No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ ወንድምአገኝ ዘውደ - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ 1/ አቶ ታፈሰ ወንድአፍራሽ 2/ ወ/ሮ በለጤ አምደመስቀ ል ሁለም ቀርበዋል 3/ ወ/ሮ ቆንጅት ምንዲሁን
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የኑዛዜ አፃፃፍ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ አመልካች ሟች ውብዬ ምንዲሁን የተውት ኑዛዜ እንዱፀድቅላቸው ለፍ/ቤቱ አመልክተው ኑዛዜው ተረጋግጦ ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ በኋላ የአሁኖቹ ተጠሪዎች ኑዛዜው ሃሰተኛ ነው፤ ተናዛዥዋ ራሣቸውን በሣቱበት ጊዜ የተደረገ ነው፤ ሟች መፃፍ የሚችለ ሆነው ሣለ በአሻራቸው መፈረማቸው ኑዛዜውን እንዲላደረጉ ያሣያል፤ በኑዛዜው በግልጽ አልተነቀልንም በማለት ኑዛዜው ውድቅ እንዱደረግ አቤቱታቸውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት አቅርበዋል። አመልካችም ቀርበው ኑዛዜው ውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ነው፤ ሟች በአሻራ ቢፈርሙም በውል አዋዋይ እና በምስክሮቹ ፉት ስለተደረገ ተገቢ ነው፤
ተጠሪዎች ተወላጆች ስላልሆኑ ከውርስ የተነቀለበት ምክንያት ሉገለፅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ኑዛዜው በታይþ ተጽፍ በምስክሮች ፉት ተነቦ ምስክሮችም ወዱያው መፈረማቸውን፣ ምስክሮቹ ችልታ ያላቸውና አማርኛ ቋንቋም እንደሚችለ፣ ሟችም ፊርማቸውን እንዲኖሩበት ተረጋግጧል፤ የምስክሮቹም ብዛት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 መሰረት በቂ ነው፤ የሟች የአእምሮ ሁኔታ ደህንነትን በተመለከተ ኑዛዜውን ያስፈፀሙት ኃላፉ በምስክርነት ተጠርተው አረጋግጠዋል፤ ስለዚህ ኑዛዜው የሚነቀፍበት ምክንያት ስለላለ የቀድሞው ውሣኔ አይሻርም በማለት የተጠሪዎችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል።
ይህንን ውሣኔ በመቃወም ተጠሪዎች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 መሰረት ግልጽ ኑዛዜ በ2 ምስክሮች መፈረሙ በቂ የሚሆነው ከምስክሮቹ አንደ ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው አካል ከሆነ ብቻ ነው። በኑዛዜው ላይ ከፈረሙት ሁለት ምስክሮች ውስጥ አንዲቸውም የውልና ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ ስላልሆኑ ኑዛዜው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 የተቀመጠውን መስፈርት አያሟላም ስለሆነም አመልካች የሟች ውብዬ ምንዲሁን የኑዛዜ ወራሽነት መብት የላቸውም ሲል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል።
አመልካችም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። የአመልካች አቤቱታም ኑዛዜው የተደረገው ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ስራውን በሚያካሂድበት በአ/አበባ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በመሆኑ በበቂ ምስክር ተረጋግጧል፤ ሟች ኑዛዜውን ያደረጉትም በነፃ ፍላጎታቸው ነው የሚል ነው። ተጠሪዎችም ቀርበው ኑዛዜው በሕግ የተመለከተውን ስርዓት አልተከተለም፤ ሟች ኑዛዜውን የሰጡት ጤነኛ በነበሩበት ሰዓት አልነበረም ሟች የተማሩ ስለነበሩ በጣት መፈረማቸው በጠና መታመማቸውን ያሣያል በማለት ተከራክረዋል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትና ይህም ችልት አቤቱታው ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱጣራ ያደረገበት ነጥብ ሟች ውብዬ ያደረጉት ኑዛዜ በሕጉ ላይ የተመለከተውን መስፈርት ያሟላል አያሟላም የሚለው ነው። ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ግልፅ ኑዛዜ መሆኑ ያላከራከረ ጉዲይ ነው። ግልጽ ኑዛዜ ሉያሟላ የሚገባው ስርዓቶች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 ሥር ተዘርዝረዋል። ይኸውም 1ኛው ኑዛዜው በ4 ምስክሮች ፉት መነበብ ያለበት መሆኑ፣ ይህም ስርዓት መፈፀሙና የተፃፈበት ጊዜ በኑዛዜው ላይ መመልከቱ፣ ተናዛዥና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዱያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረጋቸው መረጋገጡ አስፈላጊ ነው። በሟች ተሰጠ የተባለው ኑዛዜም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት የተደረገ፣ ሁለት ምስክሮች የፈረሙበት፣ ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ኑዛዜውን አረጋግጦ የፈረመበት፣ ኑዛዜው በምስክሮች ፉት ስለመነበቡ የሚገልጽ እና ተናዛዥዋ የጣት አሻራቸውን ምስክሮቹ ደግሞ ፊርማቸውን ያኖሩበት መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
881 ሥር የተመለከቱትን ስርዓቶች ያሟላ ነው። የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ኑዛዜው የህጉን ሥርዓት አልተከተለም ያለው በኑዛዜው ላይ የተመለከቱት ሁለት ምስክሮች ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጣቸው ሰዎች አይደለም በማለት ነው። በእርግጥ ምስክሮች ተብለው የተፃፈት ሁለት ሰዎች ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጣቸው ለመሆኑ የሚያመለክት ነገር የለም። ነገር ግን ኑዛዜው የተደረገው ከሁለቱ ምስክሮች በተጨማሪ ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ፉት፣ ስራውን በሚያካሂድበት ክፍል ነው። ምንም እንኳን እኚህ ሰው ምስክር ተብለው ባይገለፁም ሟች ኑዛዜውን በነፃ ፈቃዲቸው ሲሰጡና ኑዛዜውም ሲነበብ አይተው በኑዛዜው ላይ ፈርመዋል። የምስክሮች ዋና አስፈላጊነትም ኑዛዜ አድራጊው ኑዛዜውን በነፃ ፍላጎቱ እና በትክክለኛ አእምሮው የሰጠ መሆኑንና የኑዛዜ ቃለም የእርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ይህንን ደግሞ ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው አረጋግጠው ፊርማቸውን ያኖሩ በመሆኑ ምስክር ተብለው ስማቸው ባለመገለፁ ብቻ ምስክር አልነበሩም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም። ከምስክሮቹ አንደ ደግሞ ዲኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ከሆነና ኑዛዜው ይኸው ሰው ስራውን በሚያካሂድበት ክፍል ከሆነ ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ መሆናቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 882 ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም ሟች አደረጉ የተባለው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት ያሟላ በመሆኑ አመልካች የሟች ውብዬ ምንዲሁን የኑዛዜ ወራሽ አይደለም በማለት የተሰጠው ውሣኔ ስህተት ነው።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 473ዐ7 በዐ1/ዐ9/99 የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 31ዐ22 በ28/ዐ6/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ8ዐ63 በ4/ዐ8/98 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል፤ ሟች አደረጉት የተባለው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት ያሟላ በመሆኑ አመልካች የሟች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።