No summary available.
ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሐረር ቢራ አክሲዮን ማኀበር - ነ/ፈ ሬድዋን አህመድ ተጠሪ፡- አቶ አብደልቃድር አብደረዛቅ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ተወስኗል።
ጉዲዩ የተጀመረው በሐረሪ ሕ/ብ/ክ/መ/ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ተከሣሽ ተጠሪ የሥር ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በመልካች ድርጅት በሰራተኝነት ከ1974 ዓ.ም. ጀምሮ ስሰራ ቆይቼ በራሴ ፍቃድ ውላን አቋርጫለው በአዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 39/2/ሸ/ መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያ ሉከፍለኝ ሲገባ ቤት ከለቀቅክ በሚል ምክንያት ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፈለኝ በማለት ጠይቋል።
አመልካችም ለክሱ ባቀረበው መልስ ተጠሪ በአዋጅ ቁ 494/98 39/2/ሸ መሰረት የጠየቁት የስንብት ክፍያ የሕግ ድጋፍ የለውም ምክንያቱም ተጠሪ ኃላፉ ሆነው ሲሰሩ ስለነበረ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ሉፃፍ አይገባም በተጨማሪም ተጠሪ የጡረታ መብት ተጠቃሚ ስለሆኑ የስንብት ሉከፈላቸው አይገባም፣ የአመልካችን /የድርጅቱን/ ንብረት ሳያስረክቡ ክፍያ ሉጠይቁ አይችለም ሲል ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን በማከራከር ውሣኔ ሰጥቷል። በውሣኔውም አመልካች ላቀረቡት መቃወሚያ በመመርመር ውድቅ በማድረግ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ሲወስን ተጠሪ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ሉዲኙ እንደሚገባ በማመልከት በዚሁ አዋጅ መሰረት ተጠሪ በፈቃዲቸው ስራቸውን በመልቀቃቸው በሕጉ አግባብ ሉከፈላቸው የሚገባውን ክፍያ በጥያቄያቸው መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች ለተጠሪ እንድከፍል በመወሰን አመልካች በክስ መልሱ ላይ ንብረቴን ሳያስረክበኝ ክፍያ ሉጠይቅ አይገባውም ያለውን ነጥብ አልፍ ንብረቱን /ቤት/ አስመልክቶ አመልካች ቤቱ በራሱ ስም ተመዝግቦ መኖሩን አላረጋገጠም፤ የተከሣሽ ከሣሽነትን ማቅረብ ሲገባው ክርክር ማቅረቡ ሕጋዊ አይደለም ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
አመልካችም በዚህ ውሣኔ ባለመስማማት ለክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ቢያቀርብም ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የሥር ውሣኔ ጉድለት የለውም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት መዝገቡን ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረምለት ጠይቋል።
በዚህ መሰረት የሰበር ችልቱ ተጠሪ በአመልካች በኩል ላቀረበው አቤቱታ ቀርቦ መልሱን እንዱሰጥ መጥሪያ ብልክለትም ተጠሪ መጥሪያ ቢደርሰውም ክርክሩ ሉሰማ በተወሰነበት ቀን ላቀርብ ባለመቻለና አመልካችም ይህንኑ በማረጋገጡ ተጠሪ በላለበት ጉዲዩ እንዱታይ በማድረግ መዝገቡን መርምረናል መዝገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተባለውም በሥር ፍ/ቤት ለተጠሪ ሉከፈለው ይገባል ያለት የስንብት እና የቦነስ ክፍያን አግባብነት ለመመርመር ነው።
የሰበር ችልቱም አቤቱታ የቀረበለትን ውሣኔ የአመልካችን አቤቱታ፣ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን መርምረናል፡እኛም የጉዲዩን አመጣጥ ጠቅላል ባለ መልኩ ስናየው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በማገልገል ቆይተው በራሳቸው ፍቃድ የሥራ ውላቸውን በማቋረጣቸው አመልካች ቤት /ንብረት/ ካላስረከብከኝ በማለት በሕጉ የሚፈቀድልኝን ሉከፍለኝ ፈቃደኛ አልሆነም ብለው በመክሰሳቸው አመልካችም ተጠሪ በእጃቸው የሚገኘውን ንብረት ሣያስረክቡኝ ክፍያ ሉጠይቁኝ አይችልም በማለት በመከራከራቸው ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የተጠሪን የክፍያ ጥያቄ በመቀበል እንዱከፈለው በመወሰን ንብረትን አስመልክቶ በተከሣሽ ከሣሽነት ያልቀረበ ነው በማለት ውድቅ ሲያደርገው የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉድለት የለበትም ሲል የሥር ውሣኔን አጽድቆታል።
እንግዱህ ከቀረበው ውሣኔና የአመልካችን አቤቱታ እንደመረመርነው ምንም እንኳ ክፍያን አስመልክቶ ለማጣራት ጭብጥ ቢያዝም በተጓዲኝ አመልካች ተጠሪ ሉያስረክበኝ ይገባል የሚለውን ቤት በዋናነት ላታይ የሚገባው ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል። በመሰረቱ ተጠሪ በሥር ክሣቸው ተጠሪ ንብረቴን ካላስረከብከኝ በማለት ክፍያ ሉከፍለኝ ፍቃደኛ አልሆነም ሲለ ክስ መስክረዋል፤ ከዚህ በመነሣት ተጠሪ ከጠየቁት ክፍያ ውስጥ በአዋጁ አንቀጽ 36 መሰረት ሉከፈላቸው የሚገባውን ጠይቋል ይህ አንቀጽም አስፈላጊ ክፍያዎች አሰሪው በሰባት /7/ ቀን ውስጥ ለሰራተኛው ሉከፍል እንደሚገባ ይደነግጋል። ይህን ካልፈፀመ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 38 መሰረት አሰሪ በራሱ ጥፊት ካልከፈለ ለሰራተኛ ክፍያ የዘገየበትን እንዱከፍል ያዛል። ለእነዚህ አንቀጾች አግባብ ያለውን ትርጉም ለመስጠት /ክፍያ ዘገየ ወይም አልዘገየም/ ለማለት የንብረቱ ባለይዞታነትና ተጠሪ ሉያስረክብ ይገባል ወይ? ወይስ አይገባም? የሚለው ነጥብ ሉጣራ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። ምክንያቱም የተጠሪን የክፍያ ጥያቄ ምላሽ ለመሰጠት ስለሚረዲ ነው። በተጨማሪም አመልካች ተጠሪ ንብረቱን ሣያስረክበኝ ክፍያ ፈጽምልኝ ሉለኝ አይገባም የሚል ክርክር ስላለው ነው በመሰረቱ በአመልካች አቤቱታ ላይ ለመረዲት እንደቻልነው አመልካች የተባለውን ቤት ለሰራተኞቹ ማረፉያነት በማሰብ ከክልለ የኪራይ ቤቶች አስተዲደር በራሱ ስም እንደተረከባቸው እየገለፀ ነው ይህ ባለበት የሥር ፍ/ቤቶች ቤቱንም ቢሆን የማን ንብረት /በማን ስም/ እንዲለ በራሱ ጊዜ ሉያጣራውና ውሣኔ ሉያሳርፍበት ሲገባ የአመልካች ቤት መሆኑ አልተረጋገጠም የተከሣሽ ከሣሽነት ላቀርብበት ይገባል በማለት ጥያቄውን ማለፈ አግባብነት የለውም ምክንያቱም ተጠሪም ቢሆን የኔ ንብረት ነው ሲል ያቀረበው ማሳመኛ ነጥብ የለምና ነው። ባጠቃላይ የንብረት ጥያቄው ምላሽ ሣያገኝ የተጠየቀውን ክፍያ ነጥል ውሣኔ መስጠቱ የተጠየቀውን ዲኝነት በአግባቡ ምላሽ ተሰጥቶታል ለማለት አዲጋች ነው። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ተጣርቶ ሣይጠናቀቁ በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ እና በከፍተኛውም ፍ/ቤት ሣይታረም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የሐረሪ ሕዝብ ብ/ክ/መ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27167 ግንቦት 21/2ዐዐዐ እና የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የመ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ በያዙት ቤት ላይ በማከራከር ውሣኔ በሕጉ መሰረት ይስጥ ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።
ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.