽ የማይሆንበት ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ላላው በሟቹ ኑዛዜ የተገለፀው ነገር የሟቹን ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነትን ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል። በዚህ እረገድ የሟቹ ኑዛዜ ሰነድ ይዘት ሲታይ ፡- "… በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 19 ቀበላ 55 የቤት ቁጥር 1654 የሆነውን መኖሪያ ቤቴን ግቢ ውስጥ ያለትን ቤቶችንና መኖሪያ ቤት ውስጥ ያለውን ንብረቴን በስሜ በባንክ ያለውን ገንዘብ ሁለት እጁን ለእህቴ ለወ/ሮ ሰላማዊት ንጉሤ ኪዲኔ በራሤ ፈቃድ ተናዝዣለሁ፣አንድ እጁን ለልጄ ለአምስት ዓመቱ ለናትናኤል ዘነበ ንጉሤ አውርሻለሁ፣ የኑዛዜ ተቀባይዋ እህቴ ወ/ሮ ሰላማዊት ንጉሤ ኪዲኔ ከላይ ስሙ የተጠቀሰውን ልጄን አቅመ አዲም እስኪደርስና እራሱን እስኪችል ድረስ በኑዛዜ የተናዘዝኩትን ንብረቴን አንድ እጁን ተንከባክባ እየጠበቀች የቤቱንም ኪራይ እየተቀበለች አስቀምጣ እራሱን ሲችል እንድታስረክበው የእሷን ድርሻ ሁለት እጁን ለራሷ እንድትጠቀምበት ላደረገችልኝ ውለታ መክፈያ መናዘዜንና ልጄን ተንከባክባ እንድታሣድግልኝ ይህንን ኑዛዜ አድርጌአለሁ …" የሚል እና በአራት ምስክሮች ፉት የተደረገ ግልጽ ኑዛዜ ነው።
ሟች ለተጠሪ ያደረጉት ኑዛዜ ተጠሪን የሟች ንብረቶች ተጠቃሚ እንዱሆኑ ያደረገው በአንድ በኩል ለሕፃኑ ለሚያበረክቱት መልካም አስተዲደግ፣ በልላ በኩል ደግሞ ለሕፃኑ ከሚያደርጉት መልካም አስተዲደግ በተጨማሪ ለሟቹ ላደረጉት ውለታ ስለመሆኑ የሚጠቅስ ይመስላል። ተጠሪ በበኩላቸው የሕፃኑ ሞግዚትነትና አስተዲዲሪነት በኑዛዜው መሰረት አይገባሽም ከተባልኩ ንብረቱን በተመለከተ ሟች 2/3ኛው ይሰጣት በማለት የተናዘዙት የሚፈርስበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ የሟች ኑዛዜ አጠቃላይ ይዘቱና መንፈሱ በውል ሲታይ ተጠሪ የሟች ንብረት የኑዛዜ ተጠቃሚ የሚሆኑት ሕፃን ናትናኤልን ተንከባክበው ሲያሣድጉ መሆኑን ያስገነዝባል። ተጠሪ ሕፃኑን ሲያሣድጉ አስፈላጊውን ወጪ የሚያደርጉበት ለራሣቸው ድርሻ ይሆናል ከተባለው ስለመሆኑም የኑዛዜው ይዘት ያሣያል። ምክንያቱም ሟች ለሕፃኑ ከተውት1/3ኛ ድርሻ ተጠሪ ተንከባክበው እንዱጠብቁ፣ የቤት ኪራዩን እየተቀበለ እንዱያስቀምጡና ለአካለመጠን ሲደርስና ራሱን ሲችል እንዱያስረክቡ በኑዛዜው ላይ በግልጽ መቀመጡ ለሕፃኑ እንክብካቤና አስተዲደግ ወጪ የሚደረገው ከተጠሪ ድርሻ መሆኑን የሚያሣይ ነው። ከዚህ አኳያ ሟች አቶ ዘነበ ንጉሤ ታህሣሥ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ገደብ ያለበት ኑዛዜ /Conditional legacy/ ስለመሆኑ መገንዘብ አያዲግትም። የኑዛዜ ስጦታ ጠቅላላ ወይም ልዩ ላሆን እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 912 ስር የተመለከተ ሲሆን እንደዚህ ዓይነት የኑዛዜ ስጦታዎች አንድ ሁኔታ ሲደርስ የሚፀኑ ወይም የሚቀሩ ሆነው ሉደረጉ የሚችለ ስለመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 916 ድንጋጌ ያስረዲል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ሕፃን ናትናኤልን ተንከባክበው ያሣደጉት ሁኔታ የለም።
ተጠሪ ሕፃኑን ከራሣቸው የኑዛዜ ድርሻ ወጪ በማድረግ ተንከባክበው የማሣደግ ሁኔታ ካልተረጋገጠ ደግሞ ተጠሪ የንብረቱ በኑዛዜ ተጠቃሚነት የፀና ላሆን አይችልም። ስለሆነም ተጠሪ የኑዛዜው ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሕጋዊ ምክን ያት ሣይኖር የኑዛዜ ጠቅላላ ወራሽ ናቸው ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህም ምክንያት የሟች አቶ ዘነበ ንጉሤ ማንኛውም የሚንቀሣቀስም ሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት ሕጋዊ መብት የሚተላለፈው ለሕፃን ናትናኤል ዘነበ ሆኖ የሕፃኑ ሞግዚትና አስተዲዲሪ አመልካች ሆነው ሉያስተዲድሩት የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል። አመልካች የሕፃኑን የማይንቀሣቀስ ሀብት መልካም አስተዲደር በሚመለከት የሞግዚትነት ሥልጣን እንዱኖራቸውም መወሰን አለበት ብንልም ሕፃኑ ከሟቹ አባቱ የሚተላለፍለትን ሀብት አጠቃላይ ሁኔታ፣ የአመልካችን ችልታ፣የክርክሩን አጠቃላይ ይዘትንና የልጁን ጥቅም በማመዛዘን ስለሀብቱ አስተዲደር አመልካች የሚኖራቸውን ሥልጣን ከወዱህ መግለጽ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል። በአጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.
ዐ4273 ጥር ዐ2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
2/ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ከተማ ነክ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 1120/98 ሚያዝያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም፣ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ደግሞ በመ/ቁ/ ዐ3383
No topics extracted.