No summary available.
ግንቦት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሙልሙል ዲቦ መጋገሪያ ድርጅት - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ በለጠ ተገኝ - ቀረቡ።
ለዚህ ጉዲይ መነሻ የሆነው ተጠሪ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪ በክሣቸው አመልካች ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ስላገዲቸው በመሆኑ ከታገደበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ሥራቸው እንዱመለሱ ይህ ካልሆነ ግን የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ጠይቀዋል።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ በተለያየ ጊዜ ሰራተኛ በመደብደብ እና ዛቻ በመፈፀማቸው ሁኔታውን ለማጣራት ከሥራ አገዲቸው እንጂ ከሥራ ስላላሰናበታቸው ከሣሽ የጠየቁት ዲኝነት አግባብ አለመሆኑን ተከራክሯል።
ጉዲዩን ያየው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሥራ ታገደ እንጂ ከሥራ ስላልተሰናበቱ ያለአግባብ ከሥራ የተሰናበተ ሰራተኛ የሚጠይቀውን የመብት ጥያቄ መጠየቃቸው አግባብ አይደለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል።
ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ግን አንድ ሰራተኛ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/4/ መሰረት የሚታገደው ለ3ዐ ቀናት ብቻ ስለሆነ ከዚያ በላይ ማገድ ከሥራ ማሰናበት ተደርጎ ይቆጠራል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አቤቱታው በአጭሩ ተጠሪ ያላግባብ ከሥራ ተሰናብቻለሁ የሚል ክስ አላቀረቡም የእገዲው ጊዜ በማብቃቱ ወደ ሥራ እንዱመለሱ የማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎ ስላልቀረቡ አመልካች ለክሱ መልስ ከሰጠ በኋላ ከሥራ አሰናብቷቸዋል። ከ3ዐ ቀናት በላይ ማገድ እንደ ስንብት ይቆጠራል የሚል ሕግ የለም የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ የቃል ክርክር አሰምተዋል። ፍ/ቤቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል። እንደመረመረውም ሉወሰኑ የሚገባቸው ጭብጦች፡-
ከ3ዐ ቀናት በላይ ማገድ ከሥራ እንደመሰናበት ይቆጠራል ወይ?
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ ከሥራ መሰናበታቸው በክርክሩ ሂደት ላይ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? የሚለት ናቸው።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪ በመጀመሪያ ክስ የመሰረቱት ያለአግባብ ከሥራ ታግጃለሁ በማለት ወደ ስራ ለመመለስ ወይም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው በመጠየቅ ነው። አመልካች ደግሞ ተጠሪን ከሥራ አገድኩ እንጂ ስላላሰናበትኩ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። በእርግጥ ተጠሪ ክስ ሲመሰርቱ ከሥራ ታግደው እንጂ ከሥራ ተሰናብተው አልነበረም። ነገር ግን በክርክር ላይ እያለ አመልካች ተጠሪን ከሥራ ማሰናበቱን ከመዝገቡ ሂደት የተረዲን ሲሆን አመልካችም ይህንን አልካደም።
ይህ አዱስ ክስተትም ክስ የቀረበበትን ከሥራ የመታገድ ጉዲይ የክስ ምክንያት የሚያሳጣውና የክርክሩን ጭብጥ እንዱለወጥ የሚያደርገው ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 251/1/ ሥር እንደተደነገገው ፍ/ቤቱ ነገሩን በፍርድ ከመወሰኑ በፉት በተከራካሪዎቹ ወገኖች የተያዘው ጭብጥ እንዱሻሻል ወይም ተጨማሪ ጭብጥ እንዱያዝ አስፈላጊና ተገቢ መሆኑን የገመተ እንደሆነና ይህን ማድረግ ለጉዲዩ መልካም አፈፃፀም ቀና መንገድ የሚያስገኝ መሆኑን ሲረዲው ፍ/ቤቱ ጭብጡ እንዱሻሻል ወይም ተጨማሪ ጭብጦች እንዱያዙ ለማድረግ ይችላል።
በተያዘውም ጉዲይ የተጠሪ ከሥራ መታገድ ጉዲይ በተጠሪ ከሥራ መሰናበት ምክንያት የክሱ ምክንያት ተቋርጧል። የክስ ምክንያት በላለው ጉዲይ ላይ ደግሞ ፍ/ቤቱ ላሰጥ የሚችለው ውሣኔ የለም። ይልቁንም ከክሱ በኋላ ተጠሪ ከሥራ በመሰናበታቸው ተጠሪ ክሣቸውን እንዱያሻሽለ በማድረግ ወይም ደግሞ ለጉዲዩ መልካም አፈፃፀም ቀና መንገድ ለማስገኘት ሲል ጭብጡን በመለወጥ የተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በአግባቡ መሆን አመሆኑን አከራክሮ ተገቢውን ውሣኔ ሲሰጥ ተጠሪ ያለአግባብ ተሰናብቻለሁ የሚለ ከሆነ በልላ ክስ ይጠይቁ በማለት መወሰኑ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙ ሲቀርብለት መጀመሪያ ክስ የቀረበበት ጉዲይ የክስ ምክንያቱ በተጠሪ ከሥራ መሰናበት የተቋረጠ በመሆኑ ጭብጡን አስተካክል መወሰን ሲገባው በአመልካች የተወሰደውን የሥራ ማገድ እርምጃ መሰረት አድርጎ ውሣኔ መስጠቱ የሥር ፍ/ቤት የፈጸመውን ስህተት መድገሙን ያሣያል።
በእርግጥ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ ያለአግባብ ከሥራ ተሰናብተዋል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል።
No topics extracted.
እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሰውም ተጠሪ ከ3ዐ ቀናት ከሥራ መታገዲቸው እንደስንብት ይቆጠራል በማለት ነው።
ነገር ግን አ/ቁ 377/96 አንቀጽ 27/4/ አንድ ሰራተኛ ሉታገድ የሚችልበትን ከፍተኛውን የጊዜ ገደብ ከማስቀመጥ በቀር ከ3ዐ ቀናት በላይ መታገድ ከሥራ እንደማሰናበት ይቆጠራል የሚል እንድምታ የለውም። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ተጠሪ ከ3ዐ ቀን በላይ ከሥራ ስለታገደ ከሥራ እንደተሰናበቱ ይቆጠራል በማለት ለድንጋጌው የሰጠው ትርጉም ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ከ3ዐ ቀን በላይ መታገዲቸው መሰናበታቸውን ያሣያል በማለት ያለአግባብ ከሥራ ለማሰናበት ሰራተኛ የሚገባውን ክፍያዎች እንዱያገኙ መወሰኑ ስህተት ነው። ይልቁኑ ተጠሪ በክርክሩ ሂደት ከሥራ መሰናበታቸው ስለታወቀ ይህ የሥራ ስንብት ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን ጭብጥ ይዞ ግራ ቀኙን በማከራከርና አስፈላጊም ከሆነ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ በማድረግ ተገቢውን ውሣኔ ላሰጥ ይገባው ነበር።
በልላ በኩል ግን ከክሱ በኋላ ተጠሪ ከሥራ መሰናበታቸውን አመልካችም ስላልካደ የክሱ ምክንያት የተቋረጠውን ከሥራ የመታገደ ጉዲይ የተወሰደው ይህ የሥራ ስንብት እርምጃ ሕጋዊ ነው አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ውሣኔ ላሰጥ ይገባ ነበር። በአጠቃላይ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ ክስ የመሰረቱበት ሥራ የመታገድ ጉዲይ ተጠሪ በመሰናበታቸው የክስ ምክንያቱ በመቋረጡ ክሱ እንዱሻሻል እና ጭብጡ እንዱስተካከል በማድረግ ውሣኔ ሉሰጡ ሲገባ የክስ ምክንያቱ በተቋረጠ ጉዲይ ላይ ውሣኔ መስጠታቸው ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ ውጪ ግን በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/4/ መሰረት አንድ ሰራተኛ ከሥራ ለማሰናበት የሚያበቃ ጥፊት ከፈፀመ ከሥራ ከማሰናበቱ በፉት አሰሪው ሰራተኛውን እስከ 3ዐ ቀናት ሉያግድ ይችላል። ከ3ዐ ቀናት በላይ የሚደረግ ከሥራ የማገድ እርምጃ አዋጁን የሚቃረንና ሕጋዊ ያልሆነ ተግባር በመሆኑ አመልካች ተጠሪን ከ3ዐ ቀናት በላይ አግድ ማቆየቱ ሕገወጥ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተጠሪ ከታገደበት ከ31ኛው ቀን ጀምሮ አመልካች ተጠሪን ከሥራ እስካሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ለተጠሪ ደመወዛቸውን ሉከፈላቸው የሚገባ ሆኖ አግኝተንዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37427 ግንቦት 25/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ እና በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 68297 በጥቅምት 12 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በአግባቡ ነው አይደለም? የሚለውን ጭብጥ የግራ ቀኙን ክርክርና ላላ የሚያቀረቡት ማስረጃም ካለ ማስጃቸውን ከመረመረ በኋላ ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ ይስጥ ብለናል።
አመልካች ተጠሪን ከ3ዐ ቀናት በላይ ከሥራ ማገደ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/4/ የተፈቀደ ባለመሆኑ ተጠሪን ከሥራ ካገደበት ከ31ኛው ቀን ጀምሮ ተጠሪን ከሥራ እስካሰናበተበት ያለውን ደመወዛቸውን ይክፈላቸው ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።