No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ - ነ/ፈጅ ሰይፈ በቀለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኃይለ መንግስቱ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ህዲር 03 ቀን 2000 ዓ.ም የፃፈት ማመልከቻ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከጥቅምት 22 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ በቅጥር ላይ በተመሰረተ ግንኙነት በጥበቃ ኃላፉነት የስራ መደብ ተመድበው እየሰሩ ባለበት ሁኔታ ከህብረት ስምምነቱ ውጪ ከጥቅምት 22 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ድርጅት በፃፈው ደብዲቤ የስራ መደቡን ወደ ማይገለጽ በቅርብ ኃላፉ በሚሰጥ ትእዛዝ መሰረት ብቻ እንዱሰሩ ገልፆ ያዛወራቸው መሆኑን በመዘርዘር የስራ መደብ ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው ተብል ወደ ጥበቃ ኃላፉነት የስራ መደብ ተመልሰው እንዱሰሩ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአመልካች ድርጅት ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። አመልካች ድርጅትም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መከላከያ መልስ ተጠሪ የጥበቃ የኃላፉነት ስራ ባግባቡ ስላልተወጡና ጉዲዩ ተጣርቶ ለሕግ እስኪቀርብ ድረስ ከስራ ደረጃቸውና ከደመወዛቸው ሣይቀንስ ወደ አቻ ላላ የስራ ቦታ ማዛወሩ ህጋዊ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የተጠሪ የስራ መደብ ዝውውር ከህጉ አግባብ ውጪ ነው በማለት ተጠሪ በፉት ይሰሩበት የነበረውን የጥበቃ ኃላፉ ይዘው እንዱሰሩ ሲል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ተወካይ ጥቅምት 07 ቀን 2001 ዓ.ም ከፃፈት 3/ሦስት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። የግራ ቀኙ የቃል ክርክርም መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበትና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም አመልካች የተጠሪ የስራ ደረጃና ደመወዛቸውን ማይቀንስ የስራ መደቡን ዝውውር መፈፀሙ ሕገ ወጥ ነው ተብል ተጠሪ በቀድሞ የስራ መደብ ተመድበው እንዱሰሩ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የተጠሪ የስራ ደረጃና ደመወዛቸው ሣይቀንስ አመልካች ተጠሪን ከጥበቃ ኃላፉነት የስራ መደብ በማንሣት እያሰራ የሚገኝ መሆኑን ነው። ተጠሪ በጥበቃ ኃላፉነት ያገኙ የነበሩትን ደመወዝ አሁንም እያገኙ ያለ መሆኑን ሣይክደ አጥብቀው የሚከራከሩት የሚሰሩበት የስራ መደብ በመዋቅሩ የማይቃወቅ መሆኑን በመግለጽ ነው።
በመሰረቱ አሰሪ የሰራተኛውን ደረጃ ደመወዝና ላልች ጥቅማጥቅሞችን ሣይነካ ከአንደ የስራ መደብ ወደ ላላ ተመሳሳይ የስራ መደብ አዛውሮ ማሰራት ከተቋሙ አደረጃጀትና ከአሰሪነት መብቱ የሚመነጭ መብት ነው። የአሰሪ መዋቅርና አደረጃጀት እንዱሁም የሰራተኛን መብት በማይነካ ሁኔታ ሰራተኛን ከአንድ የስራ መደብ ወደ ላላ በተመሣሣይ የስራ መደብ አዛውሮ ማሰራት ህገ ወጥ የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም። የስራ መደብ ዝውውር ስራና ሰራተኛን ለማገናኘት ወይም ስራው እንዲይበደል ታስቦና ተረጋግጦ ከተፈጸመ ህገ ወጥ ልባል አይችልም። ይልቁንም የኢንደስትሪ ሰላምን ይፈጥራል፣ ለሐገር ሁለንተናዊ እድገትና ልማት አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል። የአሰሪን ድርጅት መዋቅርና አደረጃጀት እንዱሁም የሰራተኛውን ጥቅም የጠበቀ ትእዛዝ የመፈጸምና የማክበር ግዳታ ይኖረዋል። የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 13/2/ እና /7/ ድንጋጌዎች ይዘት የሚያስገነዝበውም ይህንኑ ነው። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች ተጠሪን ያዛወረው ከድርጅቱ መዋቅርና አደረጃጀት ውጪ እንዱሁም የተጠሪን ጥቅም ባልጠበቀ ሁኔታ ስለመሆኑ ሣይረጋገጥ አመልካች ተጠሪን በፉት ይሰሩበት በነበረው በደረጃ 10 የጥበቃ ኃላፉ የስራ መደብ ይመልሰው በማለት መወሰናቸውን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ሚያዝያ 29 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 67189 ሐምል 14 ቀን 2000 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የድርጅቱን መዋቅርና አደረጃጀት እንዱሁም የሰራተኛውን መብት በጠበቀ ሁኔታ አንድን ሰራተኛ ከአንድ የስራ መደብ ወደ ላላ ተመሣሣይ የስራ መደብ የማዛወር ሕጋዊ መብት ስላለው በተጠሪ ላይ የፈፀመው ተግባር ሕገ ወጥ አይደለም ብለናል።
ተጠሪን ወደ ደረጃ 10 የጥበቃ ኃላፉ የስራ መደብ አመልካች እንዱመልሰው የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.