No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ኤርሚያስ ሙለጌታ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- በከልቻ ትራንስፖርት አ/ማ - ይልማ ገመቹ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው የሰበር አቤቱታ አመልካች በተጠሪ ተቀጥሮ በሾፋርነት ሲሰራ በነበረበት ጊዜ ከጅቡቲ አስጭኖ ከመጣው የአርማታብረት ውስጥ 2ዐ ጥቅል ወይም 3ዐ5 ኩንታል አጉድል ተገኝቶአል በሚል ተጠሪ የመሰረተውን ክስ መነሻ በማድረግ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው ተጠሪ የብረቱን ዋጋ በማስላት እንዱከፈለው አመልካችንና ዋሱ ነች የተባለችውን ሰው አጣምሮ የከሰሰ ሲሆን፣ ተከሣሾችም የመከላከያ ክርክራቸውን አቅርበዋል። ክሱ የቀረበለት የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ አመልካች ብር 11,250(አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ከወለድ እንዱሁም ከዲኝነትና ከብር 3ዐዐ.ዐዐ(ሦስት መቶ ብር) ኪሣራ ጋር ይከፈል፤ እሱ ባይከፍል ዋሱ ትክፈል በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ላይ እንደአግባቡ ይግባኝ እና አቤቱታ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት መደበኛ ችልት እና የሰበር ችልትም ውሣኔውን አፅንተዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች ሐምል 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ ተፈፅሞአል የሚለውን የሕግ ስህተት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። በበኩላችንም ይህን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው አመልካች ደረሰ ለተባለው ጉድለት ተጠያቂ ነው መባለ አግባብ ነው ወይ?
በሚለው ነጥብ ላይ በመመስረት ነው።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር በዝርዝር ተመልክተናል። በዚህ ሰበር ችልት ከተደረገው ክርክር በተለይ መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ የሚቃወምበት ዋናው ምክንያት ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር በኔ በኩል ጉድለት እንዲልተገኘ ተረጋግጦ ውሣኔ ተሰጥቶአል። ክርክሩ የተካሄደው ተጠሪ ጉድለቱን መሰረት በማድረግ የሥራ ውላ በማቋረጡ ወደ ሥራዬ እንድመለስ በሥራ ክርክር ችልት ክስ በመመሥረቴ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም የስራ ውለን ለማቋረጥ የሚያስችል ጥፊት እንዲልተፈፀመ አረጋግጦ ውሣኔ ሰጥቶአል። በመሆኑም በተመሣሣይ ጉዲይ በድጋሚ ክርክር ላደረግ አይችልም። በማለት ነው። ተጠሪ ደግሞ ቀደም ሲል ቀርቦ ክርክር የተደረገበት ጉዲይ የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። በዚህ ክርክር ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች የሥራ ውል ሉያቋርጥ የሚችል ጥፊት ፈፅሞአል ወይስ አልፈፀመም የሚል ነው። በአሁኑ ጉዲይ የተያዘው ጭብጥ ግን አመልካች በክሱ የተመለከተውን ገንዘብ ለመክፈል ይገደዲል ወይስ አይገደድም? የሚለው ነው። በመሆኑም ጉዲዩቹ ተመሣሣይ አይደለም በማለት ተከራክሮአል።
እንደምንመለከተው በዚህ ሰበር ችልት ውሣኔ ላሰጥበት የሚገባው ጭብጥ ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰርተው የገንዘብ ይከፈለኝ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5 ከተቀመጠው ድንጋጌ አንፃር ታይቶ ውድቅ መሆን የሚገባው ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
በፍሬ ነገር ረገድ የቀረበው ክርክር እንደሚያመለክተው ለሁለቱም ክርክሮች መነሻ የሆነው አመልካች ያሽከረክረው በነበረው መኪና ላይ ተጭኖ የነበረው የአርማታ ብረት ጎድል ተገኝቶአል የሚለው ነው። ይህም ሆኖ ግን የመጀመሪያው የሥራ ክርክር በመሆኑም የታየው፤ በስራ ክርክር ችልት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፍታብሕር ችልት ነው የታየው ይህ በመሆኑም ነው በአመልካች የተነሣው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5 ላይ የተመሰረተው መቃወሚያ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚል አከራካሪ ጭብጥ ሉያዝ የተቻለው።
ይህ የሰበር ችልት በሰበር መ.ቁ. 3671ዐ ተመሣሣይ ክርክር ቀርቦለት በሕጉ አተገባበር ረገድ ትርጉም ሰጥቶአል። በዚህም በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚካሄደው የሥራ ክርክር የሚያዘው ጭብጥ አሰሪው የገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ /ክስ/ በሰራተኛው ላይ ባቀረበ ጊዜ ከሚያዘው ጭብጥ ጋር አንድ አይነት አይደለም እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በመጨረሻም እንደአሁኑ አመልካች በአሰሪው በጉድለት ይፈለጋል የተባለውን ገንዘብ እንዱከፍል ክስ የቀረበበት ሰራተኛ ቀደም ሲል ተካሂድ የነበረውን የሥራ ክርክር መሰረት በማድረግ ያቀረበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5 ላይ የተመሰረተው መቃወሚያ ውድቅ አድርጎአል።
የሰበር ችልቱ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በተመሣሣይ ሁኔታ በተሰየመው ችልት እስካልተለወጠ ድረስ በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፋዳራል ወይም የክልል ፍ/ቤት ላይ አስገዲጅነት እንደሚኖረው የፋዳራል ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2/1/ ተደንግጎአል። በሰበር መ.ቁ. 3671ዐ የተሰጠው የሕግ ትርጉም አልተለወጠም። በመሆኑም በዚህ መዝገብ በቀረበው ክርክርም የተለየ የሕግ ትርጉም የሚሰጥበት አግባብ የለም። አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የሚያገኝበት ምክንያት የለም።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ4ዐ76 ሚያዝያ 5 ቀን 99 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ፣ የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 53326 ህዲር 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ.ቁ. 61371 ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቶዋል።
አመልካች በዚህ ሰበር ችልት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግ ምክንያት የለም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።