No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሸን - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ ሣምሶን በለጥካቸው - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪ ታኀሣሥ 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት የክስ ማመልከቻ አመልካች ከሕግ ውጭ የሥራ ውለን በማቋረጥ ያሰናበታቸው መሆኑን ዘርዝረው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ሥራ እንዱመለሱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአመልካች ላይ በደብረብርሃን ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መከላከያ መልስ የተጠሪ ስንብት ሕጉን የተከተለ ስለመሆኑና ለዚህም ምክንያቱ ተጠሪ ለቢሮ እቃዎች ጥገና ወጪ የተደረገበት ሰነድ ቀደም ሲል የተፃፈው 2ዐ /ሃያ/ ብር ተደልዞ 1ዐዐ.00 /መቶ ብር/ እንዱሆን የተደረገና ተጠሪ የክፍያ ሰነደን ራሣቸው ያዘጋጁትና የደለዙት መሆናቸውን፣ ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪ ለሥራ አዱስ አበባ ሄጃለሁ በማለት አበል በወሰደባቸው ቀናት ደብረ ብርሃን ሥራ ላይ የነበሩ መሆኑ በአግባቡ በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡና እርምጃውም በሕጉ የተመለከተውን ቀነ ገደብ ውስጥ የተፈፀመ መሆኑን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲው ፍ/ቤትም አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተበት ምክንያት ተገቢ በሆነ የጊዜ ገደብ ባለመሆኑ ሕግን የተከተለ የሥራ ስንብት ልባል የሚችል አይደለም በማለት የተጠሪን ደመወዝ አመልካች መክፈል ካቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ለተጠሪ ከፍል ወደ ስራው እንዱመልስ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ይኸው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ አመልካች የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ያቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው ካለ በኋላ አመልካች ለተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 39 እና 4ዐ መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያና ካሣ ይከፈለው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ነሐሴ ዐ6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት 3 /ሦስት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ከሥራ የተሰናበተው በጥፊቱ ስለሆነ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ተብል ከተወሰነ በኋላ ካሣና የስንብት ክፍያ አመልካች ይክፈለው ተብል መወሰኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39 እና 4ዐ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ግንቦት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ 2 /ሁለት/ ገጽ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። በመልሣቸውም የተፈፀመ ጥፊት ሣይኖር በሕጉ አግባብ ያለበቂ ማስረጃ ከሥራ የተሰናበትኩ ሆኖ እያለ ካሣና የስንብት ክፍያ ሉከፈል አይገባውም ተብል የሰበር ቅሬታ መቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝበን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው ከተባለ የካሣና የስንብት ክፍያ እንዱከፈል መወሰን ሕጋዊነት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ውል ግንኙነት የነበረ መሆኑን፣ አመልካች የሥራ ውለን ማቋረጡንና ያቋረጠበት ምክንያትም ተጠሪ ሰነድ በመደለዝ በሰነደ ላይ ያለውን የገንዘብ መጠን አበላልጠው በመገኘታቸውና የውል አበል ያላግባብ ተጠቅመው መገኘታቸው በመረጋገጡ ስለመሆኑ ነው። ይኸው የተጠሪ አድራጎት በተገቢው ማስረጃ መረጋገጡንና የሥራ ውለ የተቋረጠበት መንገድም በሕጉ አግባብ ስለመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያረጋገጠው ጉዲይ ነው። ተጠሪ ስንብቱ ከመነሻው ያላግባብ ስለመሆኑ በመግለጽ ለዚህ ችልት መልስ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ክርክራቸው ሥርዓቱን ተከትል የቀረበ የሰበር አቤቱታ ወይም መስቀለኛ የሰበር መቃወሚያ ልባል የማይችል በመሆኑ ተቀባይነት ስለላለው በዚህ የክርክር ደረጃ ላታይ የሚገባው አይደለም በማለት አልፈነዋል።
በዚህ መዝገብ ወደተያዘው አቢይ ጭብጥ ስንመለስም የቅጥር ውል ሕጋዊ ወይም ሕጋዊ ባልሆኑ ምክንያቶች ሉቋረጥ እንደሚችል፣ ውጤቱም የተለያየ መሆኑን ሕጉ ያስገነዝባል።
የሥራ ውል በሕጋዊ መልኩ ተቋረጠ የሚባውም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 24፣ 25፣ 27፣ 28፣ 29፣ 31 እና 32 ድንጋጌዎች መሰረት የቅጥር ውለ ውጤት እንዲይኖረው ሲደረግ ነው። ከዚህ ውጪ የሚደረግ የሥራ ውል ማቋረጥ እርምጃ ከሕግ ውጪ ነው። በእያንዲንደ የሥራ ውል መቋረጥ ጊዜ አሰሪው በአዋጁ አንቀጽ 12/7/ ላይ በተደነገገው መሰረት የሥራ ልምደን የሚገልጽ ደብዲቤ የመስጠት ግዳታውን መወጣት ይኖርበታል። ከክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግን የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ አግባብ ሆኖ መገኘት አሰሪው ለሰራተኛው ለመክፈል እንደማይገደድ የአዋጁ አንቀጽ 39 እና 42 እንዱሁም ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ቅርጽና ይዘት ያስገነዝባል። የሥራ ስንብት ክፍያ አሰሪ ለሰራተኛ ለመክፈል የሚገደደው የሥራ ውለ ከሕግ ውጪ ሲያቋርጥ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 39/1/ለ/ ድንጋጌ በግልጽ ያሣያል። ላላው ሕጋዊ ያልሆነ የሥራ ውል ማቋረጥ ሉያስከትለው የሚችለው ውጤት ካሣ ሲሆን ይህም ሉፈፀም የሚችለው በአዋጁ አንቀጽ 42 ሥር የተመለከተው መመዘኛ ተሟልቶ የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕጉ አግባብ ውጪ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ ነው። የካሣ ክፍያ ዓላማም ሕገወጥ እርምጃን መከላከልና የሥራ ውለ ከሕግ ውጪ የተቋረጠበት ሰራተኛ በተቻለ መጠን ወደነበረበት ቦታ እንዱመለስ ማድረግ ነው። በመሆኑም ሕጋዊ የሆነ የሥራ ውለ የማቋረጥ እርምጃ ካሣን የማስከፈል ውጤት የለውም። ሲጠቃለልም የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው እየተባለ የሥራ ስንብትና የካሣ ክፍያ የሚከፈልበት ሕጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ የሰሜን ሸዋ አስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በደብረብርሃን ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ7ዐ34 ጥር 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በሰሜን ሸዋ መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 18364 ግንቦት 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተሻሻለው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
2/ የተጠሪ የሥራ ስንብት በሕጉ አግባብ የተደረገ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ የሥራ ስንብት እና የካሣ ክፍያ የሚከፈልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
3/ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.