No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሜድሮክ ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግል ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ሞገስ ሽፈራው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ መጋቢት 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ክስ በአመልካች ድርጅት በሹፋርነት ተቀጥረው እየሰሩ ባለበት ሁኔታ ያላግባብ ከስራ መሰናበታቸውን ገልፀው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ወይም የካሣ፣ የስራ ስንብት፣ የ65 ሣዓት ትርፍ ሣዓት፣ የ16 ቀን የእረፍት ቀን፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜና ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ ተከፍሎቸው ከስራ እንዱሰናበቱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ የድርጅቱን መኪና ባግባቡ የመጠበቅ ኃላፉነታቸውን ባለመጠበቅ ቁልፈን መኪና ላይ ትተው በመሄዲቸው ረዲታቸው መኪናውን አንቀሣቅሶ ግጭት በማድረስ ግምቱ ብር 5,867.24 /አምስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሣ ሰባት ብር ከሃያ አራት ሣንቲም/ የሆነ የንብረት ጉዲት ማስከተለንና ጥፊቱም ሁለተኛ በመሆኑ ስንብቱ በደንቡና በሕግ አግባብ መከናወኑን ዘርዝሮ የተጠሪ ወደ ስራ ልመለስና የክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የላለው መሆኑን እንዱሁም የትርፍ ሰዓት ክፍያ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የስራ ስንብቱ ሕገወጥ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ የ4 /አራት/ ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጥያቄ ደግሞ በማስረጃ አለመደገፈን ጠቅሶ ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ//ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥቅምት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የተጠሪ ድርጊት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ/ስር የሚሸፈን ሆኖ እያለ ከባድ ቸልተኝነት አይደለም ተብል ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው መባለ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ጠበቃቸው ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር የካቲት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብል አመልካች ለተጠሪ የአራት ወር ደመወዝ ከፍል ወደ ስራ ይመልሰው መባለ ባግባቡ መሆን አለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በሹፋርነት ተቀጥረው እየሰሩ ባለበት ወቅት በተረከቡት መኪና ላይ ቁልፍ ትተው በመውረዲቸው ረዲታቸው ቁልፈን በማንሣት መኪናውን ሲያንቀሣቅሱ ላላ መኪና በመግጨት በብር 5,867.24 (አምስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከሃያ አራት ሣንቲም)የተገመተ የንብረት ጉዲት መድረሱንና በልላ ወቅትም ተመሣሣይ ጥፊት ፈጽመው በድርጅቱ የዱሲþሉን ቅጣት ደንብ የአምስት ቀን ደመወዝ ተጠሪ የተቀጡ መሆኑን ነው። የስር ፍ/ቤትም ተጠሪ የመኪናውን ቁልፍ በመኪናው ላይ ትተው መውረዲቸውን አረጋግጦ ይህ ጥፊት ተጠሪን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት ከባድ ቸልተኝነት ነው ለማለት የማያስችል ነው በሚል ደምድሟል።
በመሆኑም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የተጠሪ አድራጎት በከባድ ቸልተኝነት ስር ሉወድቅ ይችላልን? የሚለው ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ ለስራው የተሰጡትን መሣሪያዎችና እቃዎች ሁለ በጥንቃቄ የመጠበቅ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 13/3/ ስር የተመለከተ ሲሆን በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረስ ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 27/1/ሸ/ ድንጋጌ ያሣያል። ሆኖም ከባድ ቸልተኝነት የሚለውን ቃል መለኪያ በተመለከተ ሕጉ በግልጽ አያሣይም። ይሁን እንጂ ቸልተኝነት የጥንቃቄ ጉድለት እንደመሆኑ መጠን የጥንቃቄ ዓይነትና ደረጃ እንደየ ድርጊቱና አድራጊው የስራ ድርሻ አኳያ በመመልከት ምላሽ ለማግኘት አያዲግትም። በመሆኑም የተጠሪ የጥፊት ደረጃ "ከባድ ቸልተኝነትን" ሉያቋቁም የሚችል መሆን አለመሆኑን ከስራቸው ባህርይ አንፃር መመልከቱ የግድ የሚል ነው። ተጠሪ ስራቸው ሹፋር ሲሆን ከስራቸው በተያያዘ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባቸው ነገሮች አንደ የመኪናውን ቁልፍ አያያዝ በተመለከተ ነው። የመኪናውን ቁልፍ በመኪናው ላይ በማናቸውም ጊዜና ቦታ ትተው ሉወርደ እንደማይገባ የስራቸው ድርሻ የግድ የሚለው ነው። ይሁን እንጂ በተያዘው ጉዲይ መኪናው ቁሞ የነበረበት ቦታ በአመልካች ድርጅት ግቢ ውስጥ ከመሆኑ እና ቁልፈን አንስተው መኪናውን በማንቀሣቀስ በልላ መኪና ላይ ጉዲት እንዱደርስ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያደገው የመኪናው ረዲት መሆኑ መረጋገጡ ከረዲቱ አስፈላጊነት አንፃር ሲታይ የተጠሪ የጥንቃቄ ጉድለት የከባድ ቸልተኝነት መለኪያ ሉያሟላ ይችላል ተብል የሚወሰድ አይደለም። ተጠሪ ቁልፈን በመኪናው ውስጥ ረዲቱ ባለበት ሁኔታ ትቶ መውረደ ትክክለኛ አእምሮ ባለው ሰውና በተጠሪ የግል ሁኔታ መመዘኛ መሰረት ከባድ ቸልተኝነትን ሉያሣይ የሚችል አይደለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የተጠሪ ጥፊት ከባድ ቸልተኝነት አይደለም ማለቱ ስህተት ሁኖ አልተገኘም። የተጠሪ ጥፊት ሁለተኛ ጊዜ ነው ቢባልም ጥፊቱ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውለን ለማቋረጥ የሚያስችል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ተ/ መሰረት የተደረገ ስምምነት ስለመኖሩ አመልካች አላስረዲም፤ ስለሆነም የስራ ውለ የተቋረጠበትን መንገድ የስር ፍ/ቤት ከሕግ ውጪ ነው ማለቱ የሚነቀፍ ሆኖ ስላልተገኘ በዚህ ረገድ የቀረበውን የሰበር አቤቱታ የምንቀበልበትን ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ይሁንና የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ከተባለ ውጤቱን በተመለከተ በአዋጁ ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመመልከት ምላሽ መስጠቱ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ የግድ የሚለው ነው። የአዋጁ አንቀፅ 43/2/ ድንጋጌ ሲታይም በዚህ ቁጥር በንዐስ ቁጥር አንድ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጅ ቁጥር 24፣25፣27፣28 እና 29 ከተደነገገው ውጪ የቅጥር ውለ የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደስራው እንዱመለስ ወይም ካሣ ተከፍልት የስራ ክርክር ሰሚ አካል ሉወስን እንደሚችል አስቀምጧል። ስለሆነም ሕገወጥነቱ እነዚህን የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች በመጣስ የተፈፀመ ዓይነት መሆኑ ከተረጋገጠ ሰራተኛው ወደ ስራ የመመለስ ወይም ካሣ ተቀብል የመሰናበቱ ምርጫ ለሰራተኛው ሣይሆን ለፍ/ቤቱ የተተወ ስለመሆኑ የአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43/1/ እና /2/ ድንጋጌዎችን በአንድነት በማንበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ፍ/ቤቱ በምን ላይ ተመስርቶ ተገቢውን ውሣኔ መወሰን እንደአለበት ደግሞ የአዋጁ አንቀጽ 43/3/ ድንጋጌ ያሣያል። በመሆኑም ሰራተኛውና አሰሪው አብሮ እንዱቀጥለ ማድረጉ ለምርታማነትና እንደስትሪያዊ ሰላም አመቺ ከሆነ ብቻ ግንኙነት እንዱቀጥል ማድረግ የሚቻል ሆኖ የዚህ ተቃራኒ ሁኔታ የሚያጋጥም መሆኑ ከታመነ ግን ፍ/ቤቱ ሰራተኛው የስራ ስንብትና ላላ ካሣ ተከፍልት የስራ ውለ እንዱቋረጥ ለመወሰን ሕጉ የሰጠው ሥልጣን ነው።
በተያዘው ጉዲይ ግን በአመልካችና በተጠሪ መካከል የስራ ግንኙነቱ እንዱቀጥል ማድረጉ ለምርታማነትና ኢንደስትሪያዊ ሰላም መሰናክል ላሆን የማይችል ነው ብል ለመደምደም አስቸጋሪ ስለመሆኑ ተጠሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመሣሣይ ጥፊት ሁለት ጊዜ ማጥፊታቸው መረጋገጡ አመላካች ሆኖ ተገኝቷል። የስር ፍ/ቤትም በተጠሪ የተጠየቀውን ዲኝነት በክርክሩ ሂደት ከተረጋገጡት ጉዲዮችና በሕጉ ለፍ/ቤቱ ከተተወው ስልጣን አኳያ በመመልከት ተጠሪ ተገቢ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ መወሰን እየተገባው ወደ ስራ እንዱመለሱ መወሰኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43/3/ ስር የተመለከተውን ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም ተጠሪ ካሣ ተከፍሎቸው ከስራ እንዱሰናበቱ ማዘዙ ሕጋዊ ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 246ዐ3 ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 61665 ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ለተጠሪ በሕጉ አግባብ ካሣ ከፍሎቸው ያሰናብቷቸው ብለናል።
በዚህ ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.