No summary available.
ሐምል 16 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አፍሪካዊት የህንፃ ስራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር - አልቀረቡም ተጠሪ፡- እነ አቶ እንድሪስ ዓሉ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በአማራ ክልል የደቡብ ወል ዞን ኮንቦልቻ ወረዲ ፍርድ ቤት እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
ክርክሩ የስራና ሰራተኛ ግነኙነት የሚመለከት ነው። አመልካች የሚሰራው የኮንስትራክሽን ስራ በከፉል የተጠናቀቀ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪዎች ከስራ አሰናብቷል። ተጠሪዎች የስራ ውላችን አላግባብ ተቋርጧል በሚል ክስ አቅርበዋል። የኮንቦልቻ ወረዲ ፍርድ ቤት የተጠሪዎች ውል አላግባብ ተቋርጧል በማለት ተጠሪዎች የጠየቁትን የተለያዩ ክፍያዎች አመልካች እንዱከፍል ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በወረዲው ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የወረዲውን ፍርድ ቤት ውሣኔ አጽንቷል።
አመልካች ታህሣስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የኮንቦልቻ ወረዲና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ተጠሪዎች የተሰናበቱት የግንባታ ስራው እየቀነሰ በመሄደ ነው።
ተጠሪዎችን ከስራ ያሰናበትኳቸው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24 እና 30 መሰረት በመጨረሻ ጊዜ የሰሩበትን ደመወዝ የእረፍት ሰአት ክፍያና ያልተጠቀሙበት የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ በመለወጥ በመክፈል ነው።
ስለዚህ ከአዋጁ ድንጋጌ መንፈስና ዓላማውም በአንቀጽ 38 እና አንቀጽ 40 እና ላልች ድንጋጌዎች መሰረት ልዩ ልዩ ክፍያ እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። አመልካች የሰሩበትን ደመወዝ የትርፍ ሰአት ክፍያና የአመት እረፍት በገንዘብ በመለወጥ የከፈላቸው መሆኑን ማስረጃ አቅርበን እያለ እና ተጠሪዎችም ይህንን አምነው በክሳቸው ገለፀው እያለ ለእያንዲንዲቸው የአንድ ወር ደመወዝ እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካች ያሰናበተን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ነው። ስንሰራ የነበረበት ወር ሣይጠናቀቅ የሰራንባቸውን ቀኖች እና የአመት እረፍት ፈቃድ ክፍያ ከፍል አሰናብቶናል። ስራውን በተመለከተ በስምንት ብልክ ሶስቱ ተጠናቅቀው አምስቱ ገና ከግንባታ ላይ እንደሆኑ አስረድተናል ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም። የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ይደረግልን በማለት በጽሐፍ መልስ ሰጥተዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ያከናውን የነበረው የግንባታ ስራ መጠን እየቀነሰ እና እያለቀ መሄደን ተጠሪዎች አልካደም።
አመልካች በኮንቦልቻ ለሚገነባው ወል ዮኒቨርሲቲ ስምንት ብልክ መገንባት ጀምሮ ሶስቱ ብልክ ስራቸው ሙለ በሙለ የተጠናቀቀ መሆኑንና አምስቱ ብልኮች እየተሰሩ መሆኑን ተጠሪዎች ገልጸዋል። ይኸም አመልካች ተጠሪዎችን ሲቀጥር የነበረው ስራ የቀነሰ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
ተጠሪዎች ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩት በአናጢነት በድንጋይ ጠራቢነት እና በሰአት ተቆጣጣሪነት የነበረ መሆኑን አመልካችና ተጠሪዎች አልተካካደም። ስለዚህ ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረው ብልክ ስራ ሲጠናቀቅ አመልካች ተጠሪዎችን ማሰናበቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24 ንኡስ አንቀጽ 1 እና በአንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የተፈጸመ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የኮንስትራክሽን ስራ የሚሰራ ድርጅት በመሆኑ ማስጠንቀቂያ የመስጠትና ላልች የቅነሣ ስነ ሥርአቶችን ሣይገልጽ የስራው መጠን ሲቀንስ ወይም ስራው ሲያልቅ ሰራተኛችን ማሰናበት የሚትል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 30 የኮንስትራክሽን ዘርፍ የስራ ባህሪ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሕግአውጭው በልዩ ሁኔታ ደንግጓል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ ሣይሰጠን ነው ያስናበተን በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ተጠሪዎች ከስራ ሲሰናበቱ የሰሩበትን ደመወዝ እና የአመት እረፍት በገንዘብ ተሰልቶ የተከፈላቸው መሆኑን ለሰበር በሰጡት መልስ የገለፁ ሲሆን ቅሬታቸው በአግባቡ አልተሰላም የሚል ነው። መጠኑን በተመለከተ የተነሣው ክርክር የፍሬ ጉዲዩ ክርክር በመሆኑ በዚህ ችልት የሚስተናገድ አይለም። ተጠሪዎች ከስራ ሲሰናበቱ የሰሩባቸው ቀናቶች ደመወዝና የአመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ የተከፈላቸው መሆኑን አምነው በሚከራከሩበት ሁኔታ አመልካች ለተጠሪዎች የአንድ ወር ደመወዛቸውን እንዱከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ የወረዲውና የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24 ንኡስ አንቀጽ 1 እና በአንቀጽ 30 መሰረት ያከናወነውን የስራ ስንብት ህገ ወጥ የስራ ስንብት ነው በማለት ለተጠሪዎች ልዩ ልዩ ክፍያዎችን እንዱከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
በአማራ ክልል የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኮንቦልቻ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪዎችን ከስራ ያሰናበተው በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች ለተጠሪዎች ምንም አይነት ክፍያ የመፈጸም ግዳታ የለበትም ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.