No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ አመልካች፡- ሮፓክ ኢንተርናሽናል ኃላ.የተ.የግል ማህበር - ጠበቃ ያለለት ተሾመ ቀረበ ተጠሪ፡- ይደርሣል አእምሮ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ህዲር 08 ቀን 1999 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከሚያዝያ 15 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 1200.00 ደመወዝ እየተከፈላቸው በአመልካች መ/ቤት በዔቃ ግምጃ ቤትነት እስከ 03/13/98 ዓ.ም ድረስ መስራታቸውን ሆኖም ከዚሁ ከተቀጠሩበት የስራ መደብ አመልካች መ/ቤት አንስቷቸው በወር ብር 650.00 በሚከፈልበት የሰዓት ተቆጣጣሪነት የስራ መደብ አዛውሯቸው ቅሬታ ቢያሰሙም ተገቢው ምላሽ በወቅቱ አመልካች ሣይሰጣቸው መቅረቱንና ከስራ ያሰናበታቸው ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው የካሣ፣ የአምስት ዓመት አገልግልት፣ የዓመት ፈቃድ፣ የህዝብ በዓላት የ14 ቀናት ክፍያ፣ ለዘገየበት ክፍያ እንዱከፍልና የስራ ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። አመልካች በተከሣሽነቱ ቀርቦም ተጠሪ የተሰናበቱት ከ22/12/1998 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 04/13/1998 ዓ.ም ድረስ በስራ ቦታቸው ላይ ስላልተገኙ መሆኑን ገልፆ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ከተቀጠሩበት የስራ መደብ ወደ ላላ ተዛውረው ቅሬታ እያሰሙ ባለበት ሁኔታ በስራ ቦታቸው አልተገኙም ማለት ተገቢነት የላለው ነው የሚለውን ነጥብ በምክንያትነት ይዞ የአመልካችን እርምጃ ከህግ ውጪ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎች ለተጠሪ እንዱከፈለ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ግንቦት 29 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 2/ሁለት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ከስራ ገበታቸው ከ10 ቀናት በላይ ስለመቅረታቸው ተረጋግጦ እያለ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1/ለ) ስር ከተመለከተው ውጪ በተሣሣተ ትርጉም ተጠሪ ከስራ የቀሩት በበቂ ምክንያት ነው ማለታቸው ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው መልሣቸውን መስከረም 27 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ ወደተዛወሩበት የስራ መደብ ያልተገኙት የአመልካች ዘበኞች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ መሆኑንና የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔም የትርጉም ስህተት ያልተፈፀመበት መሆኑን ዘርዝረው ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ህዲር 04 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት የመልስ ማመልከቻ ተጠሪ ወደ አመልካች ግቢ ለመግባት በዘበኛ ተከልክያለሁ የሚለት ክርክር አዱስ መሆኑን ገልፀው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የፁሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ የተመደብኩበት የስራ መደብ ካለሙያ ነው በማለት ከስራ ገበታው ላይ ለ10 ተከታታይ ቀናት በላይ በመቅረቱ አመልካች ከስራ ሲያሰናብተው የስራ ውለ የተቋረጠው ያለበቂ ምክንያት ነው ተብል የአመልካች እርምጃ ህገ ወጥ ነው ሲባል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው ተጠሪ በተዛወሩበት የስራ መደብ ሣያገኙ ከ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ መቅረታቸውን መሰረት በማድረግ መሆኑንና ተጠሪ በበኩላቸው የሚከራከሩት በተዛወሩበት የስራ መደብ ያልተገኙት የአመልካች ዘበኞች ግቢ እንዲይገቡ ስለከለከሎቸው እና የስራ መደብ ዝውውሩን በመቃወም ቅሬታ አሰምተው ውጤቱን እየተጠባበቁ ስለነበር መሆኑን በመግለፅ ነው።
እንግዱህ አመልካች ተጠሪን ከተቀጠሩበት የስራ መደብ ወደ ላላ የስራ መደብ በማዛወር ተጠሪ ተገቢው ደብዲቤ ከተሰጣቸው በኋላ በተዛወሩበት የስራ መደብ ሣይገኙ ከ10/አስር/ ተከታታይ ቀናት በላይ የቀሩት በአመልካች ጥበቃ ክልከላ ስለመሆኑ በመጥቀስ ይኸው ተግባር በቂ ምክንያት ነው ሲለ ተጠሪ የሚከራከሩ ሲሆን የአመልካች ጠበቃ ይህንኑ የክርክር ነጥብ በስር ያልተነሣ ስለመሆኑ ጠቅሰው የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ይህ ችልትም የስር ፍ/ቤትን ዋና መዝገብ በማስቀረብ ጉዲዩን ሲያጣራው በስር ፍ/ቤት ክሱ በተሰማበት ወቅት ተጠሪ ይህንኑ የክርክር ነጥብ አንስተው ምስክሮቻቸውም የሚያስረደት ጭብጥ መሆኑን ገልፀው ምስክሮቻቸው መስማታቸውን አረጋግጧል። በመሆኑም የአመልካች ጠበቃ አዱስ ክርክር ነው በማለት ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
በልላ በኩል ተጠሪ ከላይ የተጠቀሰውን የክርክር ነጥብ በስር ፍ/ቤት ያነሡት ቢሆንም ጉዲዩን ለማስረዲት የተሰሙት ምስክሮች ግን የአመልካች ጠበቃ ተጠሪን ግቢ እንዲይገቡ የከለከሎቸው ስለመሆኑ የሰጡት የምስክርነት ቃል የለም። የስር ፍ/ቤትም ተጠሪ በስራ ቦታቸው ላይ ያልተገኙት በአመልካች ጥበቃ ክልከላ አለመሆኑን በመገንዘብ ተጠሪ በስራ መደቡ ለውጥ ምክንያት ቅሬታ እያሰሙ ባለበት ሁኔታ በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም ልባል አይገባም በማለት ነው። በመሆኑም ተጠሪ በተዛወሩበት የስራ መደብ ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ ያልተገኙት በአመልካች ጥበቃ ክልከላ ምክንያት አለመሆኑን ስለተገነዘብን በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ አድርገናል።
የስር ፍ/ቤት ተጠሪ በስራ ላይ ያልተገኙት ዝውውሩን ተቃውመው ቅሬታ ሲያሰሙ በነበረበት ወቅት መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪ ያለበቂ ምክንያት ከስራ ቀርተዋል ሉያስብላቸው አይችልም። ሲል የደረሰበትን ድምዲሜ ህጋዊነቱን ተመልክተናል።
በመሰረቱ በቂ ምክንያት ሣይኖረው በተከታታይ ለአምስት የስራ ቀናት በስራ ገበታው ያልተገኘ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሣያስፈልግ የስራ ውለን ለማቋረጥ ለአሰሪው ህጉ የሰጠው ስልጣን መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1/ለ) ድንጋጌ ያሣያል። ሰራተኛው የአሰሪውን እርምጃ ሉቃወመው የሚችለው በቂ ምክንያት ያለው ስለመሆኑ በማስረዲት ነው። በቂ ምክንያት የሚለው ሀረግ መመዘኛው ደግሞ ሰራተኛው ከስራ ቦታው ሉገኝ የማይችልበት ሁኔታ ስለመኖሩ ሉያመላክቱ የሚችለ ምክንያቶች ስለመሆኑ ከአዋጁ አጠቃላይ ዓላማና ከተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ለመገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በመሆኑም ከስራ የቀረ ሰራተኛ በቂ ምክንያት ኑሮት ከስራው ቀርቷል ለማለት የሚቀርበው ማስረጃ ሰራተኛው በስራ ቦታው ለመገኘት የሚያስችል መሰናክል የነበረ መሆኑን የሚያስረዲ ላሆን ይገባል። ይህም ሰራተኛው ባልተገባ ምክንያት ከስራው በመቅረት በምርትና ምርታማነት ላይ አለታዊ ተፅዔኖ እንዲያሳድር ሉያደርግ የሚችል ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ በስራ ገበታቸው ያልተገኙት ምክንያት የስራ መደብ ዝውውሩን በመቃወም ቅሬታ እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ገልጿል። ሆኖም የስራ መደብ ዝውውር መደረግና ሰራተኛው ቅሬታውን በማሰማት ላይ መሆኑ በስራ ቦታ ላለመገኘት እንደ በቂ ህጋዊነት ምክንያት የሚወሰድ አይደለም። የስራ መደብ ዝውውሩ ሰራተኛው በስራው ቦታ እንዲይገኝ መሰናክል የሚሆንበት ሁኔታ የለምና። ሰራተኛው በዝውውሩ ላይ ቅሬታ ካለውም ስራውን እየሰራ በህጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት መብቱን ማስጠበቅ አለበት እንጂ ከስራው ሉቀር አይገባም። ስለሆነም የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.