No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3965ዐ ግንቦት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ አመልካች፡- የየረር በር ምስራቅ ፀሐይ ቅደስ ዐራኤል ቤ/ክርስቲያን የደብሩ ዋና አስተዲደር - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- እነ ቄስ ሰፉነው ደሣለኝ - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪዎች በየግላቸው በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሣቸው ይዘትም በአመልካች ቤተክርስቲያን በጥበቃ ሥራ ተቀጥረው በማገልገል ላይ እያለ ጥፊት ሣይፈጽሙ ከሥራ መሰናበታቸውን ገልፀው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ሥራ መደባቸው እንዱመለሱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። አመልካችም በተከሣሽነቷ ቀርባ በሰጠችው መልስ ተጠሪዎች ከሥራ የተሰናበቱት የጥበቃ ተግባርና ኃላፉነት ባለማክበርና ባለመወጣት ብር 15,ዐዐዐ.00 /አሥራ አምስት ሺህ ብር/ የያዘ ሙዲየ ምጽዋት እንዱሰረቅ በማድረጋቸው በመሆኑ የሥራ ስንብቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ከአንቀጽ 13፣ 27/1/ሸ/ ድንጋጌዎች አኳያ ሕጋዊ ነው በማለት ተከራክራለች ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ምስክሮችን ከሰማ በኋላ አመልካች የተጠሪዎችን አላስረዲችም የሚልበትን ምክንያት በመዘርዘር የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደሚለው ድምዲሜ በመድረስ ተጠሪዎች የ6/ስድስት/ ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ምድብ ስራቸው አመልካች እንድትመልስ ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
337 መሰረት ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም በዚሁ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ወኪል ሐምል 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. 4/አራት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪዎች ኀዲር 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በጋራ በፃፈት የመልስ ማመልከቻ የአመልካችን የሰበር ቅሬታ ነጥቦች በመንቀፍ እና የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ተገቢነት በመዘርዘር ውሣኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው ዓቢይ ጭብጥ የተጠሪዎች የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ተብል ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ምድብ ሥራቸው እንዱመለሱ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪዎች በአመልካች ድርጅት ለጥበቃ ሥራ የተቀጠሩ፣ ይህንኑ ስራውን በዔለቱ ሲያከናውኑም ብር 15,ዐዐዐ.ዐዐ የያዘ ሙዲየ ምስዋት መጥፊቱ መረጋገጡን ነው። የሥር ፍ/ቤትም ይህንኑ ፍሬ ጉዲይ ያረጋገጠው ሲሆን የአመልካችን ክርክር ውደቅ ያደረገው ተጠሪዎች ለገንዘብ መጥፊት ቀጥተኛ ወይም በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ያደረጉት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም የሚል ምክንያት ይዞ ነው። ይሁን እንጂ ገንዘቡ ተጠሪዎች በጥበቃ ሥራቸው ላይ በነበሩበት ሰዓት አለመጥፊቱን የሚያረጋግጥ ክርክር አልቀረበም፤ የተጠሪዎች ሥራም የቤተክርስቲያኗን ንብረት መጠበቅ ነው። ገንዘቡ የጠፊው ገንዘቡ ተቀምጦበት የነበረው ሙዲየ ምስዋት ቁልፍ ሣይሰበር ስለመሆኑና ተመሣሣይ ቁልፍም በላልች ሰዎች እጅ እንደሚገኝም ተረጋግጧል። ነገር ግን የዚህ ፍሬ ነገር መረጋገጥ የተጠሪዎችን ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ አስተዋጽኦ ለገንዘቡ መጥፊት በምክንያት በመያዝ ኃላፉነት የለባቸውም ወደሚለው መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም። ዋናው ነጥብ ገንዘቡ የጠፊበት ሰዓት ተጠሪዎች በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙበት ከሆነ የስራቸው ኃላፉነት የለባቸውም ወደሚለው መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም። ዋናው ነጥብ ገንዘቡ በሚጠፊበት ሰዓት ተጠሪዎች በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙበት ከሆነ ከሥራቸው ኃላፉነት እና ተግባር ጋር ተያይዞ መታየቱ ላይ ነው።
እንግዱህ የአመልካች ገንዘብ የጠፊው ተጠሪዎች በጥበቃ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ከተረጋገጠ የአመልካች እርምጃ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13/3/ እና 27/1/ሸ/ አንፃር ላታይ የሚገባው ነው። ተጠሪዎች የሥራ ተግባራቸው ጥበቃ እስከሆነ ድረስ ስራው የሚጠይቀውን ጥንቃቄ እንዱያደርጉና እንዱወጡ የሥራ ደንቡ የግድ ይላል። ሥራው የሚጠይቀውን ጥንቃቄ ባለማድረግ ለሚደርሰው ጉዲት ደግሞ በሕጉ አግባብ ኃላፉነት ይከትላል።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎች በጥበቃ ላይ ባለበት ወቅት የአመልካች ንብረት መገኘቱ ስራው የሚጠይቀውን ጥንቃቄ አለማድረጋቸውን የሚያሣይ ነው።
በዚህ ተግባራቸው ደግሞ በአሰሪው ንብረት ላይ ጉዲት አድርሰዋል። ይህም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ/ መሰረት የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ነው። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በትዕዛዝ በማጽናት ተጠሪዎች ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎቸው ወደ ሥራ እንዱመለሱ ማድረጉ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር፣ የተጠሪዎች የሥራ ዓይነት የሚያስፈልገውን ጥንቃቄ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13/3/ እና 27/1/ሸ/ ድንጋጌዎች ጋር ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ተከታዩን ውሣኔ ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37446 የቀረቡት ጉዲዮች ተጣምረው ታይተው ሐምል ዐ2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተሰጠው ውሣኔ እና ይህንኑ ውሣኔ በመ/ቁ. 69644 ሐምል 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ያፀናው የፋ/ከ/ፍ/ቤት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
አመልካች የሥራ ውለን ያቋረጠው በሕጉ መሰረት ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.