No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 39ዐ42 ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ዩቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማኀበር - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ጀማል መሐመድ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሣን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በአናጺነት በቀን ብር 32.00 እየተከፈለኝ እንድሰራ ተቀጥሬ ስሰራ ቆይቻለሁ። በኋላ ግን ሥራው እያለ ያለአንዲች ጥፊት ምንም ዓይነት የቃልም ሆነ የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ ከሥራ ተሰናብቻለሁ። ሥራውን በፈቃደ ለቆአል የሚለውን ደብዲቤ የተቀበልኩት ደብዲቤውን ካልተቀበልክ ደመወዝ አትወስድም ስለተባልኩ እንጂ ፈቅጄ አይደለም። ስለዚህ በሕጉ የተፈቀደትን ክፍያዎች በሙለ ተከፍልኝ እንድሰናበት ይወሰንልኝ በማለት ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሽን የቀጠርኩት በቋሚነት ወይም በጊዜአዊነት ሳይሆን፣ በቁርጥ ሥራ ነበር። ሥራውን የለቀቀው በራሱ ፈቃድ ነው። ሥራውን ሲለቅ ሉከፈለው የሚገባ ክፍያ ሁለ ወስድአል። የቀረበት ክፍያ የለም በማለት እንደተከራከረ ከስር ፍ/ቤት ውሣኔ ይዘት መገንዘብ ችለናል።
ክሱን የሰማው ፍ/ቤት ከሣሽ /የአሁን ተጠሪ/ የቁርጥ ሥራ ሰራተኛ ለመሆኑ ተከሣሽ አላስረዲም። ሥራው ከሣሹ በራሱ ፈቃድ ነው የለቀቀው በሚለው ነጥብ ላይም ከተከሳሽ ማስረጃ ይልቅ የከሣሽ ማስረጃ የሚያመዝን ሆኖ ተገኝቶአል። ከሣሽ ሥራውን ስለመልቀቁ የሚያሳይ ማስረጃም ተከሣሽ አላቀረበም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት የሥራ ሙለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በመቀጠልም አመልካች የስንብት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የአንድ ወር ደመወዝ የካሣ ክፍያ የ6 ወር ደመወዝ እና የዓመት ዔረፍት እንደ አገልግልቱ መጠን ታስቦ ለከሣሽ /ለተጠሪ/ ይክፈል በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም ብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
የሰበር ችልቱ አመልካች ሐምል 2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በሚል የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ነው።
ተጠሪ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፃፈው የክስ ማመልክቻ እንዲረጋገጠው የስንብት ደብዲቤ ተቀብል ሥራውን ከለቀቀ በኋላ ነው ወደ ክስ ያመራው። አመልካች በመከራከሪያነት ካነሳቸው ነጥቦች አንደም ይህኛው ነው።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ ሥራውን ስለመልቀቁ ማስረጃ አልቀረበም በማለት በውሣኔው ላይ ያሰፈረው ትችት ከዚህ አንፃር ሲታይ ስህተት ነው። በፍሬ ነገር በግልጽ የታመነን ሁኔታ እንደላለ አድርጎ ማለፍ አይቻልምና።
ላላው ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ይዘት የተመለከትነው ተጠሪ ይሰራበት የነበረው ሥራ የኮንስትራክሽን /ፕሮጀክት/ ሥራ ነው። የሥራ መደቡም አናጺነት ነው። በፕሮጀክት የተያዘ የኮንስትራክሽን ሥራ በተወሰነ ጊዜ የሚያልቅ በመሆኑ በዚህ ሥራ የተቀጠሩት ሰራተኞችም እንደቅደም ተከተለ የሚሰናበቱ ናቸው። የተጠሪን የሥራ መደብ ስንመለከት የአናጺነት ሥራ ስለሆነ ምናልባትም ከላልቹ ሥራዎች ቀድሞ የሚያልቅ ነው። ተጠሪ በክሱ እንዲረጋገጠው በአናጺነት ሥራ ልምድ ያለው /ያገኘ/ መሆኑ ተገልጾ ማስረጃ እንዱሰጠው ጠይቆ ከተሰጠው በኋላ የተሰናበተውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ግልጽ ነው። በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 3ዐ/1/ እንደተመለከተው የኮንስትራክሽን ሥራው እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት በሥራ ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ቅነሣ ላደረግ ይችላል። ቅነሳው ሲደረግም አሰሪው በአዋጁ የተመለከቱትን የሰራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይኖርበትም። በያዝነው ጉዲይ የሆነውም ይኸው ነው። የሥር ፍ/ቤቶች ግን ይህን ሁኔታ አገናዝበው ውሣኔ አልሰጡም። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.