No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 38ዐ23 የካቲት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - መሰረት የማነ ቀረበ ተጠሪ፡- ብርሃኑ ደስዬ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት ኪራይ ውልን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ነው። በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው በወር ብር 8.ዐዐ /ስምንት ብር/ ኪራይ እየከፈለ ለመኖር የተከራየው ሰርቪስ ቤት ለዋናው ቤት አገልግልት እንዱውል የተሰራ በመሆኑ እንዱለቅ ቢጠየቅ ፈቃደኛ ስላልሆነ ተገድ ይወጣ ዘንድ ይወሰንበት በማለት ነው። ፍ/ቤቱ ከተጠሪ የቀረበውን መልስ ከሰማ በኋላ ክርክሩን መርምሮ የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች ያቀረበው ክስ የተሰረዘበት አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከተደረገው ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል እንደተገለፀው የግራ ቀኝ ወገኖች ግንኙነት የተመሰረተው በመሐከላቸው ተደርጎ በነበረው የቤት ኪራይ ውል ላይ ነው የቤት ኪራይ ውለ የተደረገው ለአንድ ዓመት እንዱቆይ ታስቦ ቢሆንም፤ ለብዙ ዓመታት እንደቆየ ከመዝገቡ ተመልክተናል። አመልካችም ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደታደሰ በመቁጥር በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2966/1/ በተመለከተው መሰረት ቤቱ ይለቀቅለት ዘንድ ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ አስቀድሞ ሰጥቶአል። ተጠሪ ደግሞ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠኝም ላላ ተለዋጭ ቤት እስካልተሰጠኝ ድረስ ቤቱን እንድለቅ አልገደድም። በመሐከላችን የተፈረመው ውልም የሚለው ይኸው ነው በማለት የተከራከረ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤቶችም ይህን ክርክር በመቀበል ነው የአመልካችን ክስ የሰረዙት።
ከመዝገቡ እንዲየነው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት እራሱን የቻለ የመኖሪያ ቤት ሣይሆን፤ ለአፖርታማ ተከራዮች አገልግልት ይውል ዘንድ የተሰራ ሰርቪስ ክፍል ነው። አመልካች ሰርቪስ ቤቱ እንዱለቀቅለት እንዱሁም ውለ ቀሪ እንዱሆን የጠየቀውም በዚሁ ምክንያት ነው። ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል የሚያበቃው ውለ እንዱያበቃ የሚፈልገው ተዋዋይ ወገን /አከራይ ወይም ተከራይ/ አስቀድሞ በሚሰጠው ማስታወቂያ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2966/1/ ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ አከራዩ አመልካች ሲሆን የቤቱም ባለቤት ነው። ተጠሪ ከአመልካች ጋር ሲነፃፀር በቤቱ ላይ የሚኖረው መብት በኪራይ የመጠቀም እንደመሆኑ ከባለሐብትነት ያነሰ ነው። ስለማይንቀሣቀስ ንብረት ኪራይ ትርጉም በያዘው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2896/1/ እንደተመለከተው ተከራይ የሆነው ወገን በጥሬ ገንዘብ ወይም በልላ ነገር ለአከራዩ እየከፈለ ለተወሰነ ጊዜ የሚኖርበትን ግንኙነት የሚፈጥር ነው። ይህ ግንኙነት ደግሞ ዘለዓለማዊ ወይም ማብቂያ የላለው ነው የሚባል አይደለም። ተለዋጭ ቤት ካልተሰጠኝ አልለቅም የሚለው የተጠሪ ክርክርም ከዚህ አንፃር ሲታይ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም። አመልካች ላላ ቤት መስጠት አልቻለም በሚልም የባለቤትነት መብቱን ማሣጣት በሕግ የሚደገፍ አይደለም። ተጠሪ ቤቱን የያዘው ከሰኔ 1 ቀን 1974 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ግን የባለቤቱን ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ቤቱን ይዞ የሚቆይበት ምክንያት የለም። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ትክክል ነው ለማለት አልቻልንም።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 61614 ታህሣሥ 18 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 53ዐ67 መጋቢት 2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ለአመልካች ያስረክብ ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.