No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ሰረቀብርሃን ተክላ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ከበደ አቡነቴ - ጠበቃ አበበ አሣመረ- ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ ያላግባብ ከስራ ስላገደኝ ያልተከፈለኝ ጠቅላላ ደመወዝ ብር 6569.96 ከፍልኝ ወደ ስራ እንድመልስ ይወሰንልኝ በማለት በደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መንግሥት በሀዲያ ዞን የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መከላከያ መልስም የተጠሪ የስራ ውል የተቋረጠው በኦዲት ምርመራ ጉድለት ተገኝቶባቸው መሆኑን፣የደመወዝ ይከፈለኝ ጥያቄም ላልተሰራ ስራ ላቀርብ የማይገባ መሆኑን ተጠሪ በተከሰተባቸው የገንዘብ ጉድለት በፍ/ቤት በፍትሐብሕር ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑንና በወንጀልም ምርመራው እየተካሄደ ስለመሆኑ ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ታግደው መቆየታቸው በግል እና በቤተሰባቸው ህይወት ጉዳት ማድረሱን እና የገንዘብ ጉድለት ቢኖር እንኳን በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ማስወሰን እንጂ ያለውሣኔ ማቆየት ያላግባብ መሆኑን በምክንያትነት በመያዝ የተጠሪን ክስ ተቀብል የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ ተጠሪ ያልተከፈላቸው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ካለ ተከፍሎቸው ወደ መደበኛ ስራ እንዲመለሱ ሲል ወስኗል። ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ታኀሣሥ 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፉት 3 /ሦስት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪ የመንግሥትን ገንዘብ ብር 182,845.43 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አምስት ብር ከአርባ ሦስት ሣንቲም/ ሆነ ብለው ለግል ጥቅማቸው ለማዋልና ለመበልፀግ ሲለ በስራ አጋጣሚ በእጃቸው ላይ የገባውን ገንዘብ ማጉደላቸው በድርጅቱ ኦዲተሮች ምርመራ ተረጋግጦ እያለ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደስራ እንዲመለሱ መወሰኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(/1/ሐ/መ/) ስር የተመለከተውን ያላገናዘበ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉታረም ይገባል በማለት ዳኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ይህንኑ ከሕጉ ጋር አገናዝበን በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም ተጠሪ ያልተከፈላቸው ደመወዝና ጥቅማጥቅም ተከፍሎቸው ወደ መደበኛ ስራ እንዲመለሱ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከስራ ታግደው የቆዩት በስራቸው አጋጣሚ ከእጃቸው ከገባው የአመልካች ድርጅት ገንዘብ ውስጥ ብር 182,845.43 ማጉደላቸው በአመልካች ድርጅት ኦዲተሮች የኦዲት ምርመራ ውጤት ከተረጋገጠ በኋላ የድርጅቱ የዲሲፕሉን ኮሚቴም ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ በማሣለፉ መሆኑን ነው። የስር ፍ/ቤትም የአመልካችን እርምጃ ሕገወጥ ነው ያለው ተጠሪን ከስራ ከአገደው በኋላ ለበርካታ ጊዜያት ውሣኔ ሣያስተላለፍ ቆይቷል፣ ጎደለ የተባለ ገንዘብ ካለም በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ማስወሰን አለበት በሚል ምክንያት ነው። ከዚህ የግራ ቀኙ ክርክር እና የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ማስተዋል የሚቻለው ተጠሪ የአመልካች ገንዘብ የጎደለባቸው መሆኑን ነው። ተጠሪ በስራቸው አጋጣሚ እጃቸው የገባው ገንዘብ ስለመጉደለ በአመልካች ኦዲተሮች መረጋገጡን ሣይክዱ ይኸው የምርመራ ውጤት የማስረጃነት ብቃት የለውም ተብል በፍትሐብሕር ክርክር ችልት መወሰኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ የፍትሐብሕር ክርክሩ የመጨረሻ ውሣኔ ያላገኘ በይግባኝ ደረጃ እየተከራከሩበት ያለ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ የአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚቀርቡ ክርክሮች ውጤታቸው ከፍትሐብሕር ክርክሮች የተለዩ በመሆናቸው የተጠሪ ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
የስር ፍ/ቤትም ተጠሪ ፈፀሙ የተባለት ጥፋት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/ መሰረት ከስራ እንዲሰናበቱ ሉያስወሰን የሚችል መሆን ያለመሆኑን መመርመር ሲገባው አመልካች ገንዘቡ ጎድሎል የሚል ቢሆን እንኳ በፍ/ቤት ክስ መሥርቶ ማስወሰን ይገባው ነበር ማለቱ የስር ክርክሮችና የፍትሐብሕር ክርክሮች ውጤታቸው የተለያየ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባቱን የሚያሣይ ነው በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ለፍርዱ መደምደሚያ የሰጠው ትንታኔ በበቂ የሕግ ምክንያት ያልተደገፈ ነው።
በእኛ በኩል ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱበትን ምክንያት ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/ አኳያ መርመረናል። ተጠሪ ብር 182,845.43 ማጉደላቸው በድርጅቱ ኦዲተሮች የሂሣብ ምርመራ ውጤት ተረጋግጧል።
ይህ የሂሣብ ምርመራ ውጤት ተቀባይነት የማያገኝበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም። ተጠሪ የአሰሪ ንብረት የሆነውን ብር 182,845.43 ማጉደላቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ከስራቸው ያለማስጠንቀቂያ ሉሰናበቱ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሣያል። በመሆኑም የአመልካች እርምጃ ሕጋዊ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት አልተገኘም።
በአጠቃለይ አመልካች በስር ፍ/ቤት ተጠሪ የተሰናበቱት የድርጅቱን ገንዘብ ስላጎደለና ይህም በድርጅቱ ኦዲተሮች ኦዲት ምርመራ ተረጋግጦና በዲሲፕሉን ኮሚቴ ተቀባይነት አግኝቶ ነው ሲል ያቀረበው ክርክር ታልፎ የገንዘብ ጉድለት ቢኖር እንኳን አመልካች በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ያስወስን እንጂ ማሰናበቱ በአግባቡ አይደለም በማለት ተጠሪን ወደመደበኛ ስራቸው ይመልስ፣ ያልተከፈላቸው ደመወዝና ጥቅማጥቅም ካለም ይከፈላቸው ሲል መወሰኑ በበቂ የሕግ ምክንያት ያልተገደፈና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/መ/ ስር የተመለከተውን ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በሆሣዕና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ2ዐ87 ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ በሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.ዐ4777 ታኀሣሥ 15 ቀን 2ዐዐ1 በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
2/ አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው በሕጉ አግባብ ነው ብለናል።
3/ ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.