No summary available.
ሐምል 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፊፈያ ድርጅት - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ታደሰ ዘነበ - ጠበቃ ደርበው ተመስገን መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ከመጋቢት 26 ቀን 1995 ዓ.ም. በተከሣሽ ድርጅት የሥራ መሪ በመሆን በመስራት ላይ እንዲለሁ የአሰሪና አመራር ድክመት አሳይተሀል በሚል ከነሐሴ 1997 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ የሶስት ዓመት እረፍት እንድወስድ የተደረገ ሲሆን ከጥር 22 ቀን 1998 ዓ.ም. ጀምሮ ከመምሪያ ሥራ አስኪያጅነትና ከማናጅመንት አባልነት ተከሣሽ እንድነሳ ካደረገ በኋላ ከመጋቢት 15 ቀን 1998 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ከሥራና ከደመወዝ ታግጃለሁ። በድርጅቱ የሥራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 35/2/ መሰረት ዔገዲ ከአንድ ወር ሉበልጥ እንደማይችል የተመለከተ ሲሆን ይህንን መመሪያ በመጣስ ተከሣሽን በዔግድ ያቆየው አላግባብ መሆኑ ተገልፆ ወደ ሥራ እንዱመለስና ውዝፍ ደመወዝም እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽም በሰጠው መልስ የከሣሽ የክፍያ ጥያቄ በ6 ወር ይርጋ ይታገዲል። ከሣሽ ከሥራ የተነሱት ከባድ የሥራ ጉድለት በመፈፀማቸው ሲሆን የሥራ መሪም ስለሆኑ ወደ ቀድሞ ሥራቸውም ሆነ ወደ ላላ ተመጣጣኝ ሥራ ለመመለስ ግዳታ የለብንም። ከሣሽ ላልሰሩበት ጊዜ ደመወዝና አበል እንዱከፈላቸው መጠየቅ አይችለም። ስለሆነም ክሱ ተሰርዞ ልንሰናበት ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ከሐምል 1997 ዓ.ም. በሥራ ላይ በዋለው የሥራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀፅ 35/2/ መሰረት በጥፊት ምክንያት አንድ የሥራ መሪ ከሥራ ሲታገድ ታግድ የሚቆየው ከአንድ ወር ለማይበልጥ ጊዜ እንደሆነ ተመልክቷል። ይህም ማለት በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለዔገዲው ምክንያት በሆነው ጉዲይ ላይ ተከሣሽ በዱስፒሉን ውሣኔ መስጠት አለበት ማለት ነው። ይህን ውሣኔ ካልሰጠ በከሣሽ ላይ የሰጠው ዔገዲ ተፈፃሚነት ሉኖረው አይችልም። ስለሆነም ተከሣሽ ከመጋቢት 15 ቀን 1998 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለውሣኔ አግዶቸው የሚገኙትን ተከሣሽን ወደ ሥራቸው ወይም ከቀድሞ ሥራቸው ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ሥራ ላይ የመመደብ ግዳታ አለበት። የደመወዝ ክፍያን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2541/1/ መሰረት ከሣሽ በሥራ ላይ ያልተገኙት ተከሣሽ ያለአግባብ እንዲይሰሩ ስለከለከላቸው በመሆኑ ክሱ ያቀረቡበትን የደመወዝ መጠን እና ተያይዞ የተደረገውን ጭማሪ እንደዚሁም ከሣሽ ሥራ ላይ በነበሩበት የ1997 ዓ.ም. የሥራ ዘመን የተከፈለውን ቦነስ ጨምሮ እንዱከፈላቸው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሽ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋደራል ከፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው ያቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪ አመልካችን ወደ ሥራ ሉመልሳቸው ይገባል ተብል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/2573 እና 2574 አኳያ አግባብነቱ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ፡ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመለሱ የተወሰነው በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም? በአግባቡ አይደለም ቢባል ካሣ ሉከፈላቸው ይገባል ወይስ አይገባም? ውዝፍ ደመወዝስ? የሚለት ናቸው።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተም የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ ወደ ሥራ ሉመለሱ ይገባል ያለው ከላይ እንደተመለከተው በሥራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 35/2/ ላይ እንደተመለከተው ዔገዲው የሚቆየው ለ1 ወር ጊዜ ብቻ ሆኖ ሳለ ከዚህ ጊዜ በላይ አግድ ማቆየት ዔገዲው ተፈፃሚ እንደማይሆን ያደርገዋል በሚል ነው። በተጠቀሰው የሥራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 35/2/ መሰረት አንድ የሥራ መሪ በዱስፒሉን ጉድለት ምክንያት ታግድ የሚቆየው ለአንድ ወር ጊዜ እንደሆነ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
ነገር ግን አንድ የሥራ መሪ በዱስኘሉን ጉድለት ምክንያት ከሥራ ታገድ እንዲለ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ካልተሰጠው ዔገዲው ተፈፃሚ የማይሆን ስለመሆኑ በደንቡ ላይ አልተመለከተም። የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤትም ዔገዲው ተፈፃሚ አይሆንም ወደሚል መደምደሚያ የደረሰው የደንቡን ድንጋጌ በመጥቀስ ሳይሆን የእራሱን ግንዛቤ በመውሰድ ነው።
ስለሆነም የሥራ መሪው ከሥራ ታግድ የሚቆይበት ጊዜ ከአንድ ወር ከበለጠ ዔገዲው ተፈፃሚ አይሆንም ማለት በደንቡ ባልተሸፈነበት ሁኔታ ነው።
ይልቁንም ይህንኑ በሚያጠናክር ሁኔታ ሥራ መሪው በዱስኘሉን ጉድለት ምክንያት ከሥራ ታግድ በሚቆይበት ጊዜ ጥፊቱ ተጣርቶ ውሣኔ እስከሚያገኝ ደመወዝ አይከፈለውም ተብል በዚሁ የሥራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀፅ 35/3/ ላይ መደንገጉ ሲታይ ዔገዲው ከዚህ ጊዜ ከረዘመ ለሥራ መሪው ደመወዝ ሉከፈለው እንደሚገባ ከድንጋጌው ተቃራኒ ንባብ /A contraire Reading/ መረዲት ስለሚቻል የዔገዲው ጊዜ መራዘም ዔገዲውን ሕገ ወጥ ሉያደርገው የሚችል አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2573 መሰረት አሰሪ የሥራ ውለን ቀሪ ለማድረግ በቂ ምክንያት ባይኖረውም እንኳን ለሰራተኛው ተገቢ የሆነ ካሣ ለመክፈል ከሚገደድ በሥተቀር ሰራተኛውን ወደ ሥራ ለመመለስ ግዳታ እንደላለበት መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በበቂ ምክንያት አይደለም ቢባል እንኳን ከፍ ብለው በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ/2573 መሰረት አመልካች ወደ ሥራ የመመለስ ግዳታ የላለበት ስለሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ወደ ሥራ ሉመለሱ ይገባል በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተም ተጠሪ ከሥራ የታገደት በፈፀሙት የዱስኘሉን ጉድለት ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ አመልካች አጥብቆ የተከራከረ ቢሆንም የተወሰደባቸው የዱስኘሉን ዔርምጃ ስለመኖሩ ወይንም ደግሞ ጥፊት የፈፀሙ ስለመሆናቸው አላስረዲም። ምንም እንኳን የተጠሪ ጥያቄ ወደ ሥራ የመመለስ ቢሆንም ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ከተባለ በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ/2573 ደንጋጌ መሰረት ካሣ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ ካሳ ሉከፈላቸው የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ሉከፈላቸው ይገባል ወይንስ አይገባም የሚለውን በተመለከተም ተጠሪ በክስ የጠየቁት ከመጋቢት ወር 1998 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 1999 ዓ.ም. ድረስ የተቋረጠ ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት ነው።
የፍደራል መ/ደ/ፍ/ቤትም ውዝፍ ደመወዝ ሉከፈላቸው ይገባል ያለው ከሣሽ በሥራ ላይ ያልተገኙት ተከሣሽ ያለአግባብ ሥራ እንዲይሰሩ ስለከለከላቸው በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2541/1/ መሰረት ለመክፈል ይገደዲል በማለት ነው።
ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ተጠሪን ከሥራ ካገደ በኋላ በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት ለዔገዲው ምክንያት በሆነው ጉዲይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ መስጠት ይጠበቅበት ነበር። በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ካልሰጠ ደመወዝ ለመክፈል እንደሚገደድ መተዲደሪያ ደንቡ አንቀጽ 35/3/ ድንጋጌ ተቃራኒ ንባብ መገንዘብ እንደሚችል ከላይ ተመልክተናል። እንደዚሁም አመልካች ይህንኑ የዔገዲ ጊዜ አራዝሞ መገኘቱ ሰራተኛው ለሥራ ዝግጁ ሆኖ ሳለ በዔገዲው ምክንያት ሥራ እንዲይሰራ ማድረጉን የሚያሳይ እንደመሆኑ መጠን በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ/2541/1/ መሰረት ዔገዲው ጸንቶ ከሚቆይበት ጊዜ በላይ ላለው ጊዜ አመልካች በተጠሪ ደመወዝ ለመክፈል ስለሚገደድ ይህም የደንቡን ድንጋጌ የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም አመልካች ዔገዲው ከሚያበቃበት ቀን ጀምሮ ውዝፍ ደመወዝና ከደመወዝ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ክፍያዎች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ተብል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
ለተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ ይከፈላቸው ተብል የተወሰነውን አጽንተናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.