No summary available.
ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ናዝሬት ሳሙና ፊብሪካ ተጠሪ፡- ዘውዳ ኃ/ማሪያም /አቶ/ መዝገቡን መርምረን የሚተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተደረገውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ስራዬን በገዛ ፈቅዳ ለቅቄ ስራ ያቋረጥኩ ስለሆነ በሕጉ መሰረት የስንብት ክፍያና የአገልግልት ክፍያ ይከፈለኝ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሽ በፊብሪካው ውስጥ ከ20/ሃያ/ ዓመት በላይ ያገለገለና በፈቃደ ስራውን የለቀቀ በመሆኑ እድሜው ለጡረታ ሲደርስ የጡረታ አገልግልት አበል ለእድሜልክ ማግኘት ይችላል። ስለዚህ የአገልግልት ክፍያ የማግኘት መብት የለውም በማለት ተከራክሮአል። ክሱን ያስሰተናገደው ፍ/ቤትም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ፣የአመልካች ክርክር በመቀበል ተጠሪ የጠየቀውን ክፍያ ማግኘት አይችልም በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ይግባኝ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በወረዲው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ነሐሴ 5 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ባለመቅረቡ ክርክሩ የተሰማው እሱ በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ የጡረታ የተጠበቀ ቢሆንም፤የስንብት ክፍያም ይከፈለው በሚል የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የስራ ውል የተቋረጠው ተጠሪ በራሱ ፈቃድ ስራውን በመልቀቁ ምክንያት ነው። ተጠሪ ወደ ክስ ያመራውም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 39 መሰረት የስራ ስንብት ክፍያ ለመክፈል አመልካች ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው። አመልካች የስራ ስንብት ክፍያው መክፈል የለበኝም የሚለው ተጠሪ ከ20/ሃያ/ ዓመት በላይ ያገለገለ በመሆኑ በጡረታው ሕግ መሰረት የጡረታ አገልግልት አበል የማግኘት መብት አለው የሚል የመከራከሪያ ነጥብ በማንሳት ነው። በእርግጥም የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም የጡረታ መብት የላለውና በጡረታ ሕግ የተመለከተው መደበኛ የጡረታ እድሜ ደርሶ ከስራ የተገለለ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንዲለው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(2)(ሰ) ተመልክቶአል። ሰራተኛ የስራ ውለ ሲቋረጥብት የስራ ስንበት ክፍያ የሚፈጸምለት ሉቋቋመው የማይችል ድንገተኛ የገንዘብ ችግር እንዲይገጥመው ነው። ይህ ከሕጉ በስተጀርባ ያለው አስተሳስብ ወይም ምክንያት ሲሆን በሕጉ እንደተመለከተው ሰራተኛው የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን የጡረታ መብት ካለው ግን የስራ ውለ ቢቋረጥም፤ ገንዘብ ማግኘቱን ስለሚቀጥል (ስለቀጠለ) የስራ ስንብት ክፍያው አይከፈለውም።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ የስራ ውለን ያቋረጠው በፊብሪካው ውስጥ ከ20/ሃያ/ ዓመት በላይ ካገለገለ በኋላ ነው ቢባልም፤በጡረታ ሕጉ መሰረት የጡረታ እድሜ ላይ ስለመድረሱና የጡረታ አበል የሚያገኝ ለመሆኑ አመልካች አላስረዲም። ተጠሪ የስራ ውለን እንዲቋረጠ የጡረታ አበል ማግኘቱን ይቀጥላል የሚል ክርክርም ሆነ ማስረጃ ከላለ ደግሞ ለስራ ስንብት መከፈል መሰረት የሆነውን በሕጉ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት መሰረት በማድረግ የስራ ስንብቱን ክፍያ ማስከፈል የግድ ይሆናል። ሕጉ በዚህ መልክ ካልተተረጏመም ሰራተኛው ለድንገተኛ የገንዘብ ችግር ማጋለጥ ይሆናል። በመሆኑም ለወደፉት የጡረታ አበል ያገኛል በሚል መነሻነት አመልካች ያቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ከላይ እንዲመለከትነው የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ባለመቀበል የስራ ስንብት ክፍያው እንዱከፈል ወስኖአል። ይህ ውሳኔ በበኩላችንም የምንደግፈው ነው። ውሳኔውን የደገፍነው ሕጉ ከላይ በተገለጸም አይነት መተርጏም ያለበት መሆኑን ስለምናምን ነው። ስለዚህም የከፍተኛው ፍ/ቤት የሕጉን ትርጉም በሚፈለገው መጠን ባያስቀምጥም፣የደረሰበት መደምደሚያ ግን ትክክል ስለሆነ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልቻልንም።
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 06414 ሐምል 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቶአል።
ተጠሪ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት ክፍያው ይፈጸምለት ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
ት እ ዛ ዝ ጥቅምት 20 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው ይፃፍ።
No topics extracted.