No summary available.
ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጉስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ናይኮን ኃ/የተ/የግ/ማ - ጠ/ማስተዋል ሐብታሙ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ተሰማ - ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ጉዲይ የጀመረው ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው።
በክሣቸውም ያለአግባብ ከስራ ስለተሰናበቱ ወደ ስራቸው እንዱመለሱ ካልሆነ ህጉ የሚፈቅደው ክፍያዎች እንዱከፈሎቸው ጠይቀዋል። አመልካችም ድርጅቱ ሣይሆን ከስራ ያሰናበታቸው በራሣቸው ፈቃድ ከሥራ በመቅረታቸው ነው ውለ የተቋረጠው በማለት የተከራከረ ሲሆን ፍ/ቤቱ ተጠሪ በራሳቸው ፍቃድ ነው ስራውን የለቀቁት በማለት ክሱን ሣይቀበለው ቀርቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት የ7 ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ሥራ እንዱመለሱ ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ችልቱም አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ተጠሪ በስር ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ የአመልካች ድርጅት ባለቤት ስልክ ደውለው ከስራ ያሰናበቷቸው መሆኑን ነው የገለፁት በመሆኑም በዚህ መልኩ የስራ ውላቸው መቋረጡን በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም ያለባቸው ተጠሪ ናቸው።
ይህንንም ለማስረዲት ተጠሪ ምስክሮች ቆጥረዋል። በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች ግን በተጠሪ የክስ አቀራረብ መሰረት እንዲላስረደ የሥር ፍ/ቤት አረጋግጧል። ስለዚህ ተጠሪ በስልክ የስራ ውላቸው መቋረጡን አላስረደም ማለት ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ቢሆን ስልክ ተደውል የተጠሪ የሥራ ውል መቋረጡን ተጠሪ አስረድተዋል አላለም። ይህም ተጠሪ ክስ የመሰረቱበትን ጉዲይ አለማስረዲታቸውን ያረጋግጣል። ይልቁንም ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው 3ኛ ምስክር የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ ስልክ ላይ ደውለው የስራ ቦታቸው በመቀየሩ ወደ ተቀየሩበት ቦታ እንዱሄደና ወደ ቀድሞ ስራ ቦታቸው እንዲይገቡ መከልከላቸውን ነው ያስረደት፤ ይህ ደግሞ የሚያስረዲው ለተጠሪ በስልክ የተነገራቸው የስራ ቦታቸው መቀየሩን እንጂ የሥራ ውላቸው መቋረጡን አይደለም። በልላ በኩል ተጠሪ በስልክ የተገለፀላቸው የሥራ ቦታ ሄደው እንዲይገቡ ወይም እንዲይሰሩ መከልከላቸውን ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም።
በአጠቃላይ ተጠሪ አመልካች ከሥራ ያሰናበታቸው መሆኑን ያለባቸውን የማስረዲት ሸክም ሣይወጡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተጠሪ የሥራ ስንብት ህገ-ወጥ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ታህሣስ 28/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የተጠሪ የሥራ ውላቸው በህገ-ወጥ መንገድ የተቋረጠ መሆኑን ገልፀው ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ መዝገቡ ተዘግቷል። ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.