No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሻ/ባሻ ገዛኸኝ ድልነሣው - ቀረበ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ተዋበች ደመቀ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን በአብላጫ ድምጽ ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ላቀርብ የቻለው በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን የንብረት ክፍፍል በሚመለከት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 27393 መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት የአሁን አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ ነው።
ጉዲዩም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው።
የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከፍቺ ውሣኔ ቀጥል የንብረት ክፍፍል ይደረግለት ዘንድ የንብረት ዝርዝር አቅርቧል። ከቀረበውም የንብረት ዝርዝር መካከል ለዚህ ጉዲይ መነሻ የሆነው በወረዲ 28 በቀበላ ዐ1 በቤት ቁጥር 61ዐ የተመዘገበው ቤት የጋራ በመሆኑ እኩል እንካፈል ዘንድ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ዲኝነት በመጠየቁ ነው።
የአሁን መልስ ሰጭም በተጠሪነታቸው ቀርበው ይኸው ንብረት ከጋብቻ በፉት ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ጋራ ያፈሩትና የግል ንብረታቸው የሆነውን በወረዲ 28 ቀበላ ዐ1 በቤት ቁጥር 419 በካርታ ቁጥር ኮ/ዐ1/152/73 የተመዘገበውን ቤት በመሸጥ በምትኩ ይኸው ክርክር ያስነሣው ቤት በግዥ የተገኘ በመሆኑ የግል ሀብቴ እንጅ የጋራ ሀብት ባለመሆኑ የቀረበው የክፍፍል ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም በኮ/መ/ቁ. 12164 ታህሣሥ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በዋለው ችልት የቤት ቁጥር 61ዐ የተሰራው አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ መሥርተው አብረው ሲኖሩ የነበሩበትና በቤት ቁጥር 419 የተመዘገበውን ቤት በመሸጥ ስለመሆኑ በግራ ቀኙ የተካደ ነጥብ አይደለም፤ በተጠሪ በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች እንዲረጋገጡት የቤት ቁጥር 61ዐ መኖሪያ ቤት የተሰራው በቤት ቁጥር 419 በተመዘገበው ቤት የሽያጭ ገንዘብ ሲሆን ፤
የቤት ቁጥር 419 የአሁኑ ተጠሪ የግል ንብረት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል፤ አመልካችም ይኸው በሽያጭ ገንዘብ የተሰራው የቤት ቁጥር 61ዐ ባልና ሚስቱ በጋብቻ አብረው በሚኖሩበት ጊዜ በግል ጥረታቸው ባገኙት ገቢ የተሰራ እና የተገዛ ስለመሆኑ አላስረዲም፤ ስለሆነም አመልካች የጋራ ሀብት እንደሆነ በመቁጠር የንብረት ክፍፍል ያቀረቡበት የቤት ቁጥር 61ዐ የተጠሪ የግል ሀብት በመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 58/1/ መሰረት የግል ሀብት እንጅ የጋራ ባለመሆኑ ይህንኑ ቤት አስመልክቶ ያቀረበው ክሱ ውድቅ ነው ሲል ወስኗል።
ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን በይግባኝ ደረጃ ካከራከረ በኋላ በኮ.ቁ. 44232 መስከረም 29 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ምንም እንኳን የአሁን መልስ ሰጭ ክርክር ያስነሣውንና በቤት ቁጥር 61ዐ የሚታወቀውን ቤት የገዙት የቀድሞ ቁጥሩ 419 የሆነውን መኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው መሆኑን በተሻለ ሁኔታ ቢያስረደም በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 58/2/ መሰረት በግዥ የተገኘው ቤት የግላቸው እንዱሆን በፍ/ቤት ወይም በወቅቱ እንደሚቻለው በቤተዘመድ ሽምግልና ጉባዓ አላስወሰኑም፤ ስለሆነም ተጠቃሹ ቤት የመልስ ሰጭ የግል ሀብት ነው ሲል የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ መድረሱ ውሣኔው ሕጉን በአግባቡ ያላገናዘበ ነው፤
ስለሆነም በአሁኑ አጠራር በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 19 ክልል ውስጥ በቤት ቁጥር 61ዐ ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት የጋራ ሀብት ነው፤ ከተቻለ ግራ ቀኙ በዓይነት እኩል ይካፈለ፣ ይህ የማይቻል ለመሆኑ ከተረጋገጠ ግን ከተስማሙ አንደ ለአንደ የግምቱን አጋማሽ ሰጥቶ ያስቀር፤ በዚህ ባይስማሙ ግን ከተስማሙ በጋራ ሸጠው፤ ካልተስማሙ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል ይካፈለ በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው የአሁን መልስ ሰጭ የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረቡት መሰረት ጠ/ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አከራክሯል። በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 27393 መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በዋለው ችልትም በጋብቻ ጊዜ በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ሀብት ይባልልኝ ብል ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርቦ እንዱፀድቅ ያስፈለገበት ምክንያት የጋራ ሀብትን እንደግል ሀብት በማስመሰል 3ኛ ወገኖችን የሚጎዲ ሁኔታ እንዲይፈጠር ለማድረግ ስለመሆኑ ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ረቂቅ - በ1992 ከታተመው የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ረቂቅ ማብራሪያ ላይ ለመረዲት ችለናል። ስለሆነም በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 58/2/ የተደነገገው የ3ኛ ወገኖችን መብት ለመጠበቅ ሲባል እንጅ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ለሚነሣ ክርክር አግባብነት የለውም። በመሆኑም ለክርክሩ መነሻ የሆነው በቁጥር 61ዐ የተመዘገበው ቤት የይግባኝ ባይዋ የአሁን መልስ ሰጭ የግል ሀብት እንጂ ከመልስ ሰጭው ጋር ሉካፈለት የሚገባ የጋራ ሀብት አይደለም በማለት ወስኖ አሰናብቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይም የቀረበው በዚህ አኳኋን የፋ.ጠ.ፍ/ቤት የሰጠው የሕግ ትርጓሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለበትን ክርክር በማቅረብ በሰበር ሰሚው ችልት እንዱታረምላቸው አመልካች ዲኝነት በመጠየቃቸው ነው።
መልስ ሰጭም ጠ/ፍ/ቤቱ በይግባኝ አይቶ የሰጠው ውሣኔ ትክክለኛውን የሕግ ትርጉም መሰረት በማድረግ ስለሆነ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
እኛም ጉዲዩን አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በዚህ ጉዲይ ክርክር ያስነሣው በቤት ቁጥር 61ዐ የተመዘገበው ቤት በፉት የአሁን መልስ ሰጭ የወ/ሮ ተዋበች ደመቀ የግል ሀብት የነበረው የቤት ቁጥር 419 ተሸጦ በግዥ የተገኘ ስለመሆኑ የማያከራክር የፍሬ ጉዲይ ስለመሆኑ በየደረጃቸው የተሰጡት የውሣኔ ግልባጮች አስረጂ ናቸው። በዚህ ጉዲይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ የተገኘውና በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ትርጉም የሚያሰጥ ሆኖ የተገኘው ከጋብቻ በፉት የነበረ ሀብት በመሆኑ የተነሣ የነበረን የግል ሀብት በመሸጥ ላላ ቤት በግብይት በግዥ በተገኘ ጊዜ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 58/2/ በተደነገገው መሰረት አለመፈፀም የሚያስከትለው ውጤት ምንድን ነው? የሚለው ነው።
በመሰረቱ ባል ወይም ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀጥለ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 57 ተደንግጓል። በዚህ አኳኋን የግል የነበረ ንብረት በግብይት የተነሣ ዓይነቱን ለውጦ በተገኘ ጊዜ የግል ሆኖ እንዱቆይ ለማድረግ በአንቀጽ 58 የተመለከተውን በመረዲት አስቀድሞ ሉፈፀም እንደሚገባ የሕጉ አደራደር ቅደም ተከተል ያስገነዝባል። በመርህ ደረጃ በአንቀጽ 58/1/ እንደተመለከተው ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ አንደ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሸጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ሀብቱ ይሆናል በሚል ከተቀመጠ በኋላ በዚህ ሁኔታ የተነሣ ንብረቱ የግል ይባልልኝ ብል 1ኛው ወገን ጥያቄ ሲያቀርብና ፍርድ ቤት ሲያፀድቀው ብቻ ነው በማለት በተለየ ሁኔታ አስቀምጧል። ይኸው በአንቀጽ 58/2/ መሰረት በስርዓቱ አለመፈፀሙ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ አንቀጽ 58 በእራሱ ገላጭ እንጂ ለትርጉም በር የከፈተ ሆኖ አይገኝም።
ድንጋጌው ግልፅነት ይጎድለዋል ከተባለም ድንጋጌዎችን እርስ በእርሣቸው አስተሳስረን ልንመለከት ይገባል ።
የአንቀጽ 57 እና 58 ርዔሰ ጉዲዮች ቁጥር 1 እና 2 በሚል የተያያዙ በመሆናቸው ከጋብቻ በፉት የነበረ ሀብት የግል ሆኖ የሚቀጥለው በማናቸውም ዓይነት ምክንያት ዓይነቱን ካልለወጠ እና ለውጦ ከተገኘም የግል ሀብት እንደሆነ ሉቀጥል እንደሚገባ፣ በዚህ መሰረት የግል ሀብት ሆኖ ሉቀጥል የሚገባው ግን በልዋጭ የተገኘው ሀብት የነበረውን የግልነት አቋም ይዞ እንዱቀጥል በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ እነዚህ ተያያዥነት ያላቸው ድንጋጌዎች በግልጽ ያመለክታለ። ይህን በአንቀጽ 58/2/ የተመለከተውን ማሟያ አለመተግበር የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት ወሰን በእነማን ላይ ያተኮረ ነው የሚለውም ቢሆን አሻሚ በመሆኑ ትርጉም ያስፈልገዋል፤ ለመተርጎምም የሕግ አውጭውን ሀሣብ መፈለግ ይበጃል ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም። በመሰረቱ ከትርጉም ዘዳዎች አንደ የሕግ አነጋገር ግልጽ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሕጉን እንዲለ ሥራ ላይ ማዋል እንጅ በትርጉም ሽፊን ከሕጉ ይዘት መራቅ የሚያስፈልግ አይደለም።
ይተርጎም እንኳ ቢባል የሕግ አውጭው ሀሣብ ምን ነበረ ከሚለው መነሻ ይልቅ የሕጉን ድንጋጌዎች እርስ በእርሣቸው አስተሳስሮ ማየቱ ለትክክለኛው ትርጓሜ የሚያደርስ ነው። በዚህም መሰረት በዚሁ ሕግ አንቀጽ 62/2/ "----በዚህ ሕግ አንቀጽ 58 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው ካልተባለ በቀር ባልና ሚስቱ ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁለ የጋራ ሀብታቸው ይሆናል” በማለት የባልና ሚስትን የጋራ ሀብት በሚደነግገው ክፍል መጠቀሱ በአንቀጽ 58/2/ የተመለከተውን ሥርዓት አለመፈፀም የሚያስከትለው ውጤት የተጋቢዎች የጋራ ሀብት የቱ ነው ለሚለው ጉዲይ ተፈፃሚ መሆኑን በግልጽ የሚያመለክት ነው።
ስለሆነም የአሁን መልስ ሰጭ ከጋብቻ በፉት የነበራቸውን የግል ሀብት በቁጥር 419 የተመዘገበውን ቤት በጋብቻ ላይ እያለ በመሸጥ በቤት ቁጥር 61ዐ የተመዘገበውን ቤት ሲገዙ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 58/2/ ሆነ በጊዜው ለጉዲዩ ተፈፃሚነት በነበረው ሕግ መሰረት በግብይት የተገኘው ቤት የግል ሆኖ ይቀጥል ዘንድ አቅርበው በሚመለከተው ክፍል አለማፀደቃቸው እስከተረጋገጠ ድረስ ክርክር ያስነሣው እና በቁጥር 61ዐ የተመለከተው ቤት የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ 1/ በድሮው አጠራር በወረዲ 28 ቀበላ ዐ1 በአሁኑ አጠራር ደግሞ በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 19 ክልል ውስጥ የሚገኘው እና በቤት ቁጥር 61ዐ የተመዘገበው ቤት የአመልካችና የመልስ ሰጭ/ የባልና ሚስት/ የጋራ ሀብት ስለሆነ እንደ ከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ እኩል ይካፈለ።
2/ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 12164 ታህሣሥ 24 ቀን 1998 ከሰጠው ውሣኔ ይህንን ቤት በሚመለከት ብቻ የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 27393 መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ ተሽረዋል።
3/ የከፍተኛው ፍ/ቤት በኮ.ቁ. 44232
No topics extracted.