No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4337ዐ ግንቦት 12 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ግብርና ምርት ማሣደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት - ነ/ፈጅ ዲንኤል ያሬድ ተጠሪ፡- አቶ ጌታቸው ገድላ - ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ የቀረበው በሥራ ላይ ጉዲት ለደረሰበት ሰራተኛ የሚከፈልን የጉዲት ካሣ የሚመለከት ጉዲይ ነው።
ጉዲዩ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ በመሰረቱት ክስ በሥራ ላይ በደረሰባቸው አደጋ የጉዲት ካሣ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ደመወዛቸው ሣይቋረጥ አሣክሞ መዲናቸው ሲረጋገጥ ወደ ሥራ መልሷቸው እየሰሩ በመሆኑ በተጨማሪ ካሣ ሉከፈላቸው አይገባም በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ከጉዲቱ አገግሞ ሥራ መጀመሩ በራሱ የጉዲት ካሣን የሚያስከለክለው ባለመሆኑ አመልካች ለተጠሪ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ9/3/ መሰረት የጉዲት ካሣ እንዱከፈላቸው ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ መ/ሰጪን መጥራት ሣያስፈልገው ይግባኙን ሰርዞታል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታው ተጠሪ በደረሰባቸው አደጋ ታክመው ወደ ሥራቸው የተመለሱና የመስራት ችልታቸው የቀነሰ ወይም ችልታቸውን ያጡ ወይም ገቢያቸው ያልቀነሰ በመሆኑ፣ የተጠሪ ሁኔታ የተሻሻለ ወይም የተባባሰ ለመሆኑ በድጋሚ እንዱታከሙ ጠይቀን ዲግማዊ ምኒሉክ ሆስፒታል በድጋሚ ለማከም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፍ/ቤቱ የሕክምና ምርመራው እንዱካሄድ ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው ይህንን አለማድረጉ አመልካች የመንግሥት ልማት ድርጅት በመሆኑና ለደረሰው ጉዲት በገባው የመድን ሽፊን ባለመኖሩ ጉዲት ካሣው ሉከፈል የሚገባው በመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ መሰረት ሆኖ ሣለ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ9/3/ መሰረት እንዱከፈል መወሰኑ እንዱሁም ጉዲት ካሣው መጠን ሉሰላ የሚገባው ጉዲቱ በደረሰበት ጊዜ ተጠሪ በሚያገኙት ገንዘብ እንጂ ከረጅም ዓመት በኋላ በእድገት ባገኙት የደመወዝ መጠን በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉሻር ይገባል በማለት አመልክቷል።
ይህ ችልትም ተጠሪ ከደረሰባቸው ጉዲት ታክመው ተሽሎቸው ወደ ሥራ የተመለሱና የቀድሞ ስራቸውን እያከናወኑ በመሆኑ በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 1ዐ3/3/4/ መሰረት የተጠሪ ሁኔታ መሻሻለ ወይም መባባሱ በሕክምና ሣይረጋገጥ ጉዲት ካሣ አመልካች ሉከፍል አይገባም የሚለውንና የአመልካች ቅሬታና ላልች ነጥቦችን ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ለማድረግ ተጠሪም ቀርበው ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በቃል አሰምተዋል። ችልቱም የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች አኳያ እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው ተጠሪ በስራቸው ላይ እያለ ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ በግራ ቀኙ አልተካደም።
ተጠሪም ለዚህ አደጋ የጉዲት ካሣ ሉከፈለኝ ይገባል ሲለ አመልካች ሉከፈላቸው አይገባም ይከፈል ቢባል እንኳን ሉከፈላቸው የሚገባው በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 1ዐ9/3/ መሰረት ሣይሆን በመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ መሰረት ሲሆን መጠኑም ሉሰላ የሚገባው ጉዲቱ በደረሰ ጊዜ ያገኙ በነበረው ደመወዝ ነው በማለት ተከራክሯል።
ስለሆነም በዚህ ችልት መልስ ማግኘት የሚያስፈልጋቸው ጭብጦች
አመልካች ለተጠሪ የጉዲት ካሣ ሉከፍል ይገደዲል ወይ?
ይገደዲል የሚባል ከሆነ በየትኛው ሕግ መሰረት ነው ጉዲት ካሣው ሉከፈል የሚገባው?
መጠኑስ የሚሰላው እንዳት ነው? የሚለት ሆነው አግኝተነዋል።
1ኛውን ጭብጥ በተመለከተ በተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰ መሆኑ አመልካችም አልተከራከረም ከክርክሩ ሂደትም በተጠሪ ላይ የደረሰው የጉዲት መጠን 2ዐ% ቋሚ የአካል ጉዲት መሆኑ በሃኪሞች ቦርድ መረጋገጡን ተረድተናል በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 1ዐ7 መሰረት ማንኛውም በሥራ ላይ የሚመጣ ጉዲት የደረሰበት ሰራተኛ እንደ ጉዲቱ አይነትና መጠን ክፍያ እንደሚደረግለት ይደነግጋል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ለተጠሪ ካሣ ሉከፍል አይገባም በማለት የሚከራከረው የአካል ጉዲት ማለት የመስራት ችልታ መቀነስን ወይም ማጣትን የሚያስከትል ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 99/1/ ሥር የተመለከተ በመሆኑና ተጠሪ ግን አደጋ የደረሰባቸው ቢሆንም ታክመው ስለተሻላቸው የቀድሞ ስራቸውን ያለምንም ችግር እየሰሩ በመሆኑ የመስራት ችልታቸው ሣይቀንስ ወይም ችልታቸውን ሳያጡ ወይም ገቢያቸው ሣይቀነስ ካሣ ሉከፈላቸው አይገባም በማለት ነው። በእርግጥ በአዋጁ አንቀጽ 99/1/ ሥር “የአካል ጉዲት” ማለት የሰራተኛውን የመስራት ችልታ መቀነስ የሚያስከትል ወይም ጭራሹንም ችልታውን የሚያሣጣ ጉዲት ነው ተብል ተተርጉሟል።
እዚህ ላይም መነሣት ያለበት ጉዲይ “የመስራት ችልታ” በማለት በድንጋጌው የተመለከተው ሰራተኛው ጉዲት በደረሰበት ጊዜ ይሰራ የነበረውን ሥራ ለመሥራት የሚያስችለውን ችልታ ብቻ ነው ወይስ ሰራተኛው ከአደጋው በኋላም ቢሆን ሉሰራ የሚችለውን ማንኛውንም ሥራ የመስራት ችልታ ነው? የሚለው ነጥብ ነው። ይህን ነጥብ ግልጽ ለማድረግ የአዋጁ አንቀጽ 99/1/ የእንግሉዝኛውን ትርጉም ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል።
“Disablement” means any employment injury as a consequence of which there is a decrease or loss of capacity to work /ስርዝ የተጨመረ/ ከዚህ የእንግሉዝኛ ትርጉም በግልጽ መረዲት እንደሚቻለው የአካል ጉዲት ሰራተኛው ይሰራ የነበረውን ሥራ ለመሥራት የሚያስችለውን የተወሰነ ችልታውን ብቻ የሚመለከት ሣይሆን በአጠቃላይ ወደፉትም ሰራተኛው በላልች የሥራ መስኮች ተሰማርቶ ላልች ሥራዎችንም ለመስራት የሚያስችለውን ችልታ /capacity to work/ የሚመለከት ነው አንድ ሰራተኛ እስከመጨረሻው በመጀመሪያ የተቀጠረበትን ሥራ በመስራት ሣይገደብ ወደፉትም የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት የሚችል መሆኑ ይገመታል። ሕጉም የአካል ጉዲትን ለማያያዝ የፈለገው ሰራተኛው አደጋ በደረሰበት ጊዜ ይሰራ የነበረውን ሥራ ለመስራት የሚያስችለው ውሱን ችልታ ጋር ብቻ ሣይሆን ይልቁንም የሰራተኛው ወደፉት በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርቶ ለመስራት ከሚያስችለው አጠቃላይ የመስራት ችልት ጋር ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ በአደጋው ምክንያት 2ዐ% ቋሚ የአካል ጉዲት የደረሰባቸው ለመሆኑ በሀኪሞች ቦርድ ተረጋግጧል።
ይህንንም አመልካች አልካደም ይህ የደረሰባቸው ጉዲት ደግሞ ምንም እንኳን አሁን የሚሰሩትን ሥራ በአግባቡ መስራት ቢያስችላቸውም ጉዲቱ ወደፉት የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ከሚያስችላቸው ችልታ አኳያ ሉመዘን ይገባል።
በመሆኑም አመልካች ተጠሪው አደጋ በደረሰባቸው ጊዜ ሲሰሩ የነበረውን ሥራ ያለችግር በመስራታቸው ብቻ ችልታቸው አልቀነሰምና ካሣ ሉከፍል አይገባም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ላላው አመልካች የሚከራከርበት ነጥብ የሰራተኛው ሁኔታ የተባባሰ ወይም የተሻሻለ ወይም ትክክል ያልሆነ ምርመራ ተደርጎለት ከሆነ ሰራተኛው በድጋሚ እንዱመረመር ላደረግ ስለሚችል በዚሁ መሰረት በድጋሚ ተመርምረው ውጤቱ ሣይታወቅ ካሣ ልከፍል አይገባም የሚል ነው። በእርግጥ አመልካች እንዲለው የሰራተኛው ሁኔታ ተሻሽሎል ወይም ተባብሷል የሚባል ከሆነ በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ2/3/ መሰረት ሲጠየቅ ድጋሚ ሕክምና ላደረግ እንደሚችል አዋጁ ይፈቅዲል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የተጠሪ ሁኔታ ተሻሽሎል የሚል ከሆነ ይህንን የማስረዲት ሸክም አለበት። ይህንን የማስረዲት ሸክም ግን በቂ ማስረጃ በማቅረብ አልተወጣም። ድጋሚ ምርመራ እንዱደረግ የዲግማዊ ምኒሉክ ሆስፒታልን ጠይቆ ሆስፒታለ ፈቃደኛ አለመሆኑን ከመግለጽ በቀር ላላ ያቀረበው ማስረጃ የለም። ወይም ተጠሪን በድጋሚ እንዱመረመሩ ጠይቆ ተጠሪው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምርመራው ያልተደረገ መሆኑን አልገለፀም። በመሆኑም ቀደም ሲል ተጠሪ ተመርምረው 2ዐ% ቋሚ የአካል ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን በሐኪሞች ቦርድ የተረጋገጠው ሁኔታ ስለመሻሻለ ያቀረበው ማስረጃ ሣይኖር ተጠሪ የቀድሞ ሥራቸውን መስራት በመቀጠላቸው ብቻ የጉዲት ካሣ ልከፍል አይገባም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ስለላለው የሥር ፍ/ቤቶች የጉዲት ካሣ ሉከፍል ይገባል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም።
2ኛውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች የመንግሥት የልማት ድርጅት መሆኑ አከራካሪ አይደለም። በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ9/1/ ሥርም በሕ/ስምምነቱ በልላ አኳኋን ካልተመለከተ በቀር በአዋጁ ለሚሸፈኑ የመንግሥት ድርጅቶች ሰራተኞች የሚሰጠው የጉዲት ካሣ አሰሪው በገባበት የመድኀን ዋስትና ወይም በመንግሥት የጡረታ ሕግ መሰረት ካሣው እንደሚከፈል ያመለክታል። ድርጅቱ መድን ያልገባ ከሆነ በመንግሥት የጡረታ ሕግ ለሚሸፈኑ ሰራተኞች የመንግሥት የጡረታ ሕግ ተፈፃሚ እንደሚሆን ንዐስ ቁጥር 2 አስቀምጧል።
የመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 ጉዲት ለደረሰበት ሰራተኛ የሚከፈለው ካሣ መጠን የመንግሥት ሰራተኛው ጉዲት ከደረሰበት ወር በፉት ይከፈለው በነበረው መደበኛ የወር ደመወዙ 45% በአምስት ዓመት ተባዝቶ የሚኘው ሂሣብ በመንግሥት ሰራተኛው ላይ በደረሰው ጉዲት መቶኛ ተባዝቶ እንደሆነ አንቀጽ 33 ያመለክታል።
ተጠሪ አመልካች የደረሰውን የጉዲት ዓይነት አመልካች የመድን ዋስትና ገብተው በማለት ያቀረቡት ክርክር ስለላለ ጉዲቱ መድን ያልተገባለት መሆኑን አምነው እንደተቀበለት ያስቆጥራቸዋል። አመልካችም የመንግሥት የልማት ድርጅት በመሆኑና ለጉዲቱ መድን ሽፊን ያልገባ በመሆኑ ተፈፃሚነት የሚኖረው የመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ላይ የተመለከተው የካሣ መጠን ነው። ስለሆነም አመልካች በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ9/3/ መሰረት ካሣው እንዱከፈል የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጨረሻውን ጭብጥ በተመለከተ ከፍ ሲል በተገለፀው የመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ 33 የካሣው መጠን የሚሰላው ሰራተኛው ጉዲት ከደረሰበት ወር በፉት ይከፈለው በነበረው መደበኛ የወር ደሞዙ መሰረት ነው። በተያዘውም ጉዲይ ለተጠሪ የሚከፈለው የካሣ መጠን ሉሰላ የሚገባው በተጠሪ ላይ ጉዲቱ ከደረሰበት ከሰኔ 2ዐ/1999 ዓ.ም. በፉት በነበረው ወር ይከፈላቸው በነበረው መደበኛ የወር ደመወዝ መሰረት እንጂ ከጉዲቱ በኋላ በእድገት ባገኙት ደመወዝ መሰረት ላሆን አይገባም።
ው ሣ ኔ
75693 በ28/ዐ5/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽለዋል።
አመልካች ለተጠሪ የጉዲት ካሣ የመክፈል ግዳታ አለበት።
የጉዲት ካሣውም ሉሰላ የሚገባው በአ/ቁ. 345/95 አንቀጽ 33 መሰረት ተጠሪ ከሰኔ 2ዐ/1999 ዓ.ም. በፉት በነበረው ወር ይከፈላቸው በነበረው የወር ደመወዝ መሰረት ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.