No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ነ/ፈጅ ወንድሙ መልኬ ተጠሪ፡- አቶ ይበልጣል አጥናፈ ቀረቡ
በስር ፍ/ቤት ተጠሪ ከሣሽ ነበሩ። በክሣቸውም አመልካች ያለአግባብ ያዛወሯቸው በመሆኑ ቀደም ብል ወደነበሩበት የስራ መደብ እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም ዝውውሩ ህጋዊ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብል ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የተደረገው ዝውውር ህገ ወጥ ነው በማለት ወደ ነበሩበት የስራ መደብና የስራ ቦታ እንዱመለሱ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
ችልቱም አመልካች ያደረገው ዝውውር ሕገ ወጥ ነው ተብል የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታውን ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጏ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አድምጧል። አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔም ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ተጠሪ በክሣቸው በመ/ቤቱ ውስጥ በደረሰብኝ ድብደባ እንድታረቅ ተጠይቄ ፈቃደኛ ባለመሆኔ ያለአግባብ ወደ ላላ ሥራ ተዛውሬአለሁ በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም ተጠሪን ማዛወሩን አልካደም አመልካች የተጠሪ አሰሪ ነው። አሰሪ ማለት አንድን ወይም ብዙ ሰዎችን ደመወዝ እየከፈለ በእርሱ መሪነት ስራውን እንዱሰሩለት ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2/1/ እና 4 ስር መመልከት ይቻላል። በመሆኑም አሰሪው ስራውን የሚመራ እንደመሆኑ መጠን አንድ ሰራተኛ የት ቦታ ተመድቦ ቢሰራ ለስራው ይጠቅማል የሚለውን የመወሰን አስተዲደራዊ መብት ሉኖረው ይገባል። የአሰሪው ስራውን ቅልጥፍና፣ ውጤታማነት፣የኢንደስትሪ ሰላም ወይም ላልች በተለያዩ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት አንድን ሰራተኛ ከአንድ የሰራ መደብ ወደ ላላ ወይም ከአንድ ቦታ ወደ ላላ የማዛወር መብቱ ስራ መሪነቱ ወይም አሰሪነቱ የሚመነጭ ነው። በእርግጥ አሰሪው ይህን የዝውውር እርምጃ ሲወስድ የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ሉጠብቅ ይገባል።
በተያዘው ጉዲይም ተጠሪ ወደ ላላ ቦታ የተዛወሩት ደመወዛቸውን ይዘው ለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል።
ተጠሪ በመ/ቤት ውስጥ በደረሰብኝ ድብደባ ለመታረቅ ባለመፍቀዳ ብቻ ልዛወር አይገባም በማለት ነው የሚከራከሩት ከላይ እንደተመለከተው ግን አሰሪው ለኢንደስትሪ ሰላም ሲል ወይም ለስራው ይጠቅማለ ብል በሚያምነው ቦታ ላይ የተጠሪን መብት ሣያጓድል ለማዘወር አስተዲደራዊ መብት አለው። ይህም በአዋጁ የተከለከለ ጉዲይ አይደለም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች የተጠሪ ዝውውር ሕገ-ወጥ ነው ሲለ የሰጡት ውሣኔ በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ውስጥ አሰሪው ሉኖረው የሚገባውን አስተዲደራዊ መብቶች ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
76626 በ20/06/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽረዋል።
ተጠሪ በአመልካች የተወሰደው ዝውውር ሕገ-ወጥ ነው በማለት እንዱነሣላቸው ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.