No summary available.
መጋቢት 8 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አበባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር - ነ/ፈጅ ቀርቧል ተጠሪ፡- አቶ ሣሙኤል ኪዲኔ - ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ተከሣሽ ተጠሪ የሥር ከሣሽ ነበሩ። ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት በመካኒክነት ተቀጥሬ እየሰራሁ ሳለ ሳላውቅ የዝውውር ኮሚቴ ሳይሰማ ጥገና ክፍል ለማጠናከር በሚል ሰበብ ወደ ልግያ ቅርንጫፍ አዛውሮኛል እንድታከም ጠይቄ ከሥራ አግድኛል እርምጃው ያለ አግባብ ስለሆነ ዝውውሩም እገዲውም አግባብ አይደለም ይባልልኝ ውዝፍ ደሞዝ ተከፍልኝ ወደሥራዬ እንዱመልሰኝ ሲል ጠይቋል።
አመልካችም መልስ እንዱሰጥ ታዞ ሲመልስ አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው የሕብረት ሥምምነቱ ከመውጣቱ በፉት ስለሆነ አዛውሮ ማሰራት ይችላል፣ በወቅቱም ዝውውሩን አልተቃወሙም፣ በሥራቸው ቦታ ላይም አልተገኙም በማለት ተከራክረዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበለትን ጉዲይ ከቀረቡት ማስረጃ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሮታል በውሣኔውም አመልካች ተጠሪን እንዲዛወረው የታመነ ሲሆን ሰራተኛውን የማዛወር ሥልጣን አለኝ ያዛወርኩት የሕብረት ስምምነቱ ከመውጣቱ በፉት ነው የሕብረት ሥምምነቱን መከተል አያስፈልገኝም ሲል ተከራክሯል አመልካች ሰራተኛን (ተጠሪን) የማዛወር መብቱ ከሕብረት ሥምምነት የመነጨ አለመሆኑ ግልፅ ነው በግራ ቀኙ ያለው የሥራ ውል የማዛወር ስልጣን የሰጠው መሆኑን አመልካች በማስረጃ አላስረዲም ተጠሪ ዝውውሩ ሲገለፅላቸው ጊዜ ይሰጠኝ አለ ማለት ዝውውሩን ሕጋዊ ያደርገዋል ማለት ባለመሆኑ ዝውውሩ ሕገወጥ ነው ዔግደም ያለአግባብ ስለሆነ የዝውውር ውሣኔው ተሰርዞ ተጠሪ በቀድሞ የሥራ ቦታቸው ይመለሱ ዔግደ የተላለፈበት ቀን አንስቶ ፍርድ እስከተሰጠበት ያለው ደሞዝ ተከፍልት ስራቸውን ያስቀጥል ሲል ወስኗል።
አመልካች ይህንኑ ውሣኔ ባለመስማማት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኙን ቢያቀርብም ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩን በማስቀረብ ከአከራከረ በኋላ ግድፈት የለውም ሲል የሥር ውሣኔን በፍ/ብ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች በ24/3/2001 ፅፈው ባቀረቡት ማመልከቻ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው ሲል አቤቱታውን አቅርቧል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ የማህበር አባል ስለሆነ ዝውውሩ ተገቢ አይደለም በማለት መወሰኑ ሰራተኛን አዛውሮ የማሰራት መብቴ ነው፣ ይህን ማድረግ ያልፈለገን ሰራተኛ ማሰናበት ሕግ ይፈቅዲል የሚለውን ቅሬታ ለመመርመር ነው።
በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ የግራ ቀኙ ወገኖች ባሰሙት ክርክር አቤቱታ ካቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
በእኛ በኩል ባጠቃላይ የጉዲዩን አመጣጥ ስናይ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በመካኒክነት ሙያ እያገለገለ ቆይተው የጥገና ክፍልን ለመጠናከር ሲባል ወደ ልጊያ ቅርንጫፍ እንዱዛወሩ ተደርገው በቦታው ባለመገኘታቸው ከሥራቸው በመታገዲቸው ምክንያት ዝውውሩ አግባብ አይደለም ደሞዝ ተከፍልኝ ወደ ሥራዬ ልመለስ ብለው ጠይቀዋል።
ከመዝገቡና ካቀረበው ክርክር መረዲት እንደተቻለው የሥር ፍ/ቤት አመልካች ሰራተኛውን (ተጠሪን) ለማዛወር ያበቃውን ምክንያት ከሕብረት ሥምምነት ወይም ከውል መሆኑን አላስረዲህም በማለትና የቀረቡትን የተጠሪን ማስረጃ ለማስተባበል አልቻልክም በማለት ዝውውሩና እግደ ሕገወጥ ነው ሰራተኛው ወደ ሥራው ይመለስ የተቋረጠበት ደሞዝ ይከፈለው ሲል ወስኗል።
ቀድሞውንም ቢሆን ተጠሪ ከሥራዬ ታግጃለሁ ወደ ሥራዬ ልመለስ ብል እስከጠየቀ ድረስ የሥር ፍ/ቤት ጭብጥ የዞ ሉያከራክር የሚገባው ስንብቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚል መሆን ነበረበት።
ይህ ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ ዝውውሩ ሕገወጥ ነው ሲል የሰጠውን ሐሳብ ስናይ አመልካች ተጠሪን የሕብረት ሥምምነት ወይም ከውል ባልመነጨ ምክንያት ስላዛወረው ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው ያለው አባባል አሣማኝ አይሆንም ምክንያቱም የአሰሪና የሰራተኛ ሕጉ በሁለቱም ወገን መብትና ግዳታን በማስቀመጥ የሚያገለግል ሕግ ነውና።
ባጠቃላይ ሲታይ የግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር እንዲስተዋልነው ተጠሪ ዝውውሩን በወቅቱ ሣይቃወሙ ከሥራቸው ቦታ ከ5 ቀናት በላይ እንዲልተገኙ በቃል ክርክር ጊዜ ፍ/ቤቱ ተረድቷል። ያለበቂ ምክንያት በተከታታይ ከሥራው ከ5 ቀናት በላይ የቀረ ሰራተኛ ደግሞ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 27(1)(ለ) መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለ ይቋረጣል። በዚህም ጉዲይ ተጠሪ በቃል ክርክሩ አልቀረሁም ሲል አልተከራከረም። በመሆኑም ዝውውሩን በወቅቱ ሣይቃወም ከሥራው ገበታ ላይ መቅረቱ ስለተረጋገጠ ተጠሪውን ወደ ሥራው የሚመለስበት ምንም ምክንያት ሣይኖር የሥር ፍ/ቤት የተጠሪ ዝውውር ሕገ ወጥ ነው የተቋረጠው ደሞዝ ይከፈለው በማለት የሰጡት ውሣኔ የፋ.ከ.ፍ/ቤትም ጉዲዩን አይቶ ማረም ሲገባው ማፅናቱ መሰታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ.የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀን 9/11/2000 እና የፋ.ከፍተኛ ፍ/ቤት በቀን 12- 3-2000 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች በሥራው ቦታ ላይ ከ5 ቀናት በላይ ስላልተገኘ መሰናበት አለበት ብለናል የሚከፈለውም የደሞዝ ክፍያ አይገባውም።
የግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.