No summary available.
ሰኔ 9 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አመልካች፡- የእንጨት መሰንጠቂያና መገጣጠሚያ ድርጅት - ከበደ መኯንን ቀረበ።
ተጠሪ፡- ረዱ እንዲለ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ያኔ ከሣሽ የነበረው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የስራ ውላን ከሕግ ውጪ ስላቋረጠብኝ ውዝፍ ደመወዜን በመክፈል ወደስራዬ እንዱመልሰኝ ይገደድልኝ፤ይህ ካልተቻለም የስራ ውል ከሕግ ውጪ በሚቋረጥበት ጊዜ ሉከፈለ የሚገባቸውን ክፍያዎች ከፍል ያሰናብተኝ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ውለ ሉቋረጥ የቻለው ከሣሽ ለስራ የተሰጠውን ገንዘብ አጉድል በመገኘቱ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪም የድርጅቱን ንብረት ያለአግባብ ወጪ እንዱሆን አድርጓል፤ በመሆኑም ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው በማለት ስለመከራከሩ መዝገቡ ያመለክታል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ከሣሽ የተከሣሽን ገንዘብ ስለማጉደለ በማስረጃ የተረጋገጠ እና በከሣሽም ያልተካደ ስለሆነ የስራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ መሰረት ነው በማለት ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደ ስራው ይመለስ በማለት ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ታሕሣሥ 1 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ ገንዘቡን ስለማጉደለ እና ለቤተሰቦቹ መንቀሳቀሻ እንደተጠቀመበት በችልት አምኖ እያለ የስራ ውለ ከሕግ ውጪ ነው የተቋረጠው በማለት ውሳኔ የመስጠቱን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ተጠሪ ለስራ ማስኬጃ እንዱውል ተብል ከተሰጠው የድርጅቱ ገንዘብ ውስጥ የተወሰነውን አጉድል ስለመገኘቱ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል። አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ይህን መሰረት በማድረግ እንደሆነም አላከራከረም። በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ተመስርቶ የነበረውን የስራ ውል ስለሚቋረጥባቸው ሕጋዊያን ምክንያቶች በሚመለከት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 በዝርዝር ተመልክቶአል። በዚህ መዝገብ ለተያዘው ክርክር አወሳሰን ተገቢነት የአዋጁ አንቀጽ 27 ሲሆን፣ይህም ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አስቀምጦአል። ተጠሪ በአሰሪው (በአመልካች) ገንዘብ ያለአግባብ ስለመጠቀሙ ተረጋግጦአል። ይህ ድርጊት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ከሚያቋርጡ ምክንያቶች አንደ እንደሆነ በተጠቀሰው አንቀጽ 27(1)(መ) ተመልክቶአል።
እንግዱህ ሕጉ ይህን ያሕል ግልጽ ከሆነ ከዚህ በተቃራኒ መወሰን የሚቻልበት ምክንያት አይኖርም። ሲጠቃለል የስራ ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተቃራኒው መወሰኑ ትክክል አይደለም። ውሳኔው በሕጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የስራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ብለናል። ስለዚህም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 25280 ሐምል 9 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቶአል።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.