No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 347ዐ3 ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- እንደሻው ፍቃደ - ቀረበ።
ተጠሪዎች፡- እነ ወንድማገኝ ፍቃደ /ሰባት ሰዎች/ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ነው። አመልካቹ በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው ይዘውት ከሚገኘው የውርስ ንብረት ድርሻውን እንዱያካፍለት ነው። ከተጠሪዎች መሃል ስድስቱ ለክሱ በሰጡት መልስ ከሣሹ ልክ እንደኛው ወራሽ ነው፤ ድርሻውን ለማካፈል ዝግጁ ነን፤ በእርግጥ የጠየቀው የውርስ ሃብት ግምት የተጋነነ ነው በማለት ሲከራከሩ አንደ ደግሞ ጉዲዩ በሽምግልና እየታየ ነው የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከተመለከተ በኋላ ጉዲዩ ውርስን የሚመለከት በመሆኑ ከሣሽ የውርስ ሃብቱ ይጣራልኝ የሚል ክስ በቅድሚያ ሉያቀርብ ይገባል የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ሰርዟል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ብይን ጉድለት የለበትም ብሎል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ታሕሣሥ 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የውርስ ማጣራት ስርዓት አልተካሄደም በሚል ምክንያት አመልካች ያቀረበው የውርስ ሃብት ልካፈል ክስ ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ብይን እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተመለከተው በአመልካች የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ግልጽ ነው። ክሱን የመሰረተው በወንድሞቹ እና እህቶቹ ላይ ሆኖ በወራሾች መካከል ካልተከፊፈለው የሁለም አባት ንብረት ላይ የውርስ ድርሻውን እንዱያካፍለት ነው።
የክፍያ ጥያቄ ያቀረበባቸውን የውርስ ሃብቶችም /ንብረቶች/ በክስ ማመልከቻው ላይ ዘርዝሮ ስለማቅረቡ አቤቱታ በቀረበበት ብይን ላይ ተመልክቶአል። አመልካች ተጠሪዎችን የከሰሰበት ምክንያትም ግልጽ ነው። ይኸውም የውርስ ሃብቶቹን በእጃቸው ይዘው ስለሚገኙ ነው። ተጠሪዎች ለስር ፍ/ቤትም ሆነ ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት መልሳቸው ንብረቶቹን አልያዝንም /በእጃችን አይገኙም/ የሚል ክርክር አላነሱም። አመልካች ወራሽ አይደለም ወይም ከተባለት ንብረቶች የሚያገኘው መብት የለም የሚል ክርክርም የላቸውም። ይልቁንም በክሱ የተጠየቀውን በመቀበል ለአመልካች ድርሻውን ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
እንደምንመለከተው በዚህ ጉዲይ ወራሾቹም ሆኑ የውርስ ሃብቶቹ በግልጽ ተለይተው ታውቀዋል። ሳይከናወን የቀረው ንብረቶቹን በወራሾቹ መካከል የመከፊፈለ ጉዲይ ነው። በእርግጥ ከውርሱ ሃብት የሚከፈል ዔዲ እንዲለና በአመልካች ክስ የተመለከተው የንብረት ግምት የተጋነነ እንደሆነ በተጠሪዎች ክርክር ተገልጾአል። እንደተባለው ከውርስ ሃብቱ ላይ የሚፈለግ ዔዲ ካለ ክሱ በቀረበበት ፍ/ቤት መሪነት በማስረጃ ተጣርቶ ሉታወቅ የሚችል ነው። ተጠሪዎችም በእርግጥ ያልተከፈለ እና በትክክልም ከውርስ ሃብቱ ላይ የሚከፈል ዔዲ አለ ካለ ይህንኑ በማስረጃ አስረግጠው ለፍ/ቤቱ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከዚህ ውጪ ግን ዔዲ አለ በመባለ ምክንያት ሕግና ስርዓት ተከትል የቀረበው ክስ የሚዘጋበት የሕግ ምክንያት የለም።
አመልካች ክስ በመሰረተበት /ለክሱ መነሻ በሆነው/ ሃብት ላይ ጥቅም ወይም መብት እንዲለው አረጋግጦ ነው /የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 33/። ክሱ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በጉዲዩ ላይ የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የለውም አልተባለም። ፍ/ቤቱ ክሱን የሰረዘው የዲኝነት ስልጣን የለኝም በሚል ቢሆንም፤ ለዚህ የሰጠው ምክንያት ግን የውርስ ማጣራት ስርዓት አልተካሄደም የሚል ነው። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የውርስ ሃብት ክፍፍልን መነሻ የሚያደርግ ክስ በውርስ አጣሪ በኩል ካላለፈ በቀጥታ ወደ ፍ/ቤት አይቀርብም የሚል አስተሳሰብ ወይም አካሄድ የተያዘ መሆኑን ነው።
በእርግጥ በወራሾች በራሳቸው ወይም በተመረጠ በልላ ሰው አማካይነት ውርስ እንደሚጣራ በሕጉ ተመልክቶአል።
ከውርስ ማጣራት ተግባራት አንደ የውርስ ሃብቱን መከፊፈል እንደሆነም ልብ ልባል ይገባል። ይህ እንግዱህ አንደ የውርስ ሃብት የሚከፊፈልበት መንገድ ነው ማለት ነው። በልላ በኩል ግን ድርሻዬን አላገኘሁም የሚል ወራሽ የውርስ ሃብቱን በያዘው ሰው ላይ በቀጥታ ክስ የመመስረት መብት የለውም ወይም ሕጉ ከልክልአል ለማለት የሚቻል እንዲልሆነ መገንዘቡ ተገቢ ነው። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው የውርስ ሃብቶቹ በተጠሪዎች እጅ ተይዘው እንደሚገኙ አላከራከረም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
አመልካችም ከእነዚህ ሃብቶች ላይ ድርሻውን እንዱያገኝ ነው የጠየቀው። በመሆኑም እንደማንኛውም የፍትሐብሕር ክርክር ታይቶ እና በማስረጃ የሚጣራ ካለም ተጣርቶ ሉወሰን ሲገባ የውርስ ማጣራት ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ተደርጎ መወሰደ ትክክል አይደለም። ፍ/ቤቱ የዲኝነት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 49517 ሐምል 1ዐ ቀን 99 ዓ.ም. ተሰጥቶ የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 325ዐ8 ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተከፈተው መዝገብ በመቀጠል በግራ ቀኝ ወገኖች የሚቀርብለትን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የመሰለውን ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341/1/ መሰረት ይመለስለት ብለናል።
ይፃፍ።