No summary available.
ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ነ/ፈ ሰለሞን ተክላ ቀርቧል።
ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ተከሣሽ ተጠሪዎች የሥር ከሣሾች ነበሩ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ባመልካች ድርጅት በማቴሪያልስ ማኔጅመንት ዱቪዢን አጣዲፉ የአውሮፕላን መለዋወጫ ዔቃ አቅራቢነት የሥራ መደብ እና በኋላም የዔቃ ግዢ በመሆን ተመድበን እየሰራን ወደ አዱሱ የሥራ መደብ ስንዛወር ደሞዝና ጥቅም ተቀንሶብናል። ስለዚህ ቀደም ሲል የምናገኘው ደሞዝ ይከፈለን፣ ወደ ነበርንበት እንድንመለስ ከደሞዝ ጋር የሚከፈል ክፍያ እንዱመለስልን የነዲጅ አበል እና የበረራ የቅድሚያ ትኬት መብታችን እንዱጠበቅልን በማለት ጠይቋል።
አመልካች በበኩለ ባቀረበው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።
በዋናው ነገር ግን ተጠሪዎች ሲሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ ለተቀላጠፈ የሥራ ውጤት ሲባል እንደገና ሲዋቀር የተጠሪዎች አገልግልት አስፈላጊ በመሆኑ ከሥራ ከሚሰናበቱ በድርጅቱ የደመወዝ ፖሉሲ መሰረት በአዱሱ የሥራ መደብ ለመሥራት የሚስማሙ ከሆነ እንዱሰሩ ተጠይቀው በፍቃደኝነት በመቀበላቸው ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን ያየው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበውን ክርክር አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ ውሣኔ ሲሰጥ ተጠሪዎች ይዘውት የነበረው የሥራ መደብ በመዋቅር ለውጥ ምክንያት ተዘግቷል። በመሆኑም ተጠሪዎችን ከማሰናበት ይልቅ ደሞዛቸው ተቀንሶ ወደ አዱሱ የሥራ መደብ እንዱሰሩ ተጠይቀው የቀድሞ የሥራ መደባቸው /የማቴሪያልስ ማኔጅመንት ዱቪዥን አጣዲፉ የአውሮርላን መለዋወጫ ዔቃ አቅርቦት/ መሰረዙን ሳይክደ በአዱሱ የሥራ መደብ /የዔቃ ግዢ/ ቦታ ላይ ስምምነት ያደረግነው በማስፈራራትና ተገደን ነው የሚለው መከራከሪያ እና ከተደረገው ስምምነት መረዲት እንደተቻለው በፍቃደኝነት የተመደቡበት የሥራ መደብ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለዚህ ጥያቄው ውድቅ ነው በማለት ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ ስለተሰረዘ በፉት ይከፍለን የነበረው ደሞዝ እንዲይቀነስብን፣ የተቀነሰው ይመለስልን ጥቅማ ጥቅማችን ይጠበቅልን ሲለ ያቀረቡት ክርክር ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም ሲል ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚሁ ውሣኔ ባለመሥማማት ይግባኛቸውን ለከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል። ጉዲዩ የቀረበለትም የከፍተኛው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን በማከራከር ሲወስን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 28/1/መ በአሰራር ለውጥ የአንድ ሥራ መደብ ሲታጠፍ አሰሪው ሰራተኛውን ወደ ላላ የሥራ መደብ አዛውሮ ማሰራት ካልቻለ በማስጠንቀቂያ ሰራተኛውን ማሰናበት እንደሚችል ይደነግጋል።
የአዋጁ አንቀጽ 59/1/”ም” በሕግ /በሕ. ስምምነት/ በሥራ ደንብ በልላ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር አሰሪው የሰራተኛውን ደሞዝ መቀነስ እንደማይችል ተቀምጧል። በልላም በኩል ተጠሪዎች ይሰሩበት ከነበረው የሥራ መደብ አሁን ወደ ተመደቡበት መምጣታቸው ደሞዛቸው እንዱቀንስ መስማማታቸውን አይደለም። የቀረበውም ሰነድ እንዱህ አይልም። በተጨማሪም የአዋጁ አንቀጽ 25/1/ መሰረት ሰራተኛው መብቱን ለመተው የሚያደርገው ስምምነት ዋጋ የለውም። ስለዚህ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት የተጠሪዎችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ አግባብ አይደለም በማለት የሥር ውሣኔን በመሻር አመልካች ከተጠሪዎች የቆረጠውን ገንዘብ ተመላሽ ያድርግ ደሞዛቸውን ያስተካክል በማለት ሲወስን የጥቅማጥቅም ጥያቄን አስመልክቶ ግን ተጠሪዎች አሁን ለሚሰሩበት ቦታ የሚገባ መሆኑን አላስረደም ሲል ጥያቄያቸውን ሣይቀበል ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች ታህሣሥ 2/2ዐዐ1 ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረምልን ይገባል ሲል ጠይቋል።
እኛም በዚህ መሰረት ተጠሪዎችን በማስቀረብ ግራ ቀኙ የካሄደትን የቃል ክርክር ሰምተናቸዋል። ጉዲዩም ለሰበር ቀርቦ ላታይ ይገባል የተባለውም መልስ ሰጪዎች ከአመልካች ጋር ባደረጉት ስምምነት ወደ አዱሱ የሥራ መደብ ለሚያስገኘው የደሞዝ መጠን መመደባቸውን የሥር ፍ/ቤት የውሣኔ ግልባጭ ያስረዲል ይህ መሆኑ ከተረጋገጠ በዚሁ ፍሬ ነገር የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 25 እና 59 ላይ አስመልክቶ የሰጠውን ትርጓሜ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህም መሰረት አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ የግራ ቀኙ ካደረጉት ክርክር እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በመሆኑም የጉዲዩን አመጣጥ ባጭሩ ስናይ ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ክሳቸውን ሲመሰርቱ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በማቴሪያል ማኔጅመንት ድቪዢን አጣዲፉ የአውሮፕላን መለዋወጫ ዔቃ አቅራቢነት ሲሰሩ ቆይተው ወደ አዱሱ የሥራ መደብ “ዔቃ ግዢ” የሥራ መደብ ላይ በመመደባቸው ምክንያት በፉት ሲያገኙት የነበረው የደሞዝ መጠንና የሚያገኙት ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም እንደቀነሰባቸው በመግለጽ ወደነበሩበት ቦታ እንመለስ፣ ቀደም ሲል ሲከፈለን የነበረው ደሞዝ ይከፈለን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ይሰጠን በማለት በመጠየቃቸው አመልካችም ተጠሪዎች ሲሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ በመዋቅር መሻሻል /ለውጥ/ ምክንያት ስለተሰረዘ ተጠሪን ከማሰናበት ይልቅ በነሱ ፍቃድ ወደ አዱስ የስራ መደብ እንዱመደቡ የተደረገ ነው። ለአዱሱ ቦታ የተያዘውን ደሞዝ እየከፈልናቸው ነው፤ በተዘጋ የሥራ መደብ ክፍያ ልንጠየቅ አይገባም በማለቱ ጉዲዩ የቀረበለትም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ ተጠሪዎች የድሮው ቦታ /የነበሩበት የሥራ መደብ እንደተሰረዘ ሣይክደ በፍቃዲቸው በአዱሱ የሥራ መደብ ላይ ሆነው ወደ ነበርንበት እንመለስ የተቀነሰው ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ይከፈለን በማለት የጠየቁት ጥያቄን ውድቅ አድርጎታል። የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ በተቃራኒው የአዋጁን አንቀጽ 25/1/ በመጥቀስ የቀረበው ሰነድና ተጠሪዎች ከነበረው የሥራ መደብ አሁን ወደ ተመደቡበት መምጣታቸውን እንጂ ደሞዛቸውን እንዱቀነስ መስማማታቸውን አያሣይም። ስለዚህ የተቆረጠባቸው ደሞዝ ይከፈል በዚሁም ልክ ይስተካከል ሲል የስር ፍ/ቤት ውሣኔን ሽሮታል።
በመሰረቱ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሥር ውሣኔን ለመሻር ሲል የሰጠውን የሕግ ትንተና የአዋጁን አንቀጾች አተረጓጎም አንፃር ስናይ የሥር ውሣኔ የሚነቀፍ አልነበረም። የሰበር ችልቱም ቢሆን አጽኖት ሰጥቶ በጭብጥነት የያዛቸው ነጥብም ቢሆን ይህንኑ ለመመርመር ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ተጠሪዎችና አመልካች በሰበር ችልት ቀርበው ባደረጉት የቃል ክርክርና ከሥር መዝገብ ለመገንዘብ እንደተቻለው ተጠሪ የነበሩበት የሥራ መደብ የሥራ መሪ የሚያሰኛቸውና እነሱም /ተጠሪዎች/ ያልካደት ጉዲይ ነው። ታዱያ ይህ አዱሱ ቦታ /የሥራ መደብ/ በድርጅቱ የመዋቅር ለውጥ ምክንያት መዘጋቱን የተካካደበት በላለበት አመልካች ለማሰናበት ያለውን መብት በመተው ከተጠሪዎች አገልግልት አንፃር የእነርሱን ፍቃድ በመጠየቅ በጽሐፍ ተስማምተው ተጠሪዎችም ይህ አዱሱ የሥራ መደብ የደሞዝ መጠን ምን ያሕል እንደሆነ እያወቁ ሥራቸውን የጀመሩ መሆኑ በሰበር ችልት የግራ ቀኙ ስምምነት በግልጽ ተሰምቷል። ተገደን ነው የፈረምነው የሚለት ቢሆን በዚህ ደረጃ ላይ ሉታመን የሚችል አይደለም።
ይህ ሆኖ ሣለ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአዋጁን አንቀጽ 28/መ/”ን” በመጥቀስ የሥራ መደብ ሲታጠፍ አመልካች ወደ ላላ የሥራ መደብ አዛውሮ ማሰራት ካልቻለ ተጠሪን ሉያሰናብት ይችል ነበር በማለት ተችቷል።
በመሰረቱ የተጠሪ ጥያቄም ቢሆን ዝውውርን አይመለከትም። ላላው እንደ ከፍተኛው ፍ/ቤት አባባል /አተረጓጎም/ አመልካች የመጀመሪያው የስራ መደብ ሲሰረዝ /ሲዘጋ/ የተጠሪዎችን መሰናበት የሚያበረታታ ነው፤ ድርጅቱ ግን የተጠሪዎችን አገልግልት ከግምት በማስገባት ከማሰናበት ይልቅ በልላ የሥራ መደብ በፍቃዲቸው ላይ ተንተርሶ እያሰራቸው ነው። ይህ ድርጊት ፈጽሞ ሉነቀፍ የሚገባው አልነበረም።
ላላው የአዋጁን አንቀጽ 59/1/ አስመልክቶ በይግባኝ ሰሚው የተሰጠውን ትርጉም ስናይ ሰራተኛው በጽሐፍ ካልተስማማ አሰሪው የሰራተኛውን ደሞዝ ሉቀንስ አይችልም ነው የሚለው በያዝነው ጉዲይ ግን የአመልካች ድርጊት በዚህ መልኩ የሚተረጎም አይሆንም። ምክንያቱም አመልካች የተጠሪዎች የመጀመሪያው የሥራ መደብ በመሰረዙ ምክንያት አዱስ የሥራ መደብ ላይ በአዱስ መልኩ በመደራደር ወይም /በውል ሰነድ/ በመፈቃቀድ የፈፀሙት ስለሆነ የአንቀጹን መንፈስ የሳተ ትርጉም ነው። በመጨረሻም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአዋጁን አንቀጽ 25/1/ በመጥቀስ ሰራተኛው መብቱን ለመተው የሚያደርገው ስምምነት ዋጋ የለውም ሲል ነው የሥር ውሣኔን የተቸው። ይህም ነጥብ ቢሆን ተጠሪዎችም ቢሆኑ የመጀመሪያው የሥራ መደብ ከተሰረዘ በኋላ ነው በላለ መብት መብትን የሚጠይቁት። ይህም ማለት መብትን ፈጥሮ የነበረው የሥራ መደብ ራሱ የለምና ነው።
ስለዚህ የከፍተኛው ፍ/ቤት ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ከግምት ሣያስገባ በላለ የሥራ መደብ ልክ የተጠሪዎች ደሞዝ ይስተካከል ያልተከፈላቸው ተመላሽ ይሁን በማለት የሥር ውሣኔን መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ 1- የፋዳራል የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 65973 ነሐሴ 26/2ዐዐ1 የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
2- የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 349ዐ2 በ26/6/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
3- ተጠሪዎች አሁን በሚሰሩበት የሥራ መደብ በተያዘው የደሞዝ ልክ ሉከፈላቸው ይገባል ብለናል።
4- በመ/ቁ. 47676 ላይ ተሰጥቶ የነበረው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
5- የግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.