No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 4 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የፍልውሃ አገልግልት ድርጅት ነ/ፈጅ ካሣሁን ወርቁ - ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ በረከት ተ/ማሪያም - ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪ የሥር ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ ነበሩ። ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ሰራተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው አመልካች የሥራ ውላን ያለአግባብ ስላቋረጠብኝ ወደ ሥራዬ ይመልሰኝ ካልሆነ በሕጉ የተቀመጡትን ክፍያዎች ይክፈለኝ ሲል ጠይቋል።
አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ሉሰናበቱ የቻለት አድራሻ የላለውና ለማስረጃነት ብቁ ያልሆነ የሥራ ልምድ ማቅረባቸው በመረጋገጡ ነው። ስለዚህ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ክስ ግራ ቀኙ ባቀረቡት ክርክር አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። በዚህም መሰረት አመልካች በ26/5/2000 በፃፈው ደብዲቤ ተጠሪ ያቀረቡትን የምስክር ወረቀትን አስመልክቶ ድርጅቱ ተጠይቆ የአይስክሬም ሽያጭ በድርጅቱ እንደማይካሄድ ቢገልፅም፤ አመልካች ተገቢውን አካል መጠየቁንና ሰርቷል የተባለበትን ጊዜ አይገልፅም፣ ማስረጃው ትክክል አልነበረም እንኳ ቢባል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሐ) መሰረት በሥራ ላይ ተፈፀመ የተባለው ማጭበርበር ድርጊት ልባል የሚችለው ከቅጥር በኋላ ሰራተኛው ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት የሚፈፅማቸውን የማጭበርበር ድርጊቶችን ነው። በመሆኑም የተፈፀመው ድርጊት በዚህ አንቀፅ ሥር የሚወድቅ ስላልሆነ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው። በአዋጅ አንቀፅ 43(2)(5) መሰረት የሁለት ወር ደሞዙ ተከፍልት ተጠሪ ወደ ሥራቸው ይመለሱ ሲል ወስኗል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት መዝገቡን ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። አመልካች ሐምል 22/2000 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት አቤቱታ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲል እንዱታረምለት ጠይቋል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክራቸውን ሰምቷል ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የተጠሪ ስንብት ሕገ ወጥ ነው የሁለት ወር ደሞዝ ተከፍልት ወደ ሥራ ይመለስ መባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህም መሰረት የግራ ቀኙ ካሰሙት ክርክር አቤቱታው የቀረበበትን ውሣኔ አግባብ ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የጉዲዩን አመጣጥ ባጭሩ ስናይ የአመልካች ድርጅት ተጠሪን ሲያሰናብት መሰረት ያደረገው በሀሰተኛና ብቃት በላለው ማስረጃ (የምስክር ወረቀት) በማቅረብ የተቀጠረ መሆኑን ባደረገው ማጣራት ደረስኩበት ሲል በማሰናበቱ ምክንያት የሥር ፍ/ቤቶችም ጉዲዩን በማከራከር ተጠሪ ፈፅመዋል የሚባል ድርጊት እንኳ ቢኖር በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 27(1/ሐ) ሥር ሉወድቅ አይችልም በሥራ ላይ እያለ የፈፀሙት ማጭበርበር አይደለም፣ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው፣ ተጠሪ የሁለት ወር ደሞዝና ወደ ሥራ ሉመለሱ ይገባል ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ጉዲይ የሥር ፍ/ቤቱ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ሲል መሰረት ያደረገው የአዋጁን አንቀፅ 27(1/ሐ) በመጥቀስ ትርጉም በመስጠት የተጠሪ ድርጊት በሥራ ላይ እያለ የተፈጠረ አይደለም ሲል ነው። የአዋጁ አንቀፅ 27(1/ሐ)”ን” ሙለቃል ስናነብ “የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለው ሰራተኛው በሥራው ላይ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር ሲፈፀም ነው” ይላል። በመሆኑም የዚህን አንቀፅ ትርጉምና ተጠሪ የፈፀሙትን ማጤኑ አስፈላጊ ነው። ከመጀመሪያው አመልካች የስንብቱን ምክንያት ሲገለፅ ተጠሪ ባቀረቡት የሐሰት ማስረጃ መቀጠራቸውን የተጠራጠረው ተጠሪ በተቀጠሩበት የአይስክሬም ስራ ብቃት ስላጡና ደንበኛም እየቀነሰ በመምጣቱ እና ባደረገው የማጣራት ሥራ ማስረጃው ለተጠሪ ሰጠ ያለውን ድርጅት በግንባር በመሄድ በድርጅቱ አይስክሬም እንደማይሰራ በማረጋገጥ ነው። ስለዚህ ከዚህ መረዲት የሚቻለው ተጠሪ ያቀረቡት ማስረጃ በጥርጣሬ ውስጥ የወደቀ መሆኑን ነው።
ባጠቃላይ ተጠሪ ከመጀመሪያውኑ ሲቀጠሩ በሐሰት ማስረጃ እስከሆነና በዚህም ማስረጃ ሥራቸውን መስራት ከጀመሩ በኋላ በመሀከለ የማጭበርበር ድርጊት መፈፀማቸው እስከተደረሰባቸው ድረስ ይህ ድርጊት ተጠሪ በሥራቸው ላይ (ስራቸውን በማከናወን) እያለ የፈፀሙት ነው ተብል ከመተርጏም ውጪ እንደ የሥር ፍ/ቤት አባባል በተቃራኒው ሉተረጏም የሚገባው አይደለም። በመጨረሻም ከግራ ቀኙ ክርክር ልንገነዘብ እንደቻልነው ማስረጃ ሰጠ የተባለው ድርጅት የአይስክሬም ሥራ (ሽያጭ) የማይከናወንበት መሆኑ ስለተረጋገጠ የተጠሪ ማስረጃ የተጭበረበረ ለመሆኑ በጥያቄ የሚገባ አይደለም።
ሰለዚህ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ሣያገናዝብ ለአንቀጽ 27(1/ሐ) አግባብ ያልሆነ ትርጉም በመስጠት ስንብቱ ህገወጥ ነው ሲል፤ የከፍተኛው ፍ/ቤትም ይግባኙን መዝጋቱ መሰረታዊ የህግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ቀን 4/10/2000 እና የከፍተኛው ፍ/ቤት በመ. በቀን 17/11/2000 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ስንብቱ ሕጋዊ ነው። ተጠሪ የሁለት ወር ደሞዝ መከፈለም ሆነ ወደ ሥራ ሉመለሱ አይገባም ብለናል።
የግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.