No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቢሲኒያ ባንክ (አ.ማ) - ነ/ፈጅ ደላ መራራ ተጠሪ፡- እነ አብደ አህመድ (266 ሰዎች) - ጠበቃ ምትኩ በዚህ መዝገብ የቀረበው አቤቱታ በመ/ ከቀረበው አቤቱታ ጋር በስረ ነገርም ሆነ በጭብጥ ረገድ ተመሳሳይ በመሆኑ ሁለቱም መዛግብት ጏን ለጏን ተመርምረው ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበውም ሆነ በመዝገብ የቀረበው የሰበር አቤቱታ ከፍርድ አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ሲሆን በዚህ መዝገብ የፍርድ ባለመብቶች የሆኑት የአሁን ተሰጠሪዎች በፍርድ ባለእዲ ጣና ትራንስፖርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻ አቅርበው የፍርድ ባለእዲው ንብረት ተሸጦ በአመልካች ባንክ በዝግ ሂሳብ እንዱቀመጥ የተደረገው ገንዘብ ወጭ ሆኖ እንዱከፈለን ይታዘዝልን በማለት ጠይቀው የአሁን አመልካችም ቀርቦ በፍ/ቤት የእግድ ትእዛዝ የተሰጠባቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ለብድር አከፊፈል በዋስትና የያዛቸው ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2857 መሰረት ከማናቸውም ገንዘብ ጠያቂ በፉት በተሽከርካሪዎቹ ላይ የቅድሚያ መብት ስላለኝ በእነዚህ ተሽከርካሪዎች ላይ የፍርድ አፈፃፀሙ ሉቀጥል አይገባም በማለት መቃወሚያ ማቅረቡን ተገንዝበናል። በተመሳሳይም በመ/ቁ. 42832 ተጠሪዎች የሆኑት እነ አቶ አበራ መለሰ በፍርድ ባለእዲው አበባው ደስታ የግል ትራንስፖርት ላይ የፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻ አቅርበው የባለእዲው ተሽከርካሪዎች ተሽጠው በአመልካች ባንክ በዝግ ሂሳብ እንዱቀመጥ የተደረገው ገንዘብ ወጭ ሆኖ እንዱከፈለን ይታዘዝልን በማለት አመልክተው በዚህ መዝገብም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2857 መሰረት ከማናቸውም ገንዘብ ጥያቄ በፉት የቅድሚያ መብት እንዲለው መቃወሚያውን አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 167 መሰረት በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የሚመነጭ ማንኛውም የሰራተኛ ክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የእዲ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚኖረው ስለተመለከተ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት የላለው ስለሆነ በአመልካች ባንክ በዝግ ሂሳብ እንዱቀመጥ የተደረገው ገንዘብ ወጭ ሆኖ ለፍርድ ባለመብቶች እንዱከፈል በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚሁ ትእዛዝ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ትእዛዝ ጉድለት የላለው ነው በማለት ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች በዋስትና በያዛቸው ንብረቶች ላይ የቅድሚያ መብት ሳያገኝ መቅረቱ ከአዋጅ ቁጥር 97/90 እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2857 እንደዚሁም ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አኳያ አግባብነቱ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ በሁለቱም መዛግብት ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሁፍና በቃል አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተሰጠው ሲሆን በበኩላችንም የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ መርምረነዋል። በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀሙ ሲቀጥል ለፍርድ ባለመብቶች የአሁን ተጠሪዎች ፍርድ ማስፈጸሚያነት እንዱሸጡ ትእዛዝ የተሰጠባቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ለብድር በዋስትና የያዛቸው ተሽከርካሪዎች እንደሆኑ ተረጋግጧል። ባንክ መያዣ የያዛቸውን ንብረቶች እዲው ሳይከፈለው በቀረ ጊዜ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ለተበዲሪው በመስጠት ያለማንም ጣልቃ ገብነት በመያዣ የያዘውን ንብረት በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 ላይ ተመልክቷል። ከዚህም ላላ መያዣ የተቀበለ ባለገንዘብ ከመያዣው ሽያጭ ዋጋ ከላልች ባለገንዘቦች ቀድሞ የመቀበል መብት እንዲለውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2857/1/ ላይ ተደንግጓል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች አንጻር አመልካች ከብድር አከፊፈል በመያዣነት በያዛቸው ንብረቶች ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለው መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩልም የአሰሪና ሰራተኛን ጉዲዩ በሚመለከተው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት በቅጥር ላይ ከተመሰረተ የስራ ግንኙነት የሚመነጭ ማንኛውም የሰራተኛ የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የእዲ ክፍያ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚኖረው በአንቀጽ 167 ላይ ተመልክቷል። አመልካች የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት በአሰሪው ላይ ላልች ገንዘብ ጠያቂዎች ክስ አቅርበው ያሰፈረደ ባለ ገንዘቦች በሚኖሩበት ጊዜ በፍርደ መሰረት ለነዚህ ባለገንዘቦች ክፍያ ከመፈጸሙ በፉት ሰራተኖች በአሰሪያቸው ላይ ክስ መስርተው ካስፈረደ ለሰራተኞቹ ቅድሚያ ክፍያ እንደሚፈጽም የሚያመለክት እንጂ ከዚህ አልፍ ባንኩ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን ንብረት ሕጉ በሰጠው ስልጣን መሰረት ሸጦ ለብድሩ እዲ እንዱውል ከሚያደርግ በስተቀር ከተቀበለው የመያዣ ንብረት ሽያጭ ላይ ለባለእዲው ሰራተኞች በቅድሚያ እንዱከፈል ተደርጏ ሉተረጏም የሚገባው አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ይሁንና በሕጉ ላይ ከፍ ብል እንደተጠቀሰው በቅጥር ላይ ከተመሰረተ የስራ ግንኙነት የሚመነጭ ማንኛውንም የሰራተኛ የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የእዲ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚሰጠው የተደነገገ እንደመሆኑ መጠን የላልች ገንዘብ ጠያቂዎች አቋም ተራ ገንዘብ ጠያቂዎች/ordinary creditors/ ወይንም እንደ አመልካች በመያዣ ብድር የሰጠ ባለገንዘብ /secured creditors/ ሆኑም አልሆኑ፤ የሰራተኛው የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ስለተደነገገ ይህ ሁኔታ ግምት ውስጥ ሉገባ እንደማይችል መገንዘብ እያዲግትም። ሕግ አውጭው የባንክ የክፍያ ጥያቄ ከሰራተኛም የክፍያ ጥያቄ ቅድሚያ ሉሰጠው እንደሚገባ ሐሳብ ቢኖረው በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 80 ላይ እንደተመለከተው ዋስትና የተሰጣቸው የላልች አበዲሪዎች የቅድሚያ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የግብር ሰብሳቢው መብት ግብር የመክፈል ግዳታ ባለበት ሰው ሐብት ላይ ከማናቸውም ላልች እዲዎች የቀደምትነት መብት ይኖረዋል በማለት እንደተደነገገው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅም ላይ ይህንኑ ያንጸባርቀው እንደበር ይታመናል።
ሲጠቃለልም ለሰራተኞች የሚከፈል የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይንም የእዲ ጥያቄ ቅድሚያ ሉሰጠው እንደሚገባ የተደነገገው በመያዣ በተያዘም ንብረት ላይ ተፈፃሚነት እንዲለው መገንዘብ ስሚቻል አመልካች በመያዣ በተያዙ ንብረቶች ላይ የቅድሚያ መብት ስላለኝ በእነዚህ ንብረቶች ላይ አፈፃፀሙ ሉቀጥል አይገባም በማለት ያቀረበውን አቤቱታ የስር ፍ/ቤቶች ሳይቀበለት መቅረታቸው በአግባቡ ስለሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33588 በ20/10/2000 እንደዚሁም በመ/ቁ. 33941 በ26/3/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ቁ. 69727 በ3/2/2001 እና በመ/ቁ. 74069 በ16/4/2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በአግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንተነዋል።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ፍርድ በመ/ቁ. 42132 ላይ ተፈፃሚነት ስላለው የፍርደ ግልባጭ ከመ/ ጋር እንዱያያዝ ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.