No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሀይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- እነ ወ/ት ማሜ አሰፊ (36 ሰዎች) - ወኪል ትዔግስት ድንቁና ተሾመ ሃይላ ቀረቡ ተጠሪ፡- ብሕራዊ አስጎብኚ የጉዞ ወኪል (NTO) - ጠ/ብርሃኑ ከፍያለው
በዚህ መዝገብ የተያዘው የሰራተኞችን ቅነሣ የሚመለከት ጉዲይ ነው።
የአሁኑ አመልካች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ድርጅት ከስሯል በሚል አዱስ መዋቅር አስጠንቶ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 29(3) ሥር ከተመለከተው ውጪ ቅነሣ በማድረግ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ህጋዊ ባለመሆኑ ይታገድልን ብለዋል።
ተጠሪ ድርጅት ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 28(1) መሰረት ምርታማነትን ለማሣደግ እና የአሰራር ዘዳዎችን ለመለወጥ በተዘጋጀው መዋቅር መሰረት መመዘኛውን ባለሟሟላታቸው ቅነሣውን እንዲካሄደ ተከራክሯል።
ክሱ የቀረበለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ምርታማነትን ለማሣደግና የአሰራር ዘዳን ለመለወጥ አዱስ መዋቅር ማዘጋጀት መብት ያለው ቢሆንም ከጠቅላላ ሰራተኛ ውስጥ የሚቀነሰው ሰራተኛ 10% እና ከዚያ በላይ ሲሆን በአ/ቁ 377/96 አንቀፅ 29(2) የተከተለ ቅነሣ ማድረግ አለበት። ተጠሪ ግን ሥርዓቱን ያልተከተለ በመሆኑ በአንቀፅ 29(3) ከሀ-ረ ድረስ ባለው ቅደም ተከተል መሰረት ቅነሣውን አከናውኖ እስከሚያቀርብ ጊዜ ድረስ ለአመልካቾች የአንድ ወር ደመወዝ ይክፈል በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ቅነሣው በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 28(2)(ሐ) መሰረት በተጠናው አዱስ መዋቅር አንድ በአንቀፅ 28(3) ስር እንደተመለከተው የሥራ መደቡ በመሰረዙ አይደለም። በመሆኑም በአንቀጽ 29(3) ሥር የተመለከተውን መከተል አያስፈልግም በማለት የቦርደን ውሣኔ ሽሮታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በሚል ነው። ይህ ችልትም ቅነሣው በአንቀፅ 28(2)(ሐ) መሰረት ስለተደረገ በአዋጁ አንቀፅ 29(3) ሥር የተመለከተውን ቅደም ተከተል መከተል አያስፈልግም በማለት የተሰጠውን የህግ ትርጉም አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ቀርቦ ክርክሩን በቃል አሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው ነጥብ በአ/ቁ 377/96 አንቀፅ 28(2)(ሐ) መሰረት ቅነሣ ሲደረግ በአንቀፅ 29(3) ሥር የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተል መከተል ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚለው ነው።
በሥር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድም ሆነ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር አመልካች ቅነሣውን ያደረገው ምርታማነትን ለማሣደግና የአሰራር ዘዳን ለመለወጥ አዱስ መዋቅር በማዘጋጀቱ መሆኑ ተረጋግጧል።
በመሆኑም ቅነሣው በአዋጁ አንቀፅ 28(2)(ሐ) መሰረት መደረጉን ተገንዝበናል። ተጠሪም አጥብቆ የሚከራከረው አንቀፅ 29(3) ተፈፃሚ የሚሆነው በአንቀፅ 28(1) እና 28(3) መሰረት በሚደረግ ቅነሣ እንጂ በአንቀፅ 28(2)(ሐ) የሚመለከት አይደለም የሚል ነው። በመሆኑም አንቀጽ 29(3) ተፈፃሚነቱ ለማነው የሚለውን ነጥብ መመልከቱ ጠቃሚ ነው።
በአዋጁ አንቀፅ 29 ርዔስ እንደምንረዲው ድንጋጌው የሚመለከተው የሰራተኞችን ቅነሣ ጉዲይ ነው። የዚሁ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር አንድም የሰራተኞች ቅነሣ ምን ማለት እንደሆነ ትርጓሜውን አስቀምጧል። በዚህም መሰረት የሰራተኞች ቅነሣ ማለት በአንቀፅ 28(2) በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሰራተኞች ቢያንስ 10% የሚያህለውን ወይም የሰራተኞች ቁጥር ከ20 እስከ 50 በሆነው ድርጅት 5 ሰራተኞችን የሚመለከት ከ10 ተከታታይ ቀናት ያላነሰ ጊዜ የሚቆይ ቅነሣ ነው። በመሆኑም በአንቀፅ 28(2) ሥር በተመለከቱት ሰራተኞቹ የተሰማሩበት ስራ በከፉል ወይም በሙለ ለዘለቄታው በመዘጋቱ ወይም የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዝ ወይም ደግሞ ምርታማነትን ለማሣደግና አዱስ የአሰራር ለውጥ ለመጠቀም ሲባል በርካታ ሰራተኞች መቀነስ ሲኖርባቸው ቅነሣው በምን ዓይነት ሥርዓት ሉከናወን እንደሚገባ አንቀፅ 29(3) ያመለክታል። በእርግጥ የዚህ ድንጋጌ መግቢያ በአንቀፅ 28(1) መሰረት የሰራተኞች ቅነሣ ሲደረግ ቅነሣው ከሥር የተቀመጡትን ቅደም ተከተል መከተል አስፈላጊ መሆኑን ያመለክታል። ነገር ግን የድንጋጌው መግቢያ “አንቀፅ 28(1)” በማለት የተገለፀው በአፃፃፍ ግድፈት እንጂ ሉጠቀስ የሚገባው “አንቀፅ 28(2)” መሆኑን ችልቱ ያምናል። ለዚህም የሚከተለት ምክንያቶች ማስቀመጥ ይችላል። በአንቀፅ 29(3) ሥር የተመለከተው ስርዓት ተፈፃሚ የሚሆነው በአንቀፅ 28(1) በተመለከተው መሰረት ለሚሰናበት ሰራተኛ ነው ማለቱ ትርጉም አይሰጥም። ምክንያቱም በአንቀፅ 28(1) የሚናገረው አንድን ሰራተኛ በማስጠንቀቂያ ከስራ በማሰናበት ስለሚቻልበት ሁኔታ እንጂ ስለ በርካታ ሰራተኞች ቅነሣ አይደለም አንድ ሰራተኛ የተመደበበትን ሥራ ለመስራት ችልታው የላለው በሆነ ጊዜ ወይም በደረሰበት የጤና መታወክ ወይም የአካል ጉዲት ሥራውን ለመስራት ያልቻለ ከሆነ ወይም ድርጅቱ ወደላላ ቦታ ሲዛወር ሰራተኛው ተዛውሮ ለመስራት ፈቃደኛ ሣይሆን ሲቀር ወይም ሰራተኛው የያዘው የሥራ መደብ ሲሰረዝና ወደ ላላ ሥራ መደብ ማዛወር ሣይቻል ሲቀር ሰራተኛውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የስራ ውለን ማቋረጥ ይቻላል። እነዚህ በአንቀፅ 28(1) ሥር የተዘረዘሩትን ምክንያቶች የሚመለከቱት ችግር አለበት የተባለውን ሰራተኛ ብቻ እንጂ ላልችን ሰራተኞች ባለመሆኑ ሉሰናበት የሚችለውም ይኸው ሰራተኛ ብቻ ነው። በመሆኑም አንድን ሰራተኛ ለመሰናበት በአንቀጽ 29(3) ሥር የተመለከቱት በርካታ ሰራተኞች የሚቀነሱበትን ሥርዓት መከተል ተገቢ ነው ማለቱ ትርጉም የላለው ነው።
በመሆኑም በአንቀፅ 28(1) ሥር የተመለከቱት ምክንያቶች ሲያጋጥሙ ከስራ ለማሰናበት መከተል የሚያስፈልግ ስርዓት ሣይኖር ችግር አለበት የተባለውን አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰራተኞች በማስጠንቀቂያ ማሰናበት ይቻላል።
በልላ በኩል ግን አንቀፅ 28(2) ሥር የተመለከቱት የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያቶች ሰራተኞቹ የሚሰናበቱት የተመደቡበትን ስራ ለመስራት ችልታ ሣይኖራቸው ቀርቶ ወይም ሥራውን ለመስራት ፈቃደኝነት ጎድሎቸው ሣይሆን ድርጅቱ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ብዛት ያላቸውን ሰራተኞች መቀነስ በመገደደ ነው። ብዛት ያላቸው ሰራተኞች ከእነሱ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሥራ መሰናበት ካለባቸው ሥንብቱ እንዳት መከናወን አለበት የሚለው ቀጥል መፍትሄ ማግኘት የሚገባው ነጥብ ነው። ስለዚህም ህጉ መፍትሕ ማስቀመጥ አስፈልጎታል። ህጉ ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሣዩና ችልታ ያላቸው በሥራቸው ላይ እንዱቆዩ ቅድሚያ ሲሰጣቸው ተመሣሣይ የሥራ ችልታና ተመሣሣይ የምርት ውጤት የሚያሣዩ ሰራተኞች በሚመለከት ደግሞ በአንቀፅ 29/3/ (ሀ-ረ) በተዘረዘሩት መሰረት ቅነሣው እንዱካሄድ ያዛል። በመሆኑም በአንቀፅ 29(3) ሥር የተመለከተው የቅነሣ ስርዓት ተፈፃሚነት የሚኖረው በአንቀፅ 28(2) እና (3) ሥር በተመለከቱት ሁኔታዎች ላይ እንጂ በአንቀፅ 28(1) ሥር ለተመለከቱት ሁኔታዎች አይደለም።
በአጠቃላይ አንቀፅ 28 እና 29 በአንድነት ተገናዝበው ሲታዩ በአንቀፅ 29(3) ሥር የተቀመጠው የቅነሣ ሥርዓት ተፈፃሚ የሚሆነው በአንቀፅ 28(2) መሰረት ለሚደረግ ቅነሣ እንጂ በአንቀፅ 28(1) ሥር ለሚደረግ የሥራ ውል ማቋረጥ አይደለም።
በእርግጥ በአንቀፅ 28(2)(ሐ) ሥር የድርጅት ምርታማነት ለማሣደግ የአሰራር ዘዳዎችን ለመለወጥ ወይም በአዱስ ቴክኖልጂ ለመጠቀም የሰራተኛ ቅነሣ ማድረግ የሚቻለው በአንቀፅ 29(3) ሥር በተቀመጠው ቅደም ተከተል ቢሆንም ይህን ቅደም ተከተል መከተል ግድ የሚለው ግን የተቀነሱት ሰራተኞች ብዛት ቢያንስ 10% የሚያህለው ወይም የሰራተኞች ቁጥር ከ20-50 በሆነበት ድርጅት ቢያንስ 5 ሰራተኞች ሲቀነሱ ነው። በመሆኑም አሰሪው የቅነሣ ቅደም ተከተል አይገባም የሚል ከሆነ የሚቀነሱት ሰራተኞች ብዛት ከላይ ከተመለከተው ቁጥር በታች መሆኑን ማስረዲት መቻል ይኖርበታል።
ወደተያዘው ጉዲይም ስንመለስ ተጠሪ ሰራተኞቹን በአንቀፅ 28(2)(ሐ) መሰረት የቀነሣቸው ለመሆኑ በቦርድም ሆነ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረጉት ክርክሮች ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ ደግሞ ከፍ ሲል በተብራራው ምክንያት የቅነሣ ስርዓቱ ሉከናወን የሚገባው በአዋጁ አንቀፅ 29(3) መሰረት ነው። ተጠሪ ይህንን የቅነሣ ሥርዓት ልከተል አይገባም ማለት የሚችለው የተቀነሱት ሰራተኞች ቁጥር በአንቀፅ 29(1) ሥር ቅነሣ ነው ለማለት እንዱችል በመስፈርትነት ከተቀመጠው የሰራተኞች ቁጥር በታች ነው የሚለውን ፍሬ ነገር በማስረዲት ብቻ ነው። ተጠሪ ደግሞ ከሥር ጀምሮ የተሰናበቱት የሰራተኞች ቁጥር በህጉ ከተመለከተው በታች ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የለም። እንደውም አመልካቾች የተቀነሱት ሰራተኞች 30% የሚያህለ ናቸው በማለት በሰበር ችልት ባቀረቡት አቤቱታ የገለፁትን በማስተባበል መልስ አልሰጠም። ይህም በአመልካቾች የተነገረውን ፍሬ ነገር እንዲመነ የሚያስቆጥረው ነው።
በአጠቃላይ ተጠሪ የሰራተኞችን ቅነሣ ያደረገው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 28(2)(ሐ) በመሆኑ ቅነሣው ላደረግ የሚገባው በአንቀፅ 29(3) ሥር የተመለከተውን የቅነሣ ሥርዓት በመከተል በመሆኑ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ በህጉ የተመለከተውን የቅነሣ ቅደም ተከተል መከተል አይገባውም በማለት ለድንጋጌው የሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ታህሣስ 5/2001 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
2/ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ በመ/ቁ 350/ቀወ1/2000 22/12/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
3/ ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.