No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮ-ጃፓን ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ - ጠበቃ ቴዎድሮስ ኃ/ስላሴ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ ትዔግስት ማሞ (81 ሰዎች) - ወኪል አበበ መገርሳ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የሥራ ውል መቋረጥን ተከትል የቀረበ የልዩ ልዩ ክፍያዎች ጥያቄ የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው የሥራ ውለ ሉቋረጥ የቻለው የጨርቃጨርቅ ፊብሪካው ከመንግሥት እጅ ወጥቶ ወደግል በመዛወሩ ነው። ተጠሪዎች ከሥራ የተሰናበቱት መንግስት ከ20 ዓመት በላይ ያገለገለና ዔድሜአቸው 45 ዓመት የሆኑ ሰራተኞች በጡረታ እንዱገለለ በመወሰኑ ነው። ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት የሥራ ውለ እንደሚቋረጥ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ስላልተሰጠን የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ይገባናል፤ ሰርተን ያልተከፈለን ደመወዝ ስላለና ይህም በጊዜው ስላልተከፈለን ከነመቀጫው ይከፈለን፣ ሰራተኛ በጡረታ ሲገለል የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ይሰጡን፣ ላልተጠቀምንበት የዓመት ፈቃድ እረፍት ጊዜ ገንዘብ ይከፈለን በማለት ነው።
አመልካች በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሾች በመንግስት በጡረታ እንዱገለለ እንደተወሰነ ሁለንም በአንድነት ሰብስበን ከማስታወቃችንም በላይ፤ እያንዲንደን ፍርም በማስሞላትም ከደጋፉ ሰነድ እና ፍቶግራፍ ጋር አያይዘን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ልከናል። የመጨረሻው ውሰኔ(ውጤት) እስኪደርሰን ድረስም ከሣሾች በሥራቸው ላይ እንዱቆዩ አድርገናል። በዚሁ መሰረት እየሰሩና እየተጠባበቁ ሳለ ከአንድ ዓመት በኋላ የመጨረሻው ውሳኔ ስለደረሰ ይህንኑ በፊብሪካው የማስታወቂያ ሰላዲ ላይ በመለጠፍ አሳውቀናል። የሰራተኛ ማህበሩም ይህንኑ አረጋግጦ ገልጾአል።
በመሆኑም አላሳወቃችሁም የምንባልበት ምክንያት የለም። ቀሪ ደመወዝ እና በሕጉ መሰረት ሉከፈለ የሚገባቸውን ክፍያዎች ፔይሮል አዘጋጅተን እንዱወስደ ብንጠይቅም ከሣሾች ለመቀበል ፈቃደኛ ስላልሆኑ ሳይከፈለ ቀርተዋል። ላልች ጥቅማጥቅሞች (በጡረታ በመገለል ምክንያት) ሉከፈለ የሚችለት በፊብሪካው የህብረት ስምምነት መሰረት ሰራተኛው 60 ዓመት ሞልቶት ጡረታ ሲወጣ ነው። ከሣሾች በጡረታ የተገለለት በመንግስት ውሳኔ በልዩ ሁኔታ በመሆኑና ይህም የህብረት ስምምነቱ ሥራ ላይ ሲውል አሰሪውና ሰራተኛው ያላዩት ያልተደራደሩበትና ያልተስማሙበት በመሆኑ ልንገደድበት አንችልም። በማለት ተከራክሮአል።
ክሱ የቀረበለት በምስራቅ ሸዋ ዞን የልሜ ወረዲ ፍ/ቤትም የግራቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ የተጠሪዎችን ጥያቄ በሙለ በመቀበል ወስኖአል። ከዚህ በመቀጠል አመልካች ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በወረዲው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሳኔ ላይ ተፈጽሞአል የሚለውን የሕግ ስህተት በመግለጽ እንዱታረምለት ጠይቆአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በአመልካች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር ተመልክተናል። ከዚህም እንደተገነዘብነው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የነበረው ውል የተቋረጠው ተጠሪዎች በመንግስት ውሳኔ መሰረት በልዩ ሁኔታ በጡረታ በመገለላቸው መሆኑን፣ ይህም ውሳኔ ከአንድ ዓመት በፉት ተጠሪዎች እንዱያውቁት ተደርጎ የጡረታ ፍርም ሞልተውና ፍቶግራፊቸውን ሰጥተው ውጤቱን ሲጠባበቁ የቆዩ መሆኑን በመጨረሻም ተጠናቆ በመድረሱ አመልካች ይህንኑ በማስታወቂያ ሰላዲ መለጠፈንና የሰራተኛ ማህበሩም ይህን ያረጋገጠ ስለመሆኑ አላከራከረም። ተጠሪዎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለመጠየቅ በዋቢነት የጠቀሱት የህብረት ስምምነት ድንጋጌም ጥቅማጥቅሞቹ ሉሰጡ የሚችለት ሰራተኛው 60(ስድሳ) ዓመት ሞልቶት ጡረታ ሲወጣ ነው በሚል የተደነገገ ስለመሆኑም አከራካሪ ሆኖ አልተገኘም። አከራካሪ ሆነው የተገኙት አልተከፈለም የተባለውን የስምንት ቀን ደመወዝ አከፊፈል፣ ስለማስጠንቀቂያ አሰጣጥ እና ጥቅማጥቅሞቹ የሚከፈለበትን አግባብ የሚመለከቱ ነጥቦች ናቸው።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው የሥራ ውለ ከመቃረቡ ከአንድ ዓመት በፉት ተጠሪዎች በጡረታ እንደሚገለለ (የስራ ውለ በዚህ ምክንያት እንደሚቋረጥ) አውቀው ፍጻሜውን ሲጠባበቁ ቆይተዋል። በሥር ፍ/ቤቶችም እንደተገለጸው ማስጠንቀቂያ አስፈላጊ የሚሆነው ሰራተኛው የሥራ ውለ እንደሚቋረጥ አውቆ በራሱ በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እንዱችል ነው። ከዚህ አንፃር የተጠሪዎችን ሁኔታ ሲታይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ከተቀመጠው ጊዜ በላይ አግኝተዋል። በአዋጁ አንቀጽ 35 እንደተመለከተው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ከሦስት ወር በላይ የሚረዝምበት ሁኔታ የለም። ማስጠንቀቂያው ለእያንዲንደ ሰራተኛ በእጁ ሉሰጠው ይገባ ነበር የሚለው የሥር ፍ/ቤቶች አካሄድም እንዱሁ በደፈናው ትክክል ነው የሚባል አይደለም። ዋናው መታየት ያለበት ሰራተኛው የሥራ ውለ እንደሚቋረጥበት በትክክል እንዱያውቅ መደረግ አለመደረጉን ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪዎች የሥራ ውላቸው እንደሚቋረጥ በሚገባ እንዱያውቁ ተደርጎአል ብቻ ሳይሆን ፍጻሜውንም ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ውጤቱ እንደመጣም ይኸው ተገልጾላቸው እንዱሰናበቱ ተደርጎአል። በመሆኑም የማስጠንቀቂያ ስርዓት አልተፈጸመም በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተደረሰው መደምደሚያ ሕጉን የተከተለ አይደለም።
ቀጥለን ያየነው አከራካሪ ነጥብ ከቀሪ ደመወዝ(የሳምንት ቀን) እና የተወሰኑ ሰራተኞች የዓመት እረፍት ፈቃድ ክፍያ አከፊፈል የሚመለከት ነው። ይህ ገንዘብ በእርግጥም ሉከፈል እንደሚገባ አመልካችም ያምናል። ክፍያዎቹን አዘጋጅቶ እንዱወስደ ጠይቆ እንደነበር፤ ነገር ግን ተጠሪዎች የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ላልች ጥቅሞች አብረው ካልተከፈለን ይህን ብቻ አንወስድም በማለታቸው ሳይከፈል መቅረቱን በመግለጽም ተከራክሯአል። በበኩላችንም ከአጠቃላይ የክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደቻልነው ገንዘቡ ሳይከፈል የቀረው ተጠሪዎች ለመውሰድ ባለመፈለጋቸው ነው።
የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ላልች ጥቅሞችም አብረው እንዱከፈለዋቸው ተጠሪዎች ፍላጎት ቢሆንም አመልካች እነዚህን ክፍያዎች የመክፈል ግዳታ የለብኝም የሚል ክርክር ስላነሳ ተጠሪዎች ስለፈለጉ ብቻ መክፈል ነበረበት ልባል አይችልም። የሥር ፍ/ቤቶች ግን የተጠሪዎችን ጥያቄ በመቀጠል በአዋጁ አንቀጽ 38 መሰረት ክፍያው ለዘገየበት በሚል ለእያንዲንደ ተጠሪ የ3(ሦስት) ወር ደመወዝ በተጨማሪ እንዱከፈል ወስነዋል። በእኛ እምነት ይህ አካሄድ የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ተጠሪዎች ላልቹን ክፍያዎችም የምናገኝበት የሕግ ምክንያት አለ ካለ አሁን እንደሚያደርጉት መከራከር ሲገባቸው ላላውን አንወስድም ማለታቸውም አግባብ ነው አንልም። በመሆኑም አመልካች ለገንዘቡ በጊዜው አለመከፈል ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት የለም።
በመጨረሻ የተመለከትነው በጡረታ ስለተገለልን በህብረት ስምምነቱ መሰረት የሚሰጡ ጥቅሞች እና ክፍያዎች ሉሰጡን ይገባል በማለት ተጠሪዎች ያነሱት ክርክር ነው። በዚህ ረገድ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠው ህብረት ስምምነቱ የሚናገረው 60(ስድሳ) ዓመት ሞልቶት በጡረታ ስለሚገለል ሰራተኛ እንደሆነ ነው። 60 ዓመት ከመሙላቱ በፉት በመንግስት ውሳኔ መሰረት (በልዩ ሁኔታ) በጡረታ ስለሚገለል ሰራተኛ በሚመለከት የሚለው ነገር የለም። ይሁንና የተጠሪዎች ክርክር በጡረታ ከመገለል ጋር ተያይዞ የተነሳ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ ብቻ በመመልከት የተጠሪዎችን ጥያቄ ተቀብለዋል። አመልካች ግን በዚህ አይስማሙም። ያነሳው ክርክርም ቀደም ሲል ተገልጾአል።
በመሆኑም እዚህ ላይ ሉመለስ የሚገባው ጥያቄ ተጠሪዎች ይጠቅመናል በማለት የጠቀሱት የህብረት ስምምነት ለተያዘው ክርክር አወሳሰን አግባብነት አለው ወይስ የለውም? የሚለው እንደሆነ እንገነዘባለን።
የህብረት ስምምነት በአሰሪና ሰራተኛ(ኞች) መካከል ድርድር ከተካሄደ በኋላ የተደረሰውን የሁለቱ ወገኖች ስምምነት የሚይዝ ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ የሁለቱም ስምምነት የያዘ እና ያፀደቁትም በመሆኑ የሚገዙበትና የሚተዲደሩበት ውላቸው ነው። በያዝነው ጉዲይ በአመልካች ክርክር እንደተመለከተው የህብረት ስምምነቱ ሰራተኛው 60 ዓመት ሳይሞላው በመንግስት ውሳኔ መሰረት (በልዩ ሁኔታ) በጡረታ ሲገለል የሚያገኘውን ጥቅም በሚመለከት ስምምነት የተደረገበት አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪዎች አመልካችን የሚያስገድደበት የህብረት ስምምነት ወይም ውል የለም ማለት ነው። በክርክሩ እንደተገለጸው በልዩ ሁኔታ (የ60 ዓመት መሙላት ሳይጠበቅ) በጡረታ የተገለለት ሰራተኞች ወደ 145 የሚጠጉ ናቸው። ይህ ሁኔታ በህብረት ስምምነቱ ያልታየ እና አመልካችም ሆነ ሰራተኞቹ ይሆናል ብለው ያልጠበቁት ነው። በአመልካች ላይ ሚያስከትለው ወጪም ከፍተኛ ነው። በህብረት ስምምነቱ አስቀድሞ ስምምነት ተደርጎበት ቢሆን ኖሮ አመልካችም ከዚህ አንጻር ተዘጋጅቶ ይጠብቅ ነበር። ይህ እንግዱህ በአፈጻጸም ረገድ የሚታይ ችግር ሲሆን ዋናው ግን ሁለቱን ወገኖች የሚገዛ በህብረት ስምምነቱ የተቀመጠ ድንጋጌ ስለላለ አመልካች የተጠየቀውን ክፍያ እና ጥቅማጥቅሞች እንዱሰጥ የሚገደድበት የሕግ ምክንያት የለም። ሲጠቃለል አመልካች ሉከፍል የሚገባው የሥራ ውለ ከመቋረጡ በፉት ለተሰራ ሥራ ያልተከፈለ ቀሪ ደመወዝ ካለ እና የዓመት ዔረፍት ፈቃድ ላላቸው ሰራተኞች (ተጠሪዎች) ሉከፈል የሚገባውን ክፍያ ብቻ ነው። ስለዚህም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን የልሜ ወረዲ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 11855 ግንቦት 15 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የምስራቅ ሸዋዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 16691 ታሕሣሥ 14 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
አመልካች የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ለዘገየበት ጊዜ እና በጡረታ መገለልን መሰረት በማድረግ የተጠያቂ ክፍያዎች እና ጥቅማጥቅም ሉከፍል አይገባም ብለናል።
ተጠሪዎች ሉከፈላቸው የሚገባው ውለ ከመቋረጡ በፉት ለሰሩት ሥራ ያልተከፈለ ቀሪ ደመወዝ እና ያልተጠቀሙበት የዓመት ዔረፍት ፈቃድ ክፍያ ብቻ ነው።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.