No summary available.
መ/ቁ. 366ዐ4 ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ጽጌ መንግሥቱ - ጠበቃ ሰልሞን ገ/ሚካኤል ቀረበ ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ ለቀረበው ይግባኝ መነሻ የሆነው ጉዲይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪዎች በአመልካች አቤቱታ አቅራቢነት ተሰጥቶ የነበረው የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝላቸው መቃወሚያ አቅርበዋል። ለመቃወሚያቸው መሰረት አድርገው የጠቀሱት አመልካች የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዱሰጣት በአስረጂነት ያቀረበችው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት አያሟላም፤ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም፤ የሚል ነው። ፍ/ቤቱ አመልካችን አስቀርቦ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ኑዛዜው የኑዛዜ አድራጊዋ ወራሾች የሆኑትን ተቃዋሚዎችን ያለምንም ምክንያት ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረው ውሣኔ ተሰርዟል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ይህን ውሣኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ በዚህ ይግባኝ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቷል። ፍ/ቤቱም ኑዛዜው የሕጉን መስፈርት ያሟላ ሕጋዊ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን /ይግባኝ የተባለበትን/ ውሣኔ የሻረ ሲሆን በመቀጠልም ተጠሪዎችም እንደአመልካች ወራሾች ስለሆኑ የኑዛዜ አድራጊዋን ሐብት እኩል ይካፈለ በማለት ወስኖአል።
በመጨረሻም ይህን ውሣኔ በመቃወም ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ክርክሩን ከሰማ በኋላ ኑዛዜው ተጠሪዎች በዝምታ ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ የሚፀናበት የሕግ ምክንያት የለም፤ የውርስ ሃብቱን ግራ ቀኝ ወገኖች እኩል ይካፈለት መባለ ግን ትክክል ነው በማለት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አሻሽሎል። የሰበር አቤቱታው የቀረው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች ከስር ጀምራ አቅርባ ስትከራከርበት የቆየችው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ እንደተመለከተው ተጠሪዎች ኑዛዜውን በመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት ኑዛዜ ከተደረገ ከ16 /አስራ ስድስት/ ዓመት በኋላ ነው። ኑዛዜው ሟች ከሞቱ /ኑዛዜ አድራጊዋ ከሞቱ/ በኋላ በ8ዐኛው ቀን ሲፈስ ተጠሪዎች ተገኝተው እንደሰሙ በምስክር ስለመረጋገጡ በውሣኔው ላይ ተገልጿል።
እንደምንመለከተው ተጠሪዎች የኑዛዜውን መደረግ /መኖር/ ብቻ ሣይሆን አመልካች በኑዛዜው መሰረት ተጠቃሚ ሆና መቆየትዋን ጭምር አውቀው ለብዙ ዓመታት በዝምታ ማለትም ሣይቃወሙ ቆይተዋል። አመልካች መቃወሚያው በይርጋ ቀሪ ሆኗል የምትልበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው።
ኑዛዜን በመቃወም የሚቀርበው ማናቸውም መቃወሚያ መታየት ያለበት አግባብነት ካላቸው የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ነው። በዚህ መዝገብ ለተያዘው ክርክር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንደ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 973 የተመለከተው ነው። ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል መቃወሚያ ያላቸው ኑዛዜው ሲነገር /ሲፈስ/ የነበሩትን ሰዎች የሚመለከት ነው። ይህም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከለ ሰዎች ኑዛዜው አይፀናም ወይም በኑዛዜው የተነገረ ቃል አይፀናም የሚለትንና የመሳሰለትን በመቃወም ክስ የሚያቀርቡ ቢሆን ይህን ማድረግ ያለባቸው ኑዛዜው ከተነበበበት አንስቶ እስከ አስራ አምስት ቀን ድረስ እንደሆነ ያመለክታል። ከዚህም በተጨማሪ ክስን የማቅረብ ሃሣብ መግለጫው በጽሐፍ ካልሆነና ለአጣሪው ወይም ለዳኞች ወይም በውርስ ላይ የተነሣውን ነገር ለመጨረስ ለተመረጡት የሽምግልና ዳኞች እንዱደርስ ካልተደረገ በቀር እንደማይፀና /መቃሚያ አለ ለማለት እንደማይቻል/ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973/2/ ተደንግጓል። በመጨረሻም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ እስከ ሦስት ወር ድረስ ክስ ካልቀረበ መብቱ ከነጭራሹ እንደሚቀር በንኡስ ቁጥር /3/ ተመልክቷል።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው ተጠሪዎች ኑዛዜው ሲነገር /ሲፈስ/ በቦታው እንደነበሩ /እንደሰሙ/ አላከራከረም።
መቃወሚያ ያቀረቡት በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 973 በግልጽ የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ እንዲልሆነም ተረጋግጧል። በልላም በኩል ኑዛዜው ሲነበብ አልነበሩም ተብልም ቢሆን ኖሮ መቃወሚያውን ሣያቀርቡ የቆዩት ለ16 /አስራ ስድስት/ ዓመታት ያህል በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 974 የተቀመጠው የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ይከለክላቸዋል።
No topics extracted.
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 974/2/ በግልጽ እንደተመለከተው ኑዛዜው ከፈሰሰበት /ከተነበበት/ ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለኑዛዜው መጽናትም ሆነ ስለክፍያው ድልድል መቃወሚያ ማቅረብ አይቻልም። ሲጠቃለል ተጠሪዎች ኑዛዜው ሲነበብ /ሲፈስ/ አልነበሩም ወይም አልሰሙም አልተባለም እንጂ ተብልም ቢሆን ኖሮ በመጨረሻ ያቀረቡት መቃወሚያ በይርጋ ቀሪ ከመሆን የሚድን አይደለም። በመሆኑም አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም።
በዚህ ረገድ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ