No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አመልካች፡- የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፊፈያ ድርጅት - ነገረ ፈጅ አቶ ጌታሁን ተስፊዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ንግሥት ለጥይበለ - ጠበቃ አቶ አበራ ታደሰ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የክርክሩ ምክንያት የሥራ ክርክር ጉዲይ ሆኖ ተጠሪ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበችው ክስ ያለአግባብ የሥራ ውል የተቋረጠ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍል ወደ ሥራ እንድመለስ አሉያም ተገቢ ክፍያዎች ተከፍል እንድሰናበት ይወሰንልኝ የሚል ነው።
አመልካች ከሳሽ የሥራ መሪ እንጅ ሰራተኛ አይደለችም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር በማቅረብ መልስ በመስጠት ተከራክሯል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ወጪ ነው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልአት ወደ ሥራ ትመለስ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን በማጽናቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ጥር 20 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበውን ቅሬታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር ሰምተናል። ጉዲዩ በሰበር ሰሚ ችልት እንዱታይ የቀረበው ተጠሪ የሥራ መሪ ናቸው ወይንስ አይደለም?
የሚለውን ነጥብ ለመመርመር በመሆኑ ይህንኑ ከግራ ቀኙ ክርክርና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
ከግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር መረዲት የተቻለው ተጠሪ የድርጅቱ የሀገር ውስጥ ዔቃ ግዥ ዋና ክፍል ኃላፉ በመሆን እንዱሁም በተጨማሪነት የውጪ ሀገር ዔቃ ግዥ ዋና ክፍልና የሽያጭ ዋና ክፍልን የሚያካትተውን የንግድ መምሪያ ኃላፉነትን ደርበው ይሰሩ የነበረ መሆኑን ነው። ተጠሪ በእነዚህ መደቦች በኃላፉነት ስለመሥራታቸው አልተካደም። የሥራ መደቡ ዋና ተግባራት ምንድናቸው የሚለው ከተጠሪ የሥራ መዘርዝር /job description/ ሲታይ በአጠቃላይ በድርጅቱ መመሪያ መሰረት ማስተባበር፣ መምራት፣ ማደራጀት እና መቆጣጣር እንዱሁም ዔቅድና በጀት ዝግጅት ላይ መሳተፍ እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን በድርጅቱ ኅብረት ስምምነት አንቀጽ 3 ንዐስ ቁጥር 3.3 እንደተመለከተው ስምምነቱ የዋና ክፍልችንና የማምረቻ ኃላፉዎችን እንደማይጨምር በግልጽ ተመልክቷል። ተጠሪም ከላልች ሰራተኞች በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የድርጅቱ ኃላፉነት የተሰጠች መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንፃር ተጠሪ ሥራን የማቀድ፣ የመምራት፣ የመቆጣጠር፣ የማደራጀትና የማስተባበር ተግባራትን የሚያከናውኑ መሆኑን ከክርክሩም ሆነ ከቀረቡ ሰነድች መረዲት ተችሎል። ስለዚህ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 በአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2 እንደተሻሻለው ተጠሪ ከሥራ ተግባራቸው አንፃር የሥራ መሪ እንጅ ሰራተኛ አይደለም። በአዋጁ ለሥራ መሪ የተሰጠው ትርጉም “የሥራ መሪ የሚባለው በሕግ ወይም እንደ ድርጅቱ የሥራ ፀባይ በአሰሪው በተሰጠው ውክልና ሥልጣን መሰረት የሥራ አመራር ፖሉሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ከዚህ በተጨማሪ ወይም እነዚህኑ ሳይጨምር ሰራተኛን መቅጠር ማዛወር የማገድ የማሰናበት የመመደበ ወይም የሥነ ሥርዓት እርምጃ የመውሰድ ተግባሮችን የሚያከናውንና የሚወስን ግለሰብ ነው ይላል።” ከዚህ አንፃር የተጠሪ የሥራ ተግባር በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው የድርጅቱን ዋና ክፍል ሥራ በኃላፉነት መምራት፣ ማደራጀት መቆጣጠርና ማስተባበር ከመሆኑ አንፃር በሕጉ ትርጉም ከተሰጠው የሥራ ዘርፍ የሚመደቡ በመሆናቸው የሥራ መሪ ናቸው እንጅ፤ ሰራተኛ አይደለም። የመንግስት የልማት ድርጅቶች የቦርድም፣ የማናጅመንት አባላት ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ እኔን አይጨምርም በማለት ከተጠሪ የቀረበውን ክርክር በተመለከተ መመሪያው ለቦርድና ማናጅመንት አባላት ሉከፈል የሚገባውን ክፍያ አስመልክቶ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ እንጅ ለተያዘው ጉዲይ ተፈፃሚ ስለማይሆን ክርክሩ አግባብነት የላለው ነው። በአጠቃላይ ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች እና በሰበር መ/ በተመሳሳይ ጉዲይ ትርጉም የተሰጠበት በመሆኑ ተጠሪ የሥራ መሪ እንጅ ሰራተኛ ባለመሆናቸው ጉዲያቸው በሥራ ክርክር ችልት ክስ ለማቅረብም ሆነ ክርክር ለማካሄድና ዲኝነት ለማግኘት የሚችለበት የሕግ አግባብ ስለላለ የመጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በሕግ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ውሳኔ ነው ብለናል።
ይፃፍ።
ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆናቸው ጉዲያቸው በልላ ሕግ ከሚታይ በቀር በሥራ ክርክር ችልት ላታይ አይችልም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.